• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዘራፊዎችን ለማጋለጥ ሁሉም ይተባበር!!

May 16, 2018 06:34 am by Editor Leave a Comment

በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው በደል፥ ሰቆቃ፥ ስደታና ሞት ቀጥሎሏል። በአንድአማራ ጽኑ እምነት አሁን ካለው የባሰና የከፋ ከመምጣቱ በፊት ጠላት በመቀነስ ላይ ያተኮረ ትግል መደረጉ ተገቢ ነው በሚል ሙሉ እምነት ይዘን ዘረኛውና እብሪተኛው የትግራይ ጽንፈኛ ቡድን ላይ በማነጣጠር ትግላችንን አጠናክረን ይዘን እንገኛለን። ይህ ጽንፈኛ ተገንጣይ የትግራይ ወያኔ ቡድን አማራውን በግንባር ቀድምትነት ጠላት አድርጎ በመፈረጅ በተመቸው አጋጣሚ ሁሉ በደል እየፈጸመ ይገኛል። በቅርቡ የተቀየሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም የአማራውን ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄና የመኖር ህልውና በማረጋገጥ ረገድ እየሰሩ አለመሆናቸዉን ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ነው።

ምንም እንኳን ጠ/ሚ አብይ አማራው የሚፈልገውን ጥያቄ ለመመለስ ባይችሉም በሚያደርጓቸው ትግሎች ላይ የጋራ ጠላታችንን የሚያነጣጥር ከሆነ አብረን መተባበር አለብን ብለን እናምናለን። ከሰሞኑ በተናገሩት የባለስልጣኖችን ሃብት የመያዝና ወደ ሃገር የማስመለስ ጉዳይ ከሁሉም በላይ የህወሃትን አባላት እና የዘረፋ አጋሮቻቸዉን እንደሚመለከት በማመን አብረን መቆም እንዳለብን እናምናለን። አማራውን ከቀየው በማፈናቀል፥ ሃብት ንብረቱን በመዝረፍ አልፎም መጭው ትውልዳችን ከፍሎ የማይጨርሰውን ዕዳ በመበደር የትግራይ ዘራፊ አምባገነኖችና ሆዳም አሽከሮቻቸው ሃብት ማካበታቸው ግልጽ ነው።

ስለሆነም እነዚህ ጽንፈኛና ተገንጣይ የትግራይ ወያኔ አባላትና ስራ አስፈፃሚዎቻቸዉ የኦህዴድ፥ ብአዴን፥ ዴህዴግ ጥቅመኞች በራሳቸው፥ በልጆቻቸው፥ በዘመዶቻነውና በጏደኞቻቸው በተለያዩ የውጭ ሃገራት ያጠራቀሟቸዉን ቤቶች፥ የንግድ ድርጅቶች፥ መኪኖች፥ መርከቦች፥ የእርሻ ቦታዎችና በተለያዩ ባንኮች የተከፈቱ ኣካውንቶችን ከመረጃና ማስረጃ ጋር በማጠናከር የሃገራችንን ሃብት እድናስመለስ እና በህግ ጠተያቂ ይሆኑ ዘንድ ለመታገል በጋር እንድንቆም ጥሪ እናቀርባለን።

በአንድ አማራ ንቅናቄ እምነት የአማራው ታሪካ ብቸኛው ጠላት ፥ ጠባቡና ትምክተኛው የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ህወሃት በመሆኑ፤ የእርስ በርስ ሽኩቻን ወደዳር በማለት ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ! አንድ አማራ ለሁሉም አማራ! በሚል የዚህ ዘመቻ የትግል አካል እንድትሆኑ ለሁሉም የአማራ ማህበረሰብና ለጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪ እናስተላለፋለን።

ትግላችን አማራው በነጻነት አያቶቹ በገነቧት ሃገሩ ኢትዮጵያ ላይ በክብር መኖር እስካልቻለ ፥ የሃገሩ እኩል ዉሳኔ ሰጭና ተጠቃሚ እስከሚሆን ድረስ ቀጣይ ነው። ነገር ግን በጋራ ጠላታችን ላይ በሚደረግ ማንኛውም የትግል እንቅስቃሴ ላይ ጠንካራ ክንዳችንን በማንሳት ጠላታችንን ድባቅ እንመታለን።በዚህ ጉዳይ ላይም የአንድ አማራ ንቅናቄ ኣመራር ኣካላት ከዚህ በፊት ይሄን ጉዳይ በማጥናት ስራ ከጀመሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር እንዲሁም ከአማራ የህግ ባለሙያና ከውጭ ሃገር የመንግስት አካላት ጋር አብረን እየሰራን መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

እዉነተኛ አማራ እንኳንስ ተነጋግሮ፥ ተያይቶ ብቻ መግባባት አለበት!!
የአንድ አማራ ንቅናቄ

Oneamhara1@gmail.com
www.oneamhara.org


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column, one amhara

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am
  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule