• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ነፃ ያልወጣች ሠንደቅ

May 15, 2018 09:47 pm by Editor 2 Comments

አዎ፤ አውሮፓዊው ቅኝ ገዢ ጣሊያን አድዋ ላይ ድል ሆኗል በ1888 ዓ/ም። በኢትዮጵያና ኢትዮጵያን በሚወክለው ቀስተ ደመናዊ ሠንደቅ ዓላማዋ ላይ ግን ከትውልድ የዘለለ ቂም ቋጥሮ የደማ ልቡን በመዳፉ ደግፎ በተቆረጠው ቋንጃው እያነከሰ አንድ እግሩን ኤርትራ ላይ ልብና ሌላ እግሩን ጣሊያን – አውሮፓ ላይ አድርጎና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ፍራንቺስኮ ክሪስፒን ከሥልጣን አባርሮ ድፍን ጣሊያን ሀዘን ተቀመጠ። አርባ ዓመት ሲታመምና ሲያገግም ኖረ። ጣሊያን በኢትዮጵያና በሠንደቋ ላይ ለአርባ ዓመት ያረገዘው ቂም ዱቼንና ፋሽስት ፓርቲን ወለደ። ለጣሊያን ትንሳዔ ኢትዮጵያ መሥዋዕት መሆን አለባት ሲል እነሆ ዱቼ በሮም አደባባይ ተጣራ። ሙሶሎኒ ኢትዮጵያን በመሥዋዕትነት ለተዋረደችው ጣሊያን ትንሳኤ አቀረበ። አውሮፓ አጨበጨበ፤ ቪቫ ዱቼ ሲል ደገፈ።

ጥቁር ለባሽ የፋሽስት ጦር ከጣሊያን ጫፍ እስከ ጫፍ ተነቃንቆ ኢትዮጵያን እንበቀላለን ሲል ቃል ገባ። በቫቲካንም ተባረከ። ዱቼም ለፋሽስቱ ጦር እንዲህ አለ፤- ሂዱና ኢትዮጵያን አንበርክኩ፤ የአባቶቻችንንም ውርደት ተበቀሉ፤ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀስተ ደመናዊ ሠንደቅ ዓላማዋን አውርዳችሁ እርገጡ፤ አቃጥሉም፤ ዳግም በዚያች ምድር እንዳይውለበለብም አድርጉ፤ ህገወጥ መለያቸው ነውና በሠይፍና በጥይት አግዱ፤ ሠንደቅ ዓላማውን ይዞ ሲያውለበልብም ሆነ ሲምል ለምታገኙት ሁሉ አንዳች ምህረት እንዳይኖራችሁ፤ መፍጀት እስከ ቻላችሁ ኢትዮጵያንና ሠንደቅ ዓላማዋን የሚለውን ሁሉ ፍጁት ምድሪቷንም አንድዱ፤ የምፅዐት ቀን በኢትዮጵያ ላይ አውርዱ፤ የጣሊያንን ባንዲራ በኢትዮጵያ ሠማይ ላይ አውለብልቡ – ድል ለፋሽስቶች፤ ሞት ለኢትዮጵያ – ሲል ወራሪና ቅኝ ገዢውን የፋሽስት ጦር ወደ ኢትዮጵያ አዘመተ – በ1928 ዓ/ም።

የቫቲካኑ ካሕን የፋሺሽቱን ጦር ሲባርኩ

እነሆም የምፅዐት ዘመን በሀበሻ ምድር ሆነ። አዎ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ በፋሽስቶች ተረገጠ፤ ተቃጠለ፤ ታገደ። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ በፋሽስቶች በይፋ ከኢትዮጵያ ሠማይ ላይ ተጋዘ። ተሰደደ። ህገ ወጥ ሠንደቅ ዓላማ ተብሎም ታወጀ። አረንጓዴ፤ ቢጫ ቀይ የኢትዮጵያን መለያ (መንግሥታዊ ያይደለ)  ህዝባዊ ሠንደቅ ዓላማ የያዘ ሁሉ በፋሽስት ጥቁር ለባሽ ኮማንዶና ጦር ሠራዊት በጥይት ተነደለ፤ በእግረ ሙቅ ተከረቸመ፤ በቆመጥ ህሊናውን እስኪስት ተወገረ፤ በሶማሊያ በኤርትራ እና በጣሊያን ደሴቶች እስር ቤቶች እየተወሰደ ታጎረ። በሀገሩ ምድርም ወህኒ ተወረወረ፤ ከሀገርም ተሰደደ። እነሆም ለአምስት ዓመት ኢትዮጵያ በጣሊያን ፋሽስቶች ሥር ወደቀች። እነሆም እልፍ ኢትዮጵያውያንም ስለ ሀገራቸውና ስለ ሠንደቅ ዓላማቸው ወራሪ ፋሽስቶችንና ምንደኛ ባንዶችን እየጣሉ ወደቁ።

በአምስቱ ዓመት የወረራና የግፍ አገዛዝ ዘመን የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ግን ለአንዲትም ደቂቃ ቢሆን ከኢትዮጵያ ምድር ከተራራውና ከጉድባው፤ ከዋሻውና ከገደላ ገደሉ ስር አሻቅባ ከመውለብለብ የሚያግዳት አንዳችም የፋሽስት ሃይል አልነበረም፤ የአርበኛው ሀይልና ጉልበት ሠንደቅ ዓላማውን ከፍ አድርጎ መያዝና ለነፃነቱ መዋደቅ ነበርና!! በአምስት ዓመት የኢትዮጵያ አርበኞች መሥዋዕትነት እነሆ ኢትዮጵያ ከዱቼ ፋሽስት መዳፍ ነፃ ወጣች፤ ታላቂቷም የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓለማ ነፃነቷን ተቀዳጅታ በኢትዮጵያ ሠማይ በነፃነት ተውለበለበች። ይህ የሆነው ከአንድም ሁለቴ በቀደመው ዘመን ነበር። (እነሆም በተከታታይ ትውልድ ሁሉ ሠንደቅ ዓላማችንን እንደ አባትም እንደ እናትም ፆታ እያፈራረቅን ዛሬ ድረስ የምንጠራው ለዚህ ነው)

የኢትዮጵያና የሠንደቅ ዓላማዋ ፍዳ ከጣሊያን ወረራ ጋር አላበቃም። ሶማሊያ የታላቋን ሶማሊያ ቅዠት እውን ለማድረግ ካንዴም ሁለቴ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ አቃጥላና ረግጣ፤ ኢትዮጵያንም ልታንበረክክ ተንጠራርታ ነበር። ኢትዮጵያንና ሠንደቅ ዓላማዋን የደፈረ በኢትዮጵያውያን አናብስት ክንድ መድቀቁ የታሪክ ሀቅ ነውና የታላቋ ሶማሊያም ቅዥት ያው ቅዠት ሆኖ ቀርቷል።

ዘረኝነት የተጠናወታቸው ዕብሪተኞች ግን ድሮም ሆነ ዘንድሮ ከታሪክ አልተማሩም ነገም አይማሩም፤ አይታረሙም። አብነት ቢባል የደደቢቱን ህወሃት የሚቀድም አይኖርም። እርግጥ ነው ያጎረሰን እጅ ነካሹን ሻዕቢያን አንረሳም። በኢትዮጵያና በሠንደቅ ዓላማዋ ላይ የዋለውን ግፍ ለታሪክ ትተነዋል። እንደ ሻዕቢያና ህወሃት ሁሉ ኦነግም የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ አዋርዷል፤ ዘልፏል፤ በተረታ ተረት ትርክት በኢትዮጵያና በተጋመደው የህዝቦች አንድነቷ ላይ ተዘባብቷል። ኢትዮጵያ ላይ በኦቦ ለማ መገርሳ አስገምግሞ የተነሳው ኢትዮጵያዊነት በ‘ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው!” አዝማች ኮከብ መርህ እነሆ ዛሬ ላይ ‘ኢትዮጵያዊነት የለም’ እና ‘ኢትዮጵያዊ ስለመሆናችን መደራደር’ ለሚሉት ኦነጋውያን ሁሉ ትዝብት ሆነ እንጂ ትርፉ!

በአዲስ አበባ የጣሊያን ባንዲራ ወርዶ የኢትዮጵያ ሠንደቅዓላማ በእንግሊዝ ወታደሮች ሲሰቀል – ፎቶው የተወሰደው ከዚህ ነው

ዱቼ በራሱ ህዝብ ተዋርዶ ህይወቱን ከማጣቱ በፊት ያኔ ጥቁር ለባሾችን ኢትዮጵያ ላይ ሲያዘምት ለትግራይ ምንደኞች /ባንዶች/ የላከላቸው መልዕክት ነበር፤ አማራና ኦሮሞ ጠላቶቻችሁን ልናጠፋና እናንተን ልናሳድግ በእነሱም አናት ላይ እናንተን ልናበለፅግ የመጣን በመሆኑ ከእኛ ጋር ቆማችሁ ዓላማችንን አራምዱ። አማራና ኦሮሞን ተባብረን ‘እሳትና ጭድ’ እናርጋቸው – የሚል። ያኔ የዱቼ ዓላማና ግብ በአብናቶቻችን አርበኞች ደምና አጥንት በአጭር ተቀጨ። ቅኝ አገዛዙም ተሰባበረ። ዱቼም ሞተ ተቀበረ። ፋሺዝም በሀገረ ጣሊያን ተንኮታኮተ። ነገር ግን እነሆ ከትግራይ ምንደኞች የተወለዱት የህወሃት መሥራቾች ደደቢት በረሃ ገብተው ዱቼን ከሙታን መንደር አንስተው ከመንፈሱ ጋር ተጋቡ። እነሆም ዱቼ በደደቢት በረሃ በህወሃት አድሮ ህወሃትን ሆነ። ህወሃትም የዱቼን መንፈስ ወረሰ። ፋሽዝምም በህወሃት ተተካ። ህወሃትም ፋሽሰትን ሆነ። የዱቼ መልዕክትና ዓላማ /አማራና ኦሮሞን በማባላት የትግራይን የበላይነት ማስፈን/ ከ1967 ዓ/ም ጀምሮ እስከዚህ ዘመን የህወሃት ማኒፌስቶ ሆነ። የህወሃት መለያ!!

ዱቼ በአካል ቢሞትም ዓላማው በህወሃት አልሞተም። እነሆ ዱቼም በመለስ ተቀየረ፤ መለስም ዱቼን ሆነ። ጥቁር ለባሹ የዱቼ ወራሪ በህወሃት አጋዚ ወራሪ ተተካ። ከደደቢት እስከ አራት ኪሎ ህወሃት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ እንዳዋረደ፤ እንደረገጠ፤ እራፊ ጨርቅ እያለ ቁሳቁስ እየቋጠረ አንደተዘባበተበት በግፍና በንፁሃን ደም እየዋኘ እንደ ዱቼ አዲስ አበባን በበቀለኛውና ቂመኛው ወራሪው ጦር ተቆጣጠረ። እነሆም ኢትዮጵያና ሠንደቅ ዓላማዋ በሀገር በቀሉ ወራሪና ቅኝ ገዢ ህወሃት መዳፍ ሥር ከግንቦት 20/1983 ዓ/ም ጀምሮ እስካለንበት ዘመን 2010ዓ/ም ድረስ እየማቀቁና እየተሰቃዩ ይገኛሉ። (ይህ ግፍ በአብይ ዘመነ መንግሥት ይቀየራል ብለን ተስፋ ጥለናል።)

እነሆም ኢትዮጵያን ባስተዳደሩት መሪዎች በየትኛውም ዘመነ መንግሥት ውስጥ ተደርጎና ተሰምቶ የማያውቀውን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ (የመንግሥት ዓርማ ያይደለ) የኢትዮጵያን ህዝብ ሠንደቅ ዓላማ ፋሽስት ወራሪ ህወሃት አዋጅ አውጥቶ በወንጀለኛ ሠንደቅ ዓላማነት ፈርጆ በኢትዮጵያ ሠማይ ላይ እንዳይውለበለብ አገደ። ከወራሪው ዱቼ ዘመን ቀጥሎ ሠንደቅ ዓላማችን በወንጀለኝነት ከኢትዮጵያ ሠማይ ላይ ሲታገድ ሁለተኛው በዘመነ ህወሃት/ኢህአዴግ መሆኑ ነው። ንፁሁን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሠንደቅ ዓላማ መያዝ በህወሃት አጋዚ ጦር በጥይት ያስነድላል። በወህኒ ቤቶች ለግፍና ለቶርቸር ይዳርጋል። በሽብርተኝነት ያስከስሳል። ከሀገር ያሰድዳል።

በኢትዮጵያ ምድር ግን እንዲህ የነበረው በአምስቱ ዓመት የፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ ዘመን ብቻ ነበር። ህወሃት ሀገር በቀል ወራሪና ቅኝ ገዢ ከመሆኑ በቀር ተፈጥሮውም ሆነ እርኩሰቱ፤ ለኢትዮጵያና ለሠንደቅ ዓላማዋ ያለውም ጥላቻ ከአምስቱ ዓመት የዱቼ ቅኝ አገዛዝ ቢብስ እንጂ የሚያንስ አይደለም።

የተስፋይቱን ምድር ኢትዮጵያን የሚጠብቃት አንድ አምላክ በየዘመኑ ከጥፋት የሚታደጋትን ትውልድና መሪ ባልታሰበ ወቅት ባልታሰበ ዘመን እያስነሳ ተዓምር ሲታይ ቆይቷል። በ2010 ዓ/ም በወርሃ መጋቢት የሆነውም ይኸው ነው። በኦህዴዱ ለማ መገርሳ እና በብአዴኑ ገዱ አንዳርጋቸው ቲሞች የታገዘው በኢህአዴግ ማህፀን ያደገውና የህወሃትን እርኩሰት የተጠየፈው አብይ አህመድ /ጠቅላይ ሚኒስትር/ ሆኖ ተነስቷልና! እኛም ኢትዮጵያን አስቀድሞ ኢትዮጵያን ከፍ ላደረገ እንደ ኢትዮጵያዊም እንደ ሰውም ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ የነገ ተስፋና ሠላም ፍቅርና ብልፅግና አንድነትና ህብረት ድጋፋችንና ዝግጁነታችን እንደ አባቶቻችን ነውና አብይንና ቡድኑን የደገፍነውና ተስፋም የሰነቅነው በሙሉ ጉልበትና ፍላጎትም ከጎኑ የቆምነው እነሆ ለዚህ ነው! ለዚህም ነው ይህንን መልዕክት በቀጥታ ለጎልማሳው ጠቅላይ ሚኒስትር ለተከበረው ዶ/ር አብይ አህመድ እና በዙሪያው ለቆሙት ኢትዮጵያውያን መሪዎች ሁሉ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ከትህትና ጋር የምናስተላልፈው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሆይ!! የኢትዮጵያንና የህዝቧን ሠንደቅ ዓላማ የወነጀለውንና ከኢትዮጵያ ሠማይ ላይ ያገደውን የህወሃትን ህገ ወጥ አዋጅ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ በህጋዊ አዋጅ አንሳልን!!! ይህንን የምንጠይቅህ በበዓለ ሲመትህ መጋቢት 24/2010 ዓ/ም ላይ በክብርና በታላቅ የጀግንነት አክብሮት ደጋግመህ ባነሳሃቸው በአድዋ በመተማ በማይጨው በካራማራና በባድመ ይህቺን ዛሬ የተወነጀለችውን ንፁህ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የኢትዮጵያን መገለጫ ሠንደቅ ዓላማ ከፍ አድርገው በተሰዉት እልፍ አእላፍ ኢትዮጵያውያን አጥንትና ደም ነው።

በባድመ ሠማይ ላይ የተውለበለበው ሠንደቅ ዓላማ

አብይ አህመድ ሆይ! ሌላውን የመሥዋዕትነት አውድማ ሁሉ አቆይተን አንተ ወታደር በነበርክበት ኢህአዴግ አማካይነት በተካሄደው አሰቃቂው የኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት በባድመ ሠማይ ላይ የተውለበለበው ሠንደቅ ዓላማ ንፁሁ /የመንግሥት ዓርማ ያይደለ/ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሠንደቅ ዓላማ አልነበረምን? እንደምን ቢሆን ነው ሌላው ሁሉ የመሥዋዕትነት ታሪክ ‘ቢረሳ/ቢካድ’ እንኳን በዚያ ጦርነት የተሰዋው 70ሺ(?) የሚገመት ኢትዮጵያዊ ባድመ ላይ ያውለበለበው የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ወንጀለኛና ሽብርተኛ የሚሆነው?! ይህ በቃላት ልንገልፀው የማንችል እጅግ መሪር ሀገራዊ ክህደትና ወንጀል የተፈፀመው ዛሬ አንተ በምትመራውና ያኔ ህወሃት በሚያሽከረክረው ኢህአዴግ ነው። ስለ ኢትዮጵያ ታሪክና ስለ ኢትዮጵያውያን ጀግንነትና የነፃነት ተምሳሌነት ሲተረክና ሲነገር በዚህ ታሪክ ውስጥ ሁሉ /ዛሬ በሽብር ምልክትነት በደደቢቱ ህወሃት የተወነጀለው/ የኢትዮጵያ ህዝብ ሠንደቅ ዓላማ አለ።

ነፃነቷን በህወሃት/ኢህአዴግ የተገፈፈችው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ /የመንግሥት ዓርማ ያይደለች/ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ነፃ ሳትወጣ ስለ ኢትዮጵያውያን ጀግንነትና የጥቁር ህዝቦች ነፃነት ሠንደቅ ተምሳሌነት በአደባባይ መዘከር ምን ማለት እንደሆነ በቃላት ማስቀመጥ አንፈልግም፤ አንተ የተከበርከው ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የታሪክ ሰው ነህና። ሠንደቅ ዓላማችን በሽብርተኝነት ተወንጅላና ከሀገር ተባርራ የሠላም ዓየር የሚተነፍስ ኢትዮጵያዊ አይኖርምና አብይ አህመድ ሆይ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ምላሽህን እንጠብቃለን!! ሠንደቅ ዓላማችን ነፃ ትውጣ!!! አዎ! የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ነፃ ትውጣ!!!

ኢትዮጵያ በቅን መሪዎቿና በእግዚአብሄር እርዳታ ትንሳኤዋ ዕውን ይሆናል!

ግንቦት 2010 ዓ/ም (ሜይ 2018) በህወሃት/ኢህአዴግ የአገዛዝ ዘመን 28ኛ ዓመት ዋዜማ ተፃፈ።

መስፍን ማሞ ተሰማ፤ሲድኒ አውስትራሊያ

mmtessema@gmail.com

ዋቢ

  1. ለዚህ ፅሁፍ አቅርቦት በሚስማማ መልክ /ከህወሃት ዓላማና ግብ/ አኳያ የተፍታታው ዱቼ ለትግራይ የላከው መልዕክት የተገኘው ‘የሀበሻ ጀብዱ’ በአዶልፍ ፓርለሳክ ተፅፎ በተጫኔ ጆብሬ መኮንን ከተተረጎመው መፅሀፍ ነው።
  1. በባድመ ሠማይ ላይ ስለተውለበለበችው ንፁህ /የመንግሥት ዓርማ ያይደለች/ የኢትዮጵያ ህዝብ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ፤

“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Ethiopia, flag, Left Column, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    May 17, 2018 12:48 am at 12:48 am

    ወልቂጤዎች!ይቺ ባንዲራ የማናት? የቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ እንዳትሏት ተናካሹ ኣውሬው ከነዘውዱ የለም። የደርግ ነው እንዳንል፤ ዘውዱን ነው የቀነጨበው። ይቺ ባንዲራ፣ የናንት ጨበርባሪዎች ሳትሆን ትቀራለች? ብርሃኑ ነጋ ቦንገር ነው የሚያውለበልባት?

    Reply
    • Bertu Le Ethiopia says

      May 17, 2018 08:01 pm at 8:01 pm

      Woyane, the enemy of Ethiopia forever. Period.

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው September 21, 2023 02:38 pm
  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am
  • ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ September 7, 2023 01:40 pm
  • “እንኳን ተለያይተንና እርስ በርስ ተባልተን በአንድነት ቆመንም ወጀቡን መሻገር አቅቶናል” September 7, 2023 01:31 am
  • ራሱን መሪ አልባ የሚያደርገው አማራ ክልል August 24, 2023 11:50 pm
  • ጀብደኛው August 24, 2023 10:06 am
  • ጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ተመልሰዋል August 13, 2023 10:55 pm
  • ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች August 13, 2023 10:26 pm
  • ሪፖርተር የፓርላማ ወንበር አስልቶ የአስቸኳይ አዋጁ በፓርላማ እንዳይደገፍ አቅጣጫ አመላከተ August 13, 2023 09:11 pm
  • ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው August 11, 2023 12:52 pm
  • የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል August 10, 2023 04:31 pm
  • “አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት) August 10, 2023 09:44 am
  • “አርበኛ” መሳይ – “የድል ዜና” ሳይበርድ 50ሺህ ዶላር በጎፈንድሚ August 10, 2023 09:08 am
  • በሕዝቡ ድጋፍ ከተሞች ከዘራፊው መንጋ ሥጋት ነጻ መሆናቸው ይፋ ሆነ August 9, 2023 11:47 am
  • ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ  August 8, 2023 05:47 pm
  • “ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚሉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የመከላከያ ሠራዊት August 1, 2023 09:25 am
  • ደቡብ አፍሪካ የመሸጉ ወንጀለኞች ለሕግ ተላልፈው ሊሰጡ ነው July 31, 2023 09:27 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule