አዎ፤ አውሮፓዊው ቅኝ ገዢ ጣሊያን አድዋ ላይ ድል ሆኗል በ1888 ዓ/ም። በኢትዮጵያና ኢትዮጵያን በሚወክለው ቀስተ ደመናዊ ሠንደቅ ዓላማዋ ላይ ግን ከትውልድ የዘለለ ቂም ቋጥሮ የደማ ልቡን በመዳፉ ደግፎ በተቆረጠው ቋንጃው እያነከሰ አንድ እግሩን ኤርትራ ላይ ልብና ሌላ እግሩን ጣሊያን - አውሮፓ ላይ አድርጎና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ፍራንቺስኮ ክሪስፒን ከሥልጣን አባርሮ ድፍን ጣሊያን ሀዘን ተቀመጠ። አርባ ዓመት ሲታመምና ሲያገግም ኖረ። ጣሊያን በኢትዮጵያና በሠንደቋ ላይ ለአርባ ዓመት ያረገዘው ቂም ዱቼንና ፋሽስት ፓርቲን ወለደ። ለጣሊያን ትንሳዔ ኢትዮጵያ መሥዋዕት መሆን አለባት ሲል እነሆ ዱቼ በሮም አደባባይ ተጣራ። ሙሶሎኒ ኢትዮጵያን በመሥዋዕትነት ለተዋረደችው ጣሊያን ትንሳኤ አቀረበ። አውሮፓ አጨበጨበ፤ ቪቫ ዱቼ ሲል ደገፈ። ጥቁር ለባሽ የፋሽስት ጦር ከጣሊያን ጫፍ እስከ ጫፍ … [Read more...] about ነፃ ያልወጣች ሠንደቅ
flag
ያስፈራል፤ ግን ኢትዮጵያ አትፈርስም!
ይቺ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ስንት የመከራ ወንዞችን ተሻግራለች! ገና ስንት ትሻገራለች! ስንት የግፍ ተራራዎችን አቋርጣለች! ገና ስንት ታቋርጣለች! ስንት የበደል ሰይፎችንና ጦሮችን አምክናለች! ገና ስንት ታመክናለች! ስንት የውጭ ኃይሎችን አሳፍራለች! ገና ስንቱን ታሳፍራለች! ስንት አምባገ- ነኖችን እያለቀሰች ቀብራለች! ገና ስንቱን ትቀብራለች! ጭቆና ከኢትዮጵያውያን ደም ሙልጭ ብሎ ወጥቶ በነፃነት፣ በእኩልነት፣ በዳኝነት በጠራ ደም እስቲተካ ድረስ “ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ” ትጸልያለች! እግዚአብሔርም ቃል ኪዳን አለበት ይሰማታል! የኃያላን ኃያል ኢትዮጵያ እንድትፈርስ አይፈቅድም! የኢትዮጵያን መፈራረስ የሚመኙ ግለሰቦችም መንግሥቶችም ሞልተዋል፤ ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ የሚመኙ ጭንጋፍ ልጆችም አሏት፤ ማኅጸንዋ እየደማ እየረገማቸው ሰላምና እንቅልፍ አጥተው … [Read more...] about ያስፈራል፤ ግን ኢትዮጵያ አትፈርስም!