ዶ/ር አብይ ጠ/ሚ ሆኖ ከተመረጠ በኋላ በበጎ የሚነሱና አንዳንዴም በዚህ ፍጥነት ይሆናሉ ተብሎ የማይጠበቁ ነገሮችን አድርጏል (የለማና የገዱ ከእሱ ያልተናነስ አስተዋፆ ሳይዘነጋ)። ከእነዚህም ውስጥ ጎልተው የሚወጡት ስለኢትዮጵያዊነት መናገር እንደ ወንጀል መቆጠሩ ቀርቶ ሊኮራበት የሚገባና ብዙ ዋጋ የተከፈለበት መሆኑን ማሳየቱ፥ በኦሮሞ ወገኖቻችን ዘንድ የነበረውን አንዳንድ ጥርጣሬ አስውግዶ ኦሮሞ ከሌላው ህዝብ እኩል መሰዋትነት ከፍሎ ባቆያት ሀገር ውስጥ ሆኖ የፍትህና የእኩልነት ጥያቄውን ማስመለስ እንደሚችል ማሳየቱ ፥ በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ለእስርና ለእንግልት የተዳረጉ ወገኖቻችንን ከእስር እንዲፈቱ ማድረግ፥ ለዚህም አንዳርጋቸው ፅጌን ከመፍታት የበለጠ ምንም አይነት ማስረጃ አያስፈልግም። አንዳርጋቸው ምንም እንኳን ምርጥ የፍትህና የእኩልነት ታጋይ ቢሆንም ከመረጠው የትግል … [Read more...] about የ ጠ/ሚ አብይ አህመድ በጎ ጅማሪዎችና ቀጣዩ ፈተና
Opinions
የኔ ሃሳብ
ከዲያስፖራው ጋር የሚደረገው ውይይት ትርጉም እና ፋይዳ ይኖረው ዘንድ በእውነተኛ የለውጥ እርምጃዎች የታጀበ ይሁን!!
ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ በመጭው ነሀሴ ወር 2010 ዓ.ም. ወደ አሜሪካን አገር እንደሚመጡ እና ከዲያስፖራው ማህበረሰብ ጋር የመወያዬት እቅድ እንዳላቸው በስፋት እየተነገረ ይገኛል። በአገር ውስጥም ይሁን በውጭ አገር ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ማወያዬት የሚደገፍ ሀሳብ ቢሆንም፣ የሚደረጉት ውይይቶች የአገራችንን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መሰረታዊ በሆነ መልኩ ለመፍታት እገዛ የሚያደርጉ መድረኮች ሊሆኑ ይገባል። አገራችን ኢትዮጵያ ስር የሰደዱ፣ ዘመን የጠገቡ እና ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች ያሉባት አገር ነች። እነዚህ ችግሮች ደረጃ በደረጃ መፍትሄ ያገኙ ዘንድ አገራችን በትክክለኛው የለውጥ ጎዳና ላይ መጓዝ ይኖርባታል። በመሆኑም፣ ከዲያስፖራው ጋር የሚደረግ ውይይት ከዘላቂ መፍትሄ አኳያ የሚቃኝ እንጂ የአጭር ጊዜ ግብ ለማሳካት የሚደረግ የህዝብ ግንኙነት … [Read more...] about ከዲያስፖራው ጋር የሚደረገው ውይይት ትርጉም እና ፋይዳ ይኖረው ዘንድ በእውነተኛ የለውጥ እርምጃዎች የታጀበ ይሁን!!
ዱካውን ማደን!
“የነፃነት ታጋይ” መባልን እንጂ ነፃነትን የማንፈልግ ዜጎች ሞልተናል! በዶክተር አብይ አህመድ እና በግብረ አበሮቹ መሪነት እየተነቃቃ ያለው የርቅ እና የሆደሰፊነት ባህል አስደናቂ ነው። በታሪክ ብርቅ ከሆኑ ክስተቶች አንዱን ያስታውሰኛል። በየጁ የምስፍና ዘመን ደጃዝማች ውቤ የተባሉ መስፍን የራስ አሊን መንግስት ለመቀማት ፈለጉ። በግብጡ ጎረምሳ አቡነ ሰላማ አይዞህ ባይነት በራስ አሊ ላይ ዘመቱ። ደብረታቦር ላይ ቅልጥ ያለ ጦርነት ተደርጎ ውቤ እና አቡነ ሰላማ ተሸንፈው ተማረኩ። በጊዜው ልማድ የተማረከ ሰው ህይወቱን ያጣል። በድል ነሺው እንዲኖር ከተፈቀደለት እንኳ እጁን ይቆረጣል፤ ወይም አይኑ በወስፌ ይፈርጣል። በቅንነት ተገፋፍተው ይሁን ትርፍና ኪሳራውን አስልተው አይታወቅም-ራስ አሊ ግን ይህን ከማድረግ ታቀቡ። ምርኮኞችን ምሳ ጋብዘው በምህረት ወደ ጥንቱ ሹመታቸው … [Read more...] about ዱካውን ማደን!
“ከአሁን ወዲህ ተገቢውን የህዝብ ድምጽ ሳያገኙ እዚህ ወንበር ላይ መቀመጥ አይቻልም”
የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ የግንቦት 20 ክብረበዓልን አስመልክቶ ካደረጉት ንግግር በወፍ በረር ተመርጦ የተተረጎመ ሀሳብ፤ ዴሞክራሲ በወሬ ብቻ አይመጣም፤ የሚሰባበረውን መሰባበር የሚነቀለውን መንቀል ያስፈልጋል። ባህላችንም ዴሞክራሲን እንዲሰፋ የሚያግዝ ሳይሆን በተቃራኒው እንዲቀጭጭ የሚያደረግ ስለሆነ እሱ ላይም መስራት አለብን። እስረኛውን እንደወራጅ ወንዝ እየለቀቅን ያለነው እስርቤት ለመዝጋት እቅድ ስላለን ሳይሆን አዲስ የፖለቲካ አየር ለመፍጠር ስለምንፈልግ ነው። በኦሮሚያ በአንድ አመት ውስጥ 40ሺ እስረኛ በላይ የለቀቅነው ግለሰብን ብቻ ነፃ ለማውጣት ስለምንፈልግ እንዲሁም ለመወደድ ወይም እንዲጨበጨብልን ስለፈለግን ሳይሆን የመጠላለፍ እና የመጠፋፋት ባህላችንን ለመቀየር ነው። ሰዎችን ከእስርቤት ብቻ አይደለም ነጻ ያወጣነው . . . … [Read more...] about “ከአሁን ወዲህ ተገቢውን የህዝብ ድምጽ ሳያገኙ እዚህ ወንበር ላይ መቀመጥ አይቻልም”
ሃቀኛው መላኩ ፈንታ
መልከ ቀና ነው፤ ፀጉሩ እንደ መኸር ጤፍ ተኝቷል። ሲራመድ ይፈጥናል። ወደ ምኒሊክ ቤተመንግሥት እየገባ ነው። ገባ። “አቶ መለስ ሦስት ምርጫዎች አሉኝ!” ቀጠለ። አንድ ህግ ተክትዬ መሥራት፣ ሁለት እያስመሰልኩ መኖር፣ ሶስተኛ ሳልሰራ በሪፖርት መኖር! አቶ መለስ በምርጫው ተደንቀው “በህግ ስራ፤ ማንም ከህግ በታች ነው” አሉት። የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ንግግር ከራሱ እሳቤ ጋር ተጣጣመ። የሚኒስቴር የቤተሰብ መኪና አልቀበልም ብሎ ቤተሰቡ በአዲስ አበባ የታክሲ ሰልፍ መያዝ ለመዱ። ቁርስ እና ምሳውን ከመስሪያ ቤቱ ካፍቴሪያ በ15 ብር እየተመገበ ሥራውን አጧጧፈ። አንድ የክልል ቢሮ ኃላፊ ቢያንስ ሁለት መኪና እና መኖሪያ ቤት ይሰጠዋል። ለዚህ ሰው ግን የለውም ።በጭቃ ቤት ይኖራል። ሰውየው የገቢዎች እና ጉምሩክ ኃላፊ ነው። ሚኒስትር ነው። የሃገሪቱ ገንዘብ በመዳፉ ቢያልፍም ወደ … [Read more...] about ሃቀኛው መላኩ ፈንታ
ESFNA is at a Crossroads- Should it allow Dr. Abiy address the Diaspora or not?
One's leadership is tested when confronted with tough decisions. ESFNA's leadership is at a crossroads. The decision in front of them makes or breaks the organization. It is going to leave a positive or negative scar in the history of the organization. The decision? They have to make a quick decision, by tomorrow, whether to allow the newly named Prime Minister of Ethiopia- Dr. Abiy Ahmed, to address the Diaspora community at this year's annual event in TX. By the way, if the info I got is … [Read more...] about ESFNA is at a Crossroads- Should it allow Dr. Abiy address the Diaspora or not?
ጠባብነት እና ትምክህት
ከ2 አመት በፊት፦ ጠባብነት እና ትምክህት ኢህአዴግ እንደ ፓርቲና መንግስት የችግሮች ሁሉ መንስዔ አድርጎ የሚወስደው የጥገኝነት አስተሳሰብና ተግባራትን ነው። ለህዝቡ ሰላም እና ለፌደራል ሥርዓቱ አደጋ ናቸው ከሚላቸው ውስጥ፡- ጠባብነት እና ትምክህተኝነት የሚሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ። እነዚህ ቃላት በመንግስት ድክመት ምክንያት ለተፈጠሩ ችግሮች ሌሎችን ተጠያቂ (externalize) ለማድረግ ነው። በመሠረቱ “ትምክህተኛ” የሚለው እሳቤ የአማራ ብሔር ተወላጆችን በባህላቸውና በታሪካቸው ላይ ያላቸውን የራስ መተማመን ስሜት የሚሸረሽር ነው። በዚህ መልኩ የሚደረገው ተፅዕኖ በአማራ ልሂቃን ላይ የማንነት ቀውስ (identity crisis) ይፈጥራል። በዚህ መሰረት፣ አንድ ሰው በአማራነቱ ብቻ “ትምክህተኛ” እየተባለ ታሪኩና ማንነቱ እንደ ጥፋት ሲቆጠር በውስጡ የብሔርተኝነት ስሜት … [Read more...] about ጠባብነት እና ትምክህት
ታሪክ የወረሰ ትውልድ፣ ያልተወለዱ ህልሞችና የማዋለጃው መንገድ
የዛሬ 150 ዓመት በሕይወት ብንኖር ኑሮ ብዙዎቻችን ምንአልባት ሁላችንም በዘመኑ ከኖሩት አባቶቻችን ጋር በአንድ የአስተሳሰብና የኑሮ ዘይቤ ምህዋር ላይ እንደምንተም እገምታለሁ። የነበረውን የህይወት ከባቢ እንደዘላለማዊና የማይቀየር እውነት በመቁጠር እንደምንመላለስ አስባለሁ። ፈጣሪ በማይቋረጠው የዘመናት ጐዳና ላይ በየዘመኑ የሚያስነሳቸው ታላላቆች ግን ጨለማ ባጠቆረው ሰማይ ላይ እንደሚበር አብሪ ኮከብ ለሁሉም እንዲታዩ ሆነው ይምዘገዘጋሉ። ኢትዮጵያ በታሪክ ደርሳናቷ ላይ የሚንቦገቦጉ፣ የዘመንን ጢሻ እየመነጠሩ ከትውልዶች ጋር የሚተሙ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ነበሯት። አሏት። ከእነርሱ መካከል ዛሬ ከምንዘክራቸው አፄ ቴዎድሮስ አስቀድመን የመጀመሪያው እረድፍ ላይ ማንን ልናቆም እንችላለን? እውቁ የዘመናዊ ታሪክ ፀሐፊው ሊቀ - ጠበብት ባህሩ ዘውዴ Society and State in … [Read more...] about ታሪክ የወረሰ ትውልድ፣ ያልተወለዱ ህልሞችና የማዋለጃው መንገድ
ወልቃይት እንደ ካሽሚር
የወልቃይት መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች እና የዋልድባ መነኮሳትን ጨምሮ ከመቶ በላይ ከእስር ቤት የተለቀቁ የዴሞክራሲና የፍትህ ተቆርቋሪ ታጋዮች በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ግንቦት 2 ቀን 2010 ዓ.ም በተደረገላቸው የክብር ራት ግብዣ ላይ የተገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለታዳሚው ያደረገውን ንግግር ከተመስገን ባገኘነው ፈቃድ መሠረት ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ አንባቢያን እንደወረደ በሚከተለው መንገድ አቅርበነዋል። በዕለቱም ለህሊና እስረኞች የተለያየ ስጦታም እንደተበረከተ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። እዚህ የተሰበሰባችሁ ታላላቆቼም፣ ታናናሾቼም በመጀመሪያ እንኳን ለዚህ ዕለት አበቃችሁ፤ አበቃን። በተለይም ባለፉት ሁለት አስርታት የወልቃይትን ሕዝብ የማንነት፣ የፍትሕ፣ የዴሞክራሲ እና የፖለቲካ ጥያቄ አደባባይ እንዲወጣ በተወለዳችሁበት አፈር ላይ ተተክላችሁ ለከፈላችሁት ውድ ዋጋ ጥልቅ … [Read more...] about ወልቃይት እንደ ካሽሚር
የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ ፓርቲ መግለጫ
መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው። … [Read more...] about የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ ፓርቲ መግለጫ










