
ዶ/ር አብይ ጠ/ሚ ሆኖ ከተመረጠ በኋላ በበጎ የሚነሱና አንዳንዴም በዚህ ፍጥነት ይሆናሉ ተብሎ የማይጠበቁ ነገሮችን አድርጏል (የለማና የገዱ ከእሱ ያልተናነስ አስተዋፆ ሳይዘነጋ)። ከእነዚህም ውስጥ ጎልተው የሚወጡት ስለኢትዮጵያዊነት መናገር እንደ ወንጀል መቆጠሩ ቀርቶ ሊኮራበት የሚገባና ብዙ ዋጋ የተከፈለበት መሆኑን ማሳየቱ፥ በኦሮሞ ወገኖቻችን ዘንድ የነበረውን አንዳንድ ጥርጣሬ አስውግዶ ኦሮሞ ከሌላው ህዝብ እኩል መሰዋትነት ከፍሎ ባቆያት ሀገር ውስጥ ሆኖ የፍትህና የእኩልነት ጥያቄውን ማስመለስ እንደሚችል ማሳየቱ ፥ በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ለእስርና ለእንግልት የተዳረጉ ወገኖቻችንን ከእስር እንዲፈቱ ማድረግ፥ ለዚህም አንዳርጋቸው ፅጌን ከመፍታት የበለጠ ምንም አይነት ማስረጃ አያስፈልግም። አንዳርጋቸው ምንም እንኳን ምርጥ የፍትህና የእኩልነት ታጋይ ቢሆንም ከመረጠው የትግል መንገድ አንጻር እንዲፈታ መደረጉ በቀላሉ ሊታይ አይገባውም። ለለውጥ ያለውን ቁርጠኝነት ያመላክታል። ቂመኞቹ አሁንም ከሀገር አንጋግተው ሊያባርሩት ሲያሴሩ ዶ/ር አብይ በክብር ቤተመንግስት ጠርቶ በማናገሩ ያልተደመመ ያለ አይመስለኝም። የታሰሩትን ከመፍታት በተጨማሪ በተፈበረከ የ አሸባሪነት ክስ ለስደት የተዳረጉ ምርጥ ኢትዮጵያዊያንን ክስ ማንሳትና ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማቅረቡ ሌላው ወሳኝ እርምጃ ነው። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
Leave a Reply