• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዱካውን ማደን!

May 31, 2018 08:28 am by Editor 11 Comments

  • “የነፃነት ታጋይ” መባልን እንጂ ነፃነትን የማንፈልግ ዜጎች ሞልተናል!

 በዶክተር አብይ አህመድ እና በግብረ አበሮቹ መሪነት እየተነቃቃ ያለው የርቅ እና የሆደሰፊነት ባህል አስደናቂ ነው። በታሪክ ብርቅ ከሆኑ ክስተቶች አንዱን ያስታውሰኛል።

በየጁ የምስፍና ዘመን ደጃዝማች ውቤ የተባሉ መስፍን የራስ አሊን መንግስት ለመቀማት ፈለጉ። በግብጡ ጎረምሳ አቡነ ሰላማ አይዞህ ባይነት በራስ አሊ ላይ ዘመቱ። ደብረታቦር ላይ ቅልጥ ያለ ጦርነት ተደርጎ ውቤ እና አቡነ ሰላማ ተሸንፈው ተማረኩ። በጊዜው ልማድ የተማረከ ሰው ህይወቱን ያጣል። በድል ነሺው እንዲኖር ከተፈቀደለት እንኳ እጁን ይቆረጣል፤ ወይም አይኑ በወስፌ ይፈርጣል።

በቅንነት ተገፋፍተው ይሁን ትርፍና ኪሳራውን አስልተው አይታወቅም-ራስ አሊ ግን ይህን ከማድረግ ታቀቡ። ምርኮኞችን ምሳ ጋብዘው በምህረት ወደ ጥንቱ ሹመታቸው መለሷቸው። ውቤ በዚህ ተደንቀው “ሲቻለው ማሪ፡ አሊና ፈጣሪ” ብለው በበገና ዘፈኑ። የራስ አሊን ሌጋሲ ያስቀጣላችሁልን ያዝልቅላችሁ በማለት ወደ ቀጣዩ አንቀጽ ልዝለቅ።

አንዳርጋቸው ፅጌ እና ጠ/ሚ ዓቢይ አህመድ (ፎቶ፤ ማኅበራዊ ሚዲያ)

አንዳንዶቻችን በለውጡ ጅማሬ መፈንደቅ ሲገባን ቢደብረን አትፍረዱብን። ህልውናችን ማንነታችን የተመሰረተው በግጭት ላይ ነው። ግጭቱ ሲፈታ መግቢያ እናጣለን። ያጅሬ ታሪክ ደርሶብን ነው። ከለታት አንድ ቀን፤አጅሬ ምኒሽሩን አንግቦ በቅረርቶው መንደር እያናወጠ እልም ያለው ዱር ውስጥ ይገባል። ከዚያ በዱሩ ውስጥ ሞፈር የሚቆርጥ ገበሬ ያገኝና እየተጀነነ” አዋ! እንዲያው እዚህ ግድም ያንበሳ ዱካ አይተሃል?” ይለዋል።

ገበሬው ዘና ብሎ “ዱካውን አይደለም። ራሱ አንበሳውን አሳይሃለሁ” ብሎ መለሰለት። አዳኝ መሳዩ ያልጠበቀው መልስ ስላገኘ ደነገጠ። “ለጊዜው ዱካውን እንጂ አንበሳውን ለማደን አልመጣሁም” ብሎ ላሽ አለ። አጅሬ የፈለገው “አያ እገሌ አንበሳ ሊያድን ጫካ ገብቱዋል” የሚለውን ወሬ እንጂ ጀብዱን አይደለም። አንዳንዴ ዱካውን እንጂ አንበሳውን አንፈልገውም። ድል የሚያሳድድ ሁሉ ድል የመሸከም ወኔ አለው ማለት አይቻልም። የነፃነት ታጋይ መባልን እንጂ ነፃነትን የማንፈልግ ዜጎች ሞልተናል። ተረዱን ለማለት ነው።

“ብየ ነበር” ማለት አገራዊ ልማድ ስለሆነ እኔም የሚከተለውን ብየ ነበር በማለት ልሰናበት።

“ተበዳይ መናፍስት፡ ታፍነው የኖሩ
ወደ አርነት መድረክ፡ በድንገት ሲጠሩ
ያለ ጠባቂ በር፡ ተከፍቶ ሳል በሩ
የገቡ አይመስላቸው፡ ቅጥሩን ካልሰበሩ”

(ስብስብ ግጥሞች)

ምንጭ፦ Bewketu Seyoum


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Filed Under: Opinions Tagged With: abiy, andargachew, freedom, Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    May 31, 2018 09:43 pm at 9:43 pm

    ውነት ዶ/ር ዓብይ ይህን ወንበዴ ኣነጋገሩት?? ስህተት ነው!

    Reply
  2. Ezira says

    May 31, 2018 11:06 pm at 11:06 pm

    የፅሁፉ ይዘት ተወሳሰበብኝ። ሁለት ሶስት ጊዜም ደጋግሜ ለማንበብም ሞከርኩ። ይሁንና የገባኝ መሠለኝና ግን ደግሞ እንዳልገባኝ ተረዳሁ። እንዳልገባኝ ስረዳ ”አላዋቂ ሳሚ” እንዳልሆን ብዬ አስተያየቴን በበቂ ሁኔታ ለመገለጥ ወይም ለማስፈር ታቀበኩ። ከይቅርታ ጋር !

    Reply
    • አለም says

      June 1, 2018 02:18 am at 2:18 am

      ውድ ዕዝራ፣
      የተወሳሰበብህ የአንዳርጌ ከሆነ፣ ቢገባህም ምንም አይጠቅምምና ተወው።
      የጎልጉል ኤዲተር ከሆነ፣ የአሳብ እስረኞች ከመሆናችን የተነሳ አንዳንዶቻችን
      በሩ ተበርግዶ ተከፍቶም መውጣት ተዘንግቶናል ነው የሚለን።
      የጸሐፊው ታሪክ ማጣቀስና በሳልነት አንዳርጌን አበሳጭቶታል።
      ምክንያቱም፣ እርሱም ማጣመምና ማሾፉን ቢተወው
      ጥሩ ጸሐፊ ነበር። እንደ ወንጀለኛው መለስ ዜናዊ
      የሚተካከለውን ወይም የሚበልጠውን መቀበልና መታገስ ያቅተዋል።

      Reply
  3. Ayalew Shebeshi says

    June 1, 2018 05:57 am at 5:57 am

    ዱካውን ማደን!
    በጣም አስደሳች ዕርዕስ ነው ዱካ or ኮቴ ማለት ምልክት or ምስል or sign ማለት ስለሆነ it is very interesting and timely.
    ነው።
    Also I notice it is Irony kind of expression.

    Thank you

    Reply
  4. ሀይሉ says

    June 1, 2018 10:44 am at 10:44 am

    ሌሎቹስ እሺ በሩ ተበርግዶም መውጣት ተሳናቸው ወይም ጠፋቸው ተባለ…
    አንተስ ይችን ትንሽዬ መልዕክት በቀላሉ በአንድ አረፍተ ነገር መግለፅ የጠፋህ አልመሰልክም?
    የግድ ነገሩን ሁሉ ካላወሳሰብነው አዋቂ አዋቂ አትሸትም ያለህ ማን ነው…

    Reply
  5. እዝራ says

    June 2, 2018 01:22 am at 1:22 am

    አለም እና አያሌው አመሠግናለሁ ላደረጋችሁት ማብራሪያ።

    Reply
  6. Ayalew Shebeshi says

    June 2, 2018 07:42 am at 7:42 am

    ሰላም ወንድም ሀይሉ አንተስ ያሉት ማንን ነው የፅሁፉን አበርካች ወይስ አኔን?
    thank you
    Ayalew

    http://www.estb.org/
    http://www.itts-eth.com/
    http://www.gampa.org.nz/

    visit these site for more detail if it is for me

    Reply
    • ሀይሉ says

      June 2, 2018 09:04 am at 9:04 am

      የዋናውን ፅሁፉ ባለቤት… በውቀቱን

      Reply
  7. Mulugeta Andargie says

    June 5, 2018 01:56 am at 1:56 am

    ኢህኣድግ! ኢህኣድግ!ስማኝ እንጂ፤ ኢህኣድግ!
    ምነው ጃል? ወንበዴ ታስተናግድ?
    ጥርግርግ ነበር እንጂ፤ ጥርግርግ!
    እንደ ፋሽስቱ ደርግ!
    ብለህ ብለህ ወንበዴ ማስተናገድ?
    እስኪንበረከክ በውድ!
    ፊውዳል ሁሉ ሲፏድድ
    መሬታችንን ለመቀማት፤ ብሎም ሊጥልብን ቀላድ!
    ምነው ኢህኣድግ? እኛን ኣሰደብከን፤ ዘመድ!
    ዳሩ ወንብዶ ለኖረ ፊውዳል
    ምሱ ሆኖ እስር፤ ይህ ጠብደል
    ይሁና! ትንሽ ቀምሷል፤ የህዝብ ጠበል!!

    Reply
  8. a says

    June 5, 2018 06:22 am at 6:22 am

    Thank you so much wendim Hailu.
    Let all (US-Ethiopians) stop blaming the past and do FORGIVE and FORGET approach to make peaceful transition from current Ethiopian Administration system to new, equal, modernized and based or supported by Skilled knowledgable HR + Info/data + HighTech that specially create job for our young Ethiopian to have them at least bread. I am sure if we concentrate or focus on peaceful transition, bloodless power transfer from EPRDF to Ethiopian people then we will achieve and bring fast radical changes to both political and economical situations that will serves free and fair go to all Ethiopians. Let us do it our brothers & sisters

    Reply
  9. Ayalew Shebeshi says

    June 14, 2018 03:59 am at 3:59 am

    Thank you so much wendim Hailu.
    Let all (US-Ethiopians) stop blaming the past and do FORGIVE and FORGET approach to make peaceful transition from current Ethiopian Administration system to new, equal, modernized and based or supported by Skilled knowledgable HR + Info/data + HighTech that specially create job for our young Ethiopian to have them at least bread. I am sure if we concentrate or focus on peaceful transition, bloodless power transfer from EPRDF to Ethiopian people then we will achieve and bring fast radical changes to both political and economical situations that will serves free and fair go to all Ethiopians. Let us do it our brothers & sisters

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule