“የነፃነት ታጋይ” መባልን እንጂ ነፃነትን የማንፈልግ ዜጎች ሞልተናል! በዶክተር አብይ አህመድ እና በግብረ አበሮቹ መሪነት እየተነቃቃ ያለው የርቅ እና የሆደሰፊነት ባህል አስደናቂ ነው። በታሪክ ብርቅ ከሆኑ ክስተቶች አንዱን ያስታውሰኛል። በየጁ የምስፍና ዘመን ደጃዝማች ውቤ የተባሉ መስፍን የራስ አሊን መንግስት ለመቀማት ፈለጉ። በግብጡ ጎረምሳ አቡነ ሰላማ አይዞህ ባይነት በራስ አሊ ላይ ዘመቱ። ደብረታቦር ላይ ቅልጥ ያለ ጦርነት ተደርጎ ውቤ እና አቡነ ሰላማ ተሸንፈው ተማረኩ። በጊዜው ልማድ የተማረከ ሰው ህይወቱን ያጣል። በድል ነሺው እንዲኖር ከተፈቀደለት እንኳ እጁን ይቆረጣል፤ ወይም አይኑ በወስፌ ይፈርጣል። በቅንነት ተገፋፍተው ይሁን ትርፍና ኪሳራውን አስልተው አይታወቅም-ራስ አሊ ግን ይህን ከማድረግ ታቀቡ። ምርኮኞችን ምሳ ጋብዘው በምህረት ወደ ጥንቱ ሹመታቸው … [Read more...] about ዱካውን ማደን!