የወልቃይት መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች እና የዋልድባ መነኮሳትን ጨምሮ ከመቶ በላይ ከእስር ቤት የተለቀቁ የዴሞክራሲና የፍትህ ተቆርቋሪ ታጋዮች በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ግንቦት 2 ቀን 2010 ዓ.ም በተደረገላቸው የክብር ራት ግብዣ ላይ የተገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለታዳሚው ያደረገውን ንግግር ከተመስገን ባገኘነው ፈቃድ መሠረት ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ አንባቢያን እንደወረደ በሚከተለው መንገድ አቅርበነዋል። በዕለቱም ለህሊና እስረኞች የተለያየ ስጦታም እንደተበረከተ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። እዚህ የተሰበሰባችሁ ታላላቆቼም፣ ታናናሾቼም በመጀመሪያ እንኳን ለዚህ ዕለት አበቃችሁ፤ አበቃን። በተለይም ባለፉት ሁለት አስርታት የወልቃይትን ሕዝብ የማንነት፣ የፍትሕ፣ የዴሞክራሲ እና የፖለቲካ ጥያቄ አደባባይ እንዲወጣ በተወለዳችሁበት አፈር ላይ ተተክላችሁ ለከፈላችሁት ውድ ዋጋ ጥልቅ … [Read more...] about ወልቃይት እንደ ካሽሚር