የለውጥ ውርጃ፣ የዘመናዊነት መጨናገፍ፣ የህዝባዊ ኃይል (ድምጽ) ተጽኖ ፈጣሪነት መኮላሸት፣…ድግግሞሻዊ የታሪክ አዙሪት አምሳያ የሆነችው ኢትዮጵያ፤ በተከታታይ ትውልዶች የደም ጎርፍ እየተንሳፈፈች እዚህ ደርሳለች። የአገር ግንባታ ሲሚንቶ ውሉ አልይዝ ብሎ ንቃቃት በዝቶበት የታሪክ ፈተናዋን መሻገር የተሳናት ኢትዮጵያ፤ በውስጣዊ ቅራኔ እንደተናጠች፣ ቅራኔዎቹ በተከታታይ ትውልዶች የደም ጎርፍ ከቶም እየተባባሱ የማህበራዊ ትስስሮሽ ነባር ህሊናዎች እየተናጉ፣ ዘውጋዊ መስመሮች በስታሊናዊ “ዕይታ” የልዩነት መስመሮች እየጎሉ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶች እየሻከሩ፣ ደም መቃባቱ እየበዛ በመሄዱ አገሪቱ ወደመፍረስ ጠርዝ በመገፋት ሂደት ላይ ትገኛለች። ከየትኛውም ጊዜ በከፋ መልኩ የርስ በርስ መጠራጠርና አለመተማመን ከፖለቲካ አደባባዩ ተሻግሮ በየግለሰቡ ጓዳ ገብቷል። በደብተራ ፖለቲካ ስትታመስ … [Read more...] about የታሪክ ፈተናችን እና ያሬዳዊ ትዝታ፤ ከክላሽ እስከ ብዕር!
Opinions
የኔ ሃሳብ
በማንነት ማፈናቀልን እንዴት መቀነስ ይቻላል?
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ‘የማንነት’ እና ‘የብሔር’ ፖለቲካ ወይም ጥያቄ ተምታተዋል። ብዙ ግዜ ሁሉም ነገር ‘የብሔር ጥያቄ’ ነው፤ መልሱም የሚገኘው ‘በብሔርተኝነት’ ነው የሚባለው ጉዳይ ከማንነት ጋር የተያያዘውን ጥያቄ ያድበሰብሰዋል። እንዲያውም አንዳንዴ ብሔርተኝነት ችግሩን ሊያባብሰው ይችላል። የማንነት ወይም የብሔር ትርጉሙም እንዲሁ የተምታታ ነው። ምክንያቱም ማንነትም ይሁን ብሔር በተለምዶ የሚበየነው በቋንቋ ላይ ተመሥርቶ ነው። ስለዚህም በተምታታ ትርጉም ላይ የተመሠረተ ብሔርተኝነትም ለተሳሳተ ጥያቄ የተሳሳተ መልስ ለመስጠት ይዳርጋል። ማንነት በቋንቋ ሊመሠረት ይችላል፤ ነገር ግን አንድ ቋንቋ እየተናገሩ የተለያየ ማንነት ያላቸው ግለሰቦች ወይም ሕዝቦች አሉ። ማንነት በፆታ ብቻ ሊወሰን ይችላል። ወይም ደግሞ በፆታዊ ግንኙነት ምርጫ ሊወሰን ይችላል። በመልክ ወይም በቆዳ ቀለም። … [Read more...] about በማንነት ማፈናቀልን እንዴት መቀነስ ይቻላል?
The First Peaceful Coup d’état Led by Team Lemma
In September 2016, my article entitled “A glimpse into the plausible alternative futures of Ethiopia”was posted on some Ethiopian websites. By employing one of the tools I use as I facilitate strategic planning sessions- Scenario Planning, I showed the four alternative futures of Ethiopia (see the attached pic) and pleaded both the ruling party and oppositions to sit down and negotiate to avoid bloodshed and chaos. When I wrote this futuristic commentary, both sides were seemingly strong with … [Read more...] about The First Peaceful Coup d’état Led by Team Lemma
ህወሓት፤ “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “ቆሞ ሙት”
እንደ ህወሓት ያለ አስገራሚ የፖለቲካ ቡድን ያለ አይመስለኝም። በጣም ገራሚ ነው። ከአመታት በፊት ያስቀመጥከው ቦታ ቁጭ ብሎ ይጠብቅሃል። በራሱ ምንም ዓይነት ለውጥ እንዲመጣ አይሻም። ከራሱ ባለፈ በሌሎች ዘንድ ምንም ዓይነት ለውጥና መሻሻል እንዲኖር አይፈቅድም። ከሁለት አመት በፊት ህወሓት “ቆሞ-ቀር” እንደሆነ የሚገልፅ ፅሁፍ አውጥቼ ነበር። ዛሬም ቢሆን ከነበረበት ቦታ ንቅንቅ አላለም። ህወሓት ፀረ-ለውጥ ድርጅት ከመሆኑ በተጨማሪ ሥር የሰደደ የአመራር ችግር አለበት። በመሆኑም ህወሓት ራሱን ለለውጥ ማንቀሳቀስ ሆነ መምራት አይችልም። በተለይ የመለስ ዜናዊ ህልፈትን ተከትሎ ህወሓት “በቁሙ መሞት” ጀምሯል። ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት አባይ ወልዱ ናቸው። ሰውዬው እንደ መለስ ዜናዊ ሸርና አሻጥር መጎንጎን አልቻሉበትም። በመሆኑም የመለስ ዜናዊ የነፍስ አባት … [Read more...] about ህወሓት፤ “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “ቆሞ ሙት”
ጉደኛው መሪያችን
ዶ/ር አብይ አህመድን ምን እንላቸዋለን? ከአሁን በፊት መሪዎቻችንን ለመግለፅ የተጠቀምንባቸውን ቃላት ሁሉ የሚያልፉ ሆኑብኝ። ጉደኛ የሚለውን ቃል የመረጥኩት፥ ያልተለመደና ያልታየ ነገርን ስለሚገልፅ ነው። በሌሎች ስንቀና የኛም ተራ ደርሶ ይሆንን? ደቡብ አፍሪካ ማንዴላ ነበራት፤ ሕንድ ማህተመ ጋንዲ ነበራት፤ አሜሪካ ጆርጅ ዋሽንግተን ነበራት። ኢትዮጵያ ዶ/ር አብይ ደረሰውላት ይሆን? ፋታ እንስጣቸው እያልን ስናወራ፤ እርሳቸው በድርጊታቸው አንዱን ሳናጣጥም ሌላ እየጨመሩ በመልካምነት ፋታ አሳጡን። ቀድመው ያሞገሱትን ማማት ይቸግራል ብለን፤ ተስፋን በስጋት ሰንቀን ዳር ቆመን በጥርጣሬ የምናይ ሁሉ ጉድ ፈላብን። ዛሬ ዛሬ ተስፋ ስጋትን እያሸነፈ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ለዶ/ር አብይ ድጋፍ እየጎረፈ ነው። ትላንት እንዳንጨራረስ እየፈራን ከዚህ አጣብቂኝ ማን ያወጣናል ስንል ነበር። … [Read more...] about ጉደኛው መሪያችን
አምባገነናዊነትን እያስታመሙ መቅበርም ይቻላል!
የአንባገነናዊ ሥርዓት ሞት ሁለት መልክ ያለው ነው። አንደኛው ከሱ የፈረጠመ ጡንቻ ባለው ወይም በሕዝባዊ አመጽ ድባቅ ተመቶ በሱ መቃብር ሌላ ጉልበተኛ ወይም ሕዝባዊ መንግሥት የሚሾምበት ሁኔታ ሲፈጠር ነው። ሁለተኛው ሞት ደግሞ እያዋዛ እና ረዥም ጊዜ የሚወስድ በረዥም ጣርና የስቃይ ጉዞ ውስጥ የሚመጣ ሞት ነው። በሰው ብንወስደው የመጀመሪያው በድንገተኛ አደጋ ወይም በቀናቶች ህመም የሚሞት ሰው ሲሆን ሁለተኛው ሞት ደግሞ እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሉ አንድ በአንድ እየከዳውና ከጥቅም ውጭ እየሆነ በስቃ ውስጥ ለተራዘመ ጊዜ ወይም ለአመታት ቆይቶ የሚሞት ሰው ነው። የአንድን አንባገነናዊ ሥርዓት የሞት ፍጥነት የሚለካው ለሥርዓቱ መሞት ምክንያት በሆነው ገፊ ኃይል መጠንና ፍጥነት ነው። አዝጋሚና ደክም ያለ ግፊት ሲሆን ሥርዓቱን መግደሉ ባይቀርም ሞቱን አዝጋሚ ያደርገዋል። በተቃራኒው ግፊቱ … [Read more...] about አምባገነናዊነትን እያስታመሙ መቅበርም ይቻላል!
አዮዲን አቅርቦት እጦት በአማራ ህጻናት ላይ
የአዮዲን እጥረት ችግር ምንድን ነው? አዮዲን በተፈጥሮ በውሃና በአፈር ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ነው። አዮዲን በባሕር ውስጥ በብዛት የሚገኝ ንጥረ ነገር ሲሆን በመሬት እና በንጹህ ውሃ ላይ ያለው ስርጭት ግን ከቦታ ቦታ ይለያያል። በጊዜ ብዛት በአፈር ውስጥ ያሉት የተፈጥሮ ንጥረ ነገሮች መመናመን የአዮዲንንም መጠን በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰው በመሆኑ በርካታ የኢትዮጵያ መሬት በተለይም ተራራማው የሆነው የዐማራ መኖሪያ ቦታዎች የተፈጥሮ አዮዲኑ ተመናምኗል። ስለዚህም በአለም በሙሉ እንደሚደረገው ለህዝብ በሚቀርበው ጨው ላይ አዮዲን መጨመር የተለመደ ነው። በቂ አዮዲን ያላገኙ ሰዎች የታይሮይድ ሆርሞን እጥረት (hypothyroidism) ያጋጥማቸዋል ውጤቱም የታይሮይድ ዕጢ እብጠት (እንቅርት) ይሆናል። ይህም በህጻናት ላይ ሲደርስ እድገትን ያቀጭጫል፤ የአእምሮ እድገትን በከፍተኛ ደረጃ … [Read more...] about አዮዲን አቅርቦት እጦት በአማራ ህጻናት ላይ
ግልጽ ደብዳቤ ለጠ/ሚ/ር ዓቢይ
ክቡር ሆይ ግንቦት 28 ቀን 2010 አም የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሜቴ በቁልፍ የአኮኖሚ ተግባር የተሰማሩና እስካሁን በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ አገልግሎት ሰጪና አምራች ድርጅቶች በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ለግል ባለሀብቶች እንዲሸጡ መወሰኑን ተረድቻለሁ፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የባቡር አገልግሎት ለሽያጭ እንዲቀርቡ መወሰኑ ከፍተኛ ሀዘንና ድንጋጤ ፈጥሮብኛል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከሁለት ወራት በፊት የኢህአዴግ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተመረጡ በኋላ በሚያራምዱት የአንድነት፣ የፍቅር፣ የልማት፣ የዴሞክራሲና የህግ የበላይነት ኢትዮጵያዊ ራእይ በአገራችን በኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት ታይቶ የማያውቅ የሰላም፣ የፍቅርና የተስፋ መንፈስ ቀስቅሰዋል፡፡ አንዳንዶቻችን ኢህአዴግ እንደ ድርጅትና እንደ መንግስት ባለፉት 27 አመታት በህዝብና … [Read more...] about ግልጽ ደብዳቤ ለጠ/ሚ/ር ዓቢይ
ከዚህ ደርሰናል፣ ቀጥሎስ?
የአገራችንን ሕዝብ ከሚያስከብሩት ባህሪያት አንዱ የሚያስደንቅ፣ አንዳንዴም እልህ የሚያጨርስ እርጋታው ነው። ይህንንም ገፀ-ባህሪ በዘፈኖቹ፣ ውብና ድንቅ በሆኑ ተረቶቹና አባባሎቹ እየቋጠረ ለትውልድ ሲያስተላልፍ ቆይቷል። ዶክተር አብይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ ባደረጓቸው ንግግሮችና በወሰዷችው እርምጃዎች የተማረከ፣ በርካታ የአገራችን ሕዝብ፣ ከላይ የተጠቀሰውን ዓይነት እርጋታ በተላበሰ መልኩ እስቲ እንያቸው የሚል ወደ ድጋፍ ያዘመመ አቋም ይዞ ሰንብቷል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ … [Read more...] about ከዚህ ደርሰናል፣ ቀጥሎስ?
LETTER FROM OBANG AND THE SMNE TO THE ETHIOPIAN PEOPLE:
Dear Fellow Ethiopian Brothers and Sisters, Ethiopians have new reason for hope. Over the last sixty days, we have witnessed many encouraging developments that have stirred new depths of hope within us. We should be thankful; yet, the road ahead is long and filled with challenges. Much will be required from all of us if we are to see genuine freedom, justice, reconciliation and healing become the pillars of a revived Ethiopian society. Hope alone, without responsible action on the part of all … [Read more...] about LETTER FROM OBANG AND THE SMNE TO THE ETHIOPIAN PEOPLE:










