የአዮዲን እጥረት ችግር ምንድን ነው?
አዮዲን በተፈጥሮ በውሃና በአፈር ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ነው። አዮዲን በባሕር ውስጥ በብዛት የሚገኝ ንጥረ ነገር ሲሆን በመሬት እና በንጹህ ውሃ ላይ ያለው ስርጭት ግን ከቦታ ቦታ ይለያያል። በጊዜ ብዛት በአፈር ውስጥ ያሉት የተፈጥሮ ንጥረ ነገሮች መመናመን የአዮዲንንም መጠን በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰው በመሆኑ በርካታ የኢትዮጵያ መሬት በተለይም ተራራማው የሆነው የዐማራ መኖሪያ ቦታዎች የተፈጥሮ አዮዲኑ ተመናምኗል።
ስለዚህም በአለም በሙሉ እንደሚደረገው ለህዝብ በሚቀርበው ጨው ላይ አዮዲን መጨመር የተለመደ ነው። በቂ አዮዲን ያላገኙ ሰዎች የታይሮይድ ሆርሞን እጥረት (hypothyroidism) ያጋጥማቸዋል ውጤቱም የታይሮይድ ዕጢ እብጠት (እንቅርት) ይሆናል። ይህም በህጻናት ላይ ሲደርስ እድገትን ያቀጭጫል፤ የአእምሮ እድገትን በከፍተኛ ደረጃ ይጎዳል።
የአዮዲን እጥረት በዓለም አቀፍ ደረጃ የአእምሮ ዝግመት እና የማይመለስ ከፍተኛ የአንጎል ጉዳት ከሚያደርሱት ዋነኛው መንስኤ ነው። የአዮዲን እጥረት ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሰው ነፍሰጡር እናቶች በቂ አዮዲን ሳያገኙ ሲቀሩና ህጻናት ከተወለዱም በኋላ በጨቅላ እድሜያቸው ወቅት ነው።
የእናቶች አዮዲን እጥረት የፅንስ መጨንገፍና ሌሎች የእርግዝና ችግሮች ለምሳሌ ያለጊዜው መወለድ እና መሃንነት የመሳሰሉትን ሊያስከትል ይችላል። የአዮዲን እጥረት ለልጆች የመማርና የማሰብ ችሎታ (IQ) በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ዋነኛ መንስኤ ነው።በኢትዮጵያ በተለይም የ“አማራ ክልል” በተባለው አካባቢ እጅግ በጣም በርካታ ህጻናት በወቅቱ በቂ አዮዲን ባለማግኘታቸውና ለአዮዲን እጥረት በመጋለጣቸው ምክንያት እድገታቸው ቀጭጯል ለአእምሮ ዝግመትም ተዳርገዋል። (ሙሉውን ዘገባ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
ፎቶው ከዚህ በፊት የተፈናቀሉትን እንጂ ተጎጂዎችን የሚመለክት አይደለም
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
Leave a Reply