• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ግልጽ ደብዳቤ ለጠ/ሚ/ር ዓቢይ

June 6, 2018 12:35 am by Editor Leave a Comment

ክቡር ሆይ

ግንቦት 28 ቀን 2010 አም የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሜቴ በቁልፍ የአኮኖሚ ተግባር የተሰማሩና እስካሁን በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ አገልግሎት ሰጪና አምራች ድርጅቶች በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ለግል ባለሀብቶች እንዲሸጡ መወሰኑን ተረድቻለሁ፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የባቡር አገልግሎት ለሽያጭ እንዲቀርቡ መወሰኑ ከፍተኛ ሀዘንና ድንጋጤ ፈጥሮብኛል፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣

ከሁለት ወራት በፊት የኢህአዴግ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተመረጡ በኋላ በሚያራምዱት የአንድነት፣ የፍቅር፣ የልማት፣ የዴሞክራሲና የህግ የበላይነት ኢትዮጵያዊ ራእይ በአገራችን በኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት ታይቶ የማያውቅ የሰላም፣ የፍቅርና የተስፋ መንፈስ ቀስቅሰዋል፡፡ አንዳንዶቻችን ኢህአዴግ እንደ ድርጅትና እንደ መንግስት ባለፉት 27 አመታት በህዝብና በአገር ላይ የፈጸመው በደል ሳያግደን ከጎንዎ ተሰልፈናል፡፡ የሁን እንጂ፣ ይህ አሁን የተገለጠው የኢህአዴግ ውሳኔ የአገርንና የህዝብን ዘላቂ ጥቅም ከፍተኛ ጉዳት ላይ የሚጥል መሆኑን በአክብሮት ልገልጥልዎ እወዳለሁ፡፡

የህዝብ ንብረት የሆኑ አገልግሎት ሰጭና አምራች ድርጅቶችን ወደ ግል ንብረትነት ለማዛወር የተወሰነው የአገሪቱን ፈጣንና ተከታታይ እድገት ለማገዝ መሆኑ ተገልጧል፡፡ ይህ ምክንያት ለስኳር አምራች ድርጅቶችና ለኢትዮ ቴሌኮም ይሰራ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እና ባቡርን በሚመለከት ግን የሚያስከትለው ጥቅምን ሳይሆን ከፍተኛ ጉዳትን ነው፡፡

በ1938 አም የተቋቋመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአገልግሎቱ ብቃትና ጥራት በአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌለው፣ በአለም ዙሪያ ታዋቂነትን ያተረፈ ድርጅት፡፡ በአለም ዙሪያ ያሉ ትላልቅ የግልና የመንግስት አየር መንገዶች እየከሰሩ በሚዘጉበት ወቅት በአትራፊነት የዘለቀ ብሄራዊ ቅርስ ነው፡፡ በሙሉ ቀርቶ በከፈልም ቢሆን ለግል ባለንብረቶች የሚሸጥበት አንዳች አሳማኝ ምክንያት የለም፡፡ አላማው ይበልጥ እድገት ማስቻል ከሆነ የግል ባለሀብቶች ሌላ ተፎካካሪ አየር መንገድ አቋቁመው ገበያውን እንዲቀላቀሉ መምከር እንጂ ይህንን የመሰለ ሁለት ትውልድ መስዋእት ከፍሎ ያበለጸገውን አትራፊ ስመ-ጥር ተቋም ለግል ባለሀብቶች መሸጥ ታሪካዊ ስህተት ይሆናል፡፡

ባቡርን በሚመለከት የበርካታ አውሮፓ አገሮች ልምድ የሚያሳየው ባቡር ሙሉ ለሙሉ ወይም ከ80 በመቶ በላይ የአክስዮን ድርሻው በህዝብ ንብረትነት የተያዘ ነው፡፡ ከነዚህ መሀል ሆላንድ፣ ስዊድን፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ቤልጂግ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

በአንጻሩ በ1985 አም በስልጣን ላይ የነበረው የእንግሊዝ ወግ አጥባቂ መንግስት፣ በፖለቲካ ምክንያት፣ የህዝብ ንብረት የነበረውን የእንግሊዝ ባቡር ለግል ባለንብረቶች ከሸጠው በኋላ እስካሁን ራሱን መቻል አቅቶት በኪሳራ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በየአመቱ ከእንግሊዝ መንግስት በቢልዮን ዶላር የሚቆጠር ድጎማ ለግል ባለንብረቶቹ ይሰጣል፡፡ የባቡር አገልግሎት ጥራት ከአውሮፓ አገሮች ጋር ሲወዳደር የእንግሊዝ ከተጠቀሱት አገሮች ሁሉ ዝቅተኛ ነው፡፡ ባቡር ለመሳፈር የእንግሊዝ ህዝብ የሚከፍለው ዋጋ ግን ከአውሮፓ አገሮች ጋር ሲወዳደር እስከ 40 በመቶ ከፍ ያለ ነው፡፡ በነዚህና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ተቃዋሚው የእንግሊዝ ሰራተኞች ፓርቲ ባቡርን መልሼ እወርስና የህዝብ ንብረት አደርጋለሁ ሲል ለህዝብ ቃል ገብቷል፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣

ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅምና ለዘላቂው ህዝባዊ ጥቅም ሲባል፣ ጫናው ከየትም ይምጣ ከየት፣ እነዚህን የመሳሰሉ ብሄራዊ ተቋሞች ለሽያጭ ሊቀርቡ አይገባም፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

አበራ የማነ አብ፣ ብሩሴል፣ ቤልጅግ ግንቦት 29፣ 2010

aberayemaneab@gmail.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule