(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን) ዛሬ ላይ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች በስፋት አየተዘገበ ስላለው የኮሮና መድሀኒት ተገኘ የተባለው ዴክሳሜታሶን መድሀኒት አዲስ የተገኘ ሳይሆን ከዚህ በፊት እኛም ሀገር ላይ በስፋት ስንጠቀምበት የነበረ መድሀኒት ነዉ። ዴክሳሜታሶን (Dexamethasone) የሚባለው ስቴሮይድስ (Steroids) ከሚባለው ቤተሰብ የሚመደብ የመድኃኒት ዓይነት እ.ኤ.አ ከ1960 ጀምሮ ለተለያዩ በሽታዎች ጥቅም ላይ ሲዉል የቆየ ነው። ዛሬ ቢቢሲ ላይ የተዘገበዉ መድሀኒት የመተንፈስ ችግር እና በጽኑ የኮሮና ቫይረስ ሕመም ላይ ያሉ ሰዎችን እንጂ መጠነኛ (Mild Symptoms) ምልክት ላላቸው እንደማይጠቅም በጥናቱ ላይ አስፍረዋል። በተጨማሪ ስቴሮይድስ (Steroids) ' በከፍተኛ ጥንቃቄ' የሚሰጡ መድኃኒቶች ሲሆኑ በርካታ 'የጎንዮሽ ጉዳት' እንዳላቸው … [Read more...] about ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት
Slider
የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!?
እንደ መግቢያ ሰሞኑንን ከኮቪድ - 19 ጋር ተያይዞ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሓኖም አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ ይታወሳል። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ካወደመው፣ የዘር ፖለቲካን ከሚያራምደው ፍጹም ጽንፈኛና ዘረኛ፣ እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ ኢትዮጵያውያንን በዘራቸው፣ በፖለቲካ እምነታቸው ካኮላሸ፣ ከጨፈጨፈ፣ ቶርቸር ካደረገ፣ በጅምላ ሴቶች እንዲደፈሩና ከነነፍሳቸው ለአውሬ እንዲጣሉ ካደረገ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር/ትህነግ ቴድሮስ የተቀዳ አመራር እንደነበር አይዘነጋም። የተመረጠው በኃያላኑ ዓላማና መልካም ፈቃድ ነበር፤ ኃያላኑ አሁን ፍጥጫ በሚመስል ውዝግብ ውስጥ ይገኛሉ፤ የተመረጠበትን ዓላማ የፈጸመ ከሆነ መወገዱ የማይቀር ይሆናል፤ ካላለቀ ደግሞ ዕድሜ ማራዘሚያ ይሰጠዋል። የቴድሮስ የWHO ምርጫ ወቅቱ የዛሬ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር … [Read more...] about የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!?
በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው
በትግራይ የሚገኘውና 18 ሺሕ ገደማ ኤርትራውያን የሚኖሩበት ሕንፃፅ የስደተኞች መጠለያ ሊዘጋ መሆኑን ስደተኞች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። በመጠለያው የሚኖሩ በአስር ቀናት ሕንፃጽ መጠለያን እንዲለቁ በኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር ባለፈው ሐሙስ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ከሚገኙ ስድስት ኤርትራውያን ስደተኞች ከሚያስተናግዱ መጠለያ ጣብያዎች መካከል አንዱ የሆነው በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው ሕንፃፅ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ከሰባት ዓመት በፊት ተቋቁሞ 18 ሺህ ገደማ ኤርትራውያን ስደተኞች እያስተናገደ የሚገኝ ማእከል ነው። በስደተኞች መጠልያ ጣብያው ሕንፃፅ የሚኖሩ ኤርትራውያን እንደሚሉት ባለፈው ዕለተ ሐሙስ ነበር የሚኖሩበት መጠልያ እንደሚዘጋና በአስር ቀናት ውስጥ ቦታ እንዲቀይሩ የተነገራቸው። … [Read more...] about በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው
እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደ ስያሜው የኢትዮጵያዊያን ነው። ከአቶ ተፈራ ደግፌ 1956 ዓ.ም. እስከ አቶ በቃሉ ዘለቀ 2010 ዓ.ም. በትውልድ ቅብብሎሽ ዘር ሳይለይ፣ ጎሳ ሳይመርጥ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን ሆኖ የዘለቀ አንጋፋ ባንክ። አቶ ተፈራ ደግፌ መጋቢት 12 ቀን 1956 ዓ.ም. ባንኩን ከመረከባቸው በፊት፣ ባንኩ ለኢትዮጵያዊያንና ለአገራችን እምብዛም ግድ በማይሰጣቸው ለራሳቸው ጥቅምና የኢኮኖሚ ዕድገት በሚታትሩ የውጭ አገር ዜጎች ይመራ ነበር። ህንዳዊያን፣ አርመኖች፣ ግብፆችና አውሮፓዊያን አቶ ተፈራ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት ባንኩን የኢትዮጵያ መንግሥት ባንክ በሚል ስያሜ ያስተዳድሩ የነበሩ ናቸው። ይህን የተረዱት አፄ ኃይለ ሥላሴ ጣሊያን አገራችንን ከለቀቀ በኋላ ኢትዮጵያዊያን የባንክ፣ የኢንሹራንስና የሕግ ዕውቀቶችን እንዲያዳብሩ ወደ ተለያዩ የአውሮፓ … [Read more...] about እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል
የሚዲያው ዝምታ ለምን ይሆን? የኮሮና ቫይረስ በቻይና ከመከሰቱ በፊት በአሜሪካ በቫይረሱ ተጠቅተው የሞቱ መኖራቸው ተረጋገጠ። ይህንን ያረጋገጡት የአሜሪካ የበሽታ ቁጥጥር ማዕከል (CDC) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሮበርት ሬድፊልድ ናቸው። ዳይሬክተሩ እንዳሉት ይህ የታወቀው በኢንፍሉዌንዛ በሞቱ ሰዎች ላይ በድጋሚ በተደረገ ምርመራ ነው። በተለያዩ የሚዲያ ዘገባዎች በተደጋጋሚ ሲነገር እንደቆየው የኮሮና ቫይረስ የተጀመረው በቻይና ዉሃን ከተማ እንደሆነ ነበር። ለበሽታው መነሻም የተለያዩ መላምቶች ሲሰጡ ቆይተዋል። አንዱ መላምት ከእንስሳት ወደ ሰው ነው የተላለፈው የሚል ነው። ለዚህም እንደ ማስረጃነት የሚቀርበው ቻይናውያኑ የሚበሉት፣ “እርጥብ ገበያ” (wet market) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ከባህር የሚገኙ ማንኛውም የአሣ ዝርያ እስከ የሌሊት ወፍ፣ እባብ፣ ውሻ፣ ሸለምጥማጥ፣ … [Read more...] about ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል
ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ
በአሜሪካ የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክትል ሊቀ መንበር ተደርጎ የተሾመው የቀድሞው የህወሃት ካድሬና የበረከት ስምዖን ታማኝ ኤርሚያስ ለገሰ መሰናበቱ ተሰማ። እስክንድር ነጋን የጠቀሱ የጎልጉል እማኞች እንዳሉት ኤርሚያስ መባረሩን አያውቅም። በዚህ ሳቢያ 360 እንደ ስሙ ዘመቻውን ያዞራል ተብሎ ይጠበቃል። የእስክንድር ነጋን የአሜሪካ ጉዞ ተከትሎ በሰርግና ምላሽ የባለ አደራው ምክትል ሰብሳቢ የሆነው ኤርሚያስ ሹመቱን አስመልክቶ ስለ ቀጣዩ የትግል አቅጣጫ፣ የትግሉ ግብና አደረጃጀት እንዲሁም ኔትዎርክ ማብራሪያ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል። ተያዘውም ወደ ተፈለገው ዓላማ እንደሚደርሱ ምሎ ነበር። ለድርጅቱ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ ቅርብ የሆኑና ይህ ውይይት ሲደረግ የነበሩ ኤርሚያስ ለገሰ በቅርቡ ከሃላፊነት መነሳቱ ይነገረዋል "የእሱ መሰናበት ያለቀ ነው። መጀመሪያም ትክክል አልነበረም" … [Read more...] about ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ