አዲስ አበባን የሽብር ቀጠና ለማድረግ የአሸባሪው ህወሓት ቡድንን ዓላማ ለማሳካት ተንቀሳቅሰዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩ 284 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። 199 ሽጉጥ ከ2 ሺህ 453 ጥይት ጋር፣ 32 ክላሽንኮቭ ከ5 ሺህ ከሚልቅ ጥይት ጋር እንዲሁም 4 የጦር ሜዳ መነፅር ከተጠርጣሪዎቹ እጅ፣ ከስራ ቦታቸውና ከመኖሪያ ቤታቸው በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ ለኢቲቪ ተናግረዋል። ተጠርጣሪዎቹ ለአሸባሪው ህወሓት አገር የማፍረስ ተልዕኮ የፋይናንስ ምንጭ ሆኖ እንዲያገለግል ያከማቹት ከአንድ ኪሎ ተኩል በላይ የወርቅ እንዲሁም 37 ሺህ 294 ነጥብ 8 ግራም የብር ጌጣጌጥም መያዙን ምክትል ኮሚሽነሩ ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ ተጠርጣሪዎቹ ለሽብር ተግባር የሚጠቀሙባቸው የአዲስ አበባ … [Read more...] about በአዲስ አበባ ለትህነግ የሚሠሩ 284 የሽብር ተጠርጣሪዎች ተያዙ
Right Column
በርካታ ዓይነት እና መጠን ያለው የብረት ክምችት ተያዘ
በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 7 አስተዳደር በርካታ ዓይነት እና መጠን ያለው የብረት ክምችት በኢኮኖሚ አሻጥር ቁጥጥር ግብረ-ኃይል መያዙን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ። የኢኮኖሚ አሻጥርን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በተዋቀረው ግብረ-ኃይል ለግንባታ አገልግሎት ሊውሉ የሚገባቸው ፌሮ እና ብረታ ብረቶችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ነው የተገለጸው። ለጊዜው በገንዘብ ለመተመን ያልተቻለ ለረዥም ግዜ ሕገ-ወጥ በሆነ መልኩ የተከማቹ ፌሮ እና ብረታብረቶች በወቅቱ በገበያ ላይ ውለው ቢሆን ኖሮ አሁን ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ሚና ይኖራቸው ነበር ተብሏል። እንደነዚህ አይነት ተግባር ላይ የተሰማሩ አሻጥረኞች ላይ የሚደረገው ክትትል እና ቁጥጥር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የአቃቂ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት ሙሉጌታ ገልጸዋል። በተመሳሳይ በክፍለ ከተማው ወረዳ 2 … [Read more...] about በርካታ ዓይነት እና መጠን ያለው የብረት ክምችት ተያዘ
በሕገ-ወጡ ብረት ለገበያ እንዲቀርብ ተወሰነ፤ 400 ኩንታል ሲሚንቶና የቴሌ ኬብሎችን ሲያጓጉዙ የነበሩ ተያዙ
በተለያዩ ቦታዎች በሕገ-ወጦች አማካኝነት ተከማችቶ የተገኘ ብረት በሕጋዊ መንገድ ወደ ገበያ ገብቶ እንዲሸጥ እና ለመንግሥት ገቢ እንዲሆን መወሰኑን ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። በ13 የተለያዩ ቦታዎች በህገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘውና በዋጋ አረጋጊ ግብረ-ሀይል በቁጥጥር ስር የዋለው ከ1ሺ በላይ መኪና ብረት በህጋዊ የግብይት ስርዓቱ ውስጥ ገብቶ እንዲሸጥና ገቢው ለመንግስት እንዲገባ መወሰኑን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። በሌላ በኩል በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ሲሚንቶ እና የቴሌ ጥቅል ኬብል በመኪና ሲያጓጉዙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የክፍለ ከተማው የህዝብ ግንኙነት ቢሮ አስታውቋል። ተጠርጣሪዎቹ ትናንት ምሽት በወረዳው አደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ 400 ኩንታል ሲሚንቶ … [Read more...] about በሕገ-ወጡ ብረት ለገበያ እንዲቀርብ ተወሰነ፤ 400 ኩንታል ሲሚንቶና የቴሌ ኬብሎችን ሲያጓጉዙ የነበሩ ተያዙ
ወደ ኮምቦልቻ ሊገባ የነበረ 49 ሺህ 300 የአሜሪካ ዶላር ተያዘ
በኮምቦልቻ ከተማ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኬላ ኮድ3 የሰሌዳ ቁጥር 89654 የሆነ መኪና መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ ወደ ኮምቦልቻ ሊገባ ሲል በብሔራዊ ደኅንነት፣ በፓሊስ እና ኬላ በሚጠብቁ ወጣቶች ትብብር በቁጥጥር ሥር መዋሉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ገልጿል። የጽ/ቤቱ የታክቲክና ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር አሊ ለአሚኮ እንደገለፁት ተጠርጣሪው ከምሽቱ 2:40 ሰዓት ላይ አሽከርካሪ በኬላው ላይ በነበረ ፍተሻ ከነዶላሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ወጣቶች በኬላ ፍተሻ እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ መሆኑን የገለጹት ኮማንደር አሊ ወጣቶች እየሠሩ ያሉትን አካባቢን በንቃት የመከታተል ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። በኬላ ጥበቃ ላይ አሚኮ ያነጋገረው በጎ ፈቃደኛ ወጣት ሐሰን እንድሪስ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ለመቅበር በግንባር … [Read more...] about ወደ ኮምቦልቻ ሊገባ የነበረ 49 ሺህ 300 የአሜሪካ ዶላር ተያዘ
በባሌ ዞን የአሸባሪው ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ
በባሌ ዞን ሐረና ቡሉቅ ወረዳ ሦስት የአሸባሪው ሸኔ አባላት በኅብረተሰቡ ተሳትፎ እና በፀጥታ አካላት የተቀናጀ ሥራ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና በሕዝቡ ላይ በመተኮስ ጉዳት ለማድረስ በሞከሩ ሁለቱ ላይ ደግሞ እርምጃ መወሰዱን የባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። የአሸባሪው ሸኔ አባላት በተደጋጋሚ ወደ ዞኑ ለመግባት ሙከራ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዳይሬክተር ኮማንደር ጄይላን አሚን ተናግረዋል። በቁጥጥር ስር የዋሉት የሽብር ቡድኑ አባላት፣ “የኦሮሞን ሕዝብ ትክክለኛ ፍላጎት እንዳልተረዳን ያወቅነው ሕዝቡ በአንድነት ወጥቶ ቁጥጥር ስር ሲያውለን ነው” ብለዋል። “ሌሎች የተቀሩት ወጣቶችም ይህንኑ ሐቅ ሊረዱ ይገባል” ሲሉ መናገራቸውን ኦቢኤን ዘግቧል። የሐረና ቡሉቅ ወረዳ ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ የኦሮሞን ሕዝብ ለ27 ዓመታት ሲገድል፣ ሲያኮላሽ እና … [Read more...] about በባሌ ዞን የአሸባሪው ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ
የ360 ሤራ “ተንታኞች” መከፋፈል – “ጅብ ደም ከታየበት በጅቦች ይበላል”
ቁጭ ብዬ ናሽናል ጂኦግራፊክ ስመለከት ጅቦች አየሁ። አንድ ጎረምሳ አንበሳ ይተናኮላሉ። አንበሳው እየገላመጠ መንጋጋውን እያጓራ ያሳያቸዋል። ራሱን ለመከላከል ብዙም ያልተጨነቀው አንበሳ እየተቆጣና እየተገላመጠ ሲራመድ ጅቦቹ የልብ ልብ ተሰማቸው። ጅቦች አንበሳን ሊበሉ ቋመጡ። በመካከሉ አንዱ ጅብ ዘልቆ ሲገባ አንበሳው ተወናጭፎ መቀመጫው አካባቢ ነከሰው። ይህኔ የተነከሰው ጅብ ጩኸቱን አምባረቀ። አንበሳው በጣም ተናዶ ጉልበቱን ማሳየት ሲጀምር ጅቦች አፈገፈጉ። ይህን ጊዜ የተነከሰውን ጅብ መቀመጫ የማየት ዕድል የገጠማቸው ጅቦች አንበሳውን ትተው “ወንድማቸውን” ያሳድዱ ጀመር። አባረው ያዙት። አንበሳው በነከሰው በኩል የሚፈሰውን ደም ተከትለው በደቦ በሉት። ጅብ ሌላው ጅብ ላይ ደም ካየ አይምርም። ደም ሲደማ ሆዱ እንደሚሞላ ስለሚያውቅ ማድማት ወይም በደማው በኩል ገብቶ … [Read more...] about የ360 ሤራ “ተንታኞች” መከፋፈል – “ጅብ ደም ከታየበት በጅቦች ይበላል”
መርካቶ አካባቢ ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ ከ10 ሺህ በላይ ገጀራ ተያዘ
ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ ከ10ሺ በላይ ገጀራ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ እንደሆነ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የመርካቶ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታወቀ፡፡ በትላንትናው እለት ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ከማህበረሰቡ የተሰጠውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ መርካቶ ውስጥ ጣና የገበያ ማዕከል ጎን በሚገኝ አድማስ ህንፃ ውስጥ፤ አዲሱን የጦር መሳሪያ ቁጥጥር አዋጅ በሚፃረር መልኩ ተከማችቶ የተገኘው ከ10ሺ በላይ ገጀራ በቁጥጥር ስር በማዋል ጠቅላላ ምርመራ እያካሄደበት እንደሆነ የመርካቶ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኢኒስፔክተር ብርሃኑ አለሙ ተናግረዋል፡፡ የጦር መሳሪያውን ክምችት በመጠቆም ረገድ የህብረተሰቡ ትብብር ከፍተኛ ነበር ያሉት ምክትል ኢኒስፔክተር ብርሃኑ የብሄራዊ ደህንነት ባለሙያዎችና የፖሊስ አባሎቻችንም ድርሻም የጎላ እንደነበር … [Read more...] about መርካቶ አካባቢ ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ ከ10 ሺህ በላይ ገጀራ ተያዘ
ኢትዮጵያ በትህነግ ላይ ለምትወስደው እርምጃ ልትደገፍ ይገባታል፤ የሩሲያ መንግሥት
የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት እና ክልሉ ወደ ሰላም ተመልሶ የተረጋጋ ሕይወት እንዲቀጥል ለማድረግ የወሰደውን እርምጃ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ እና በቀጠናው የሚገኙ ተቋማት እንዲደግፉ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል። የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሪቫ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ በዛሬው ዕለት በሰጡ መግለጫ፣ ሩሲያ ወዳጅ ሀገር በሆነችው ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወነ ስላለው ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለች ነው ብለዋል። ኢትዮጵያውያን የውስጥ ችግሮቻቸውን ለመፍታት በአፍሪካውያን ወንድሞቻቸው ድጋፍ የራሳቸውን ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ የሩሲያ እምነት መሆኑንም ገልጸዋል። አሸባሪው ህወሓት የኢትዮ-ጂቡቲ ኮሪደርን ለመያዝ ባደረገው ሙከራ የሰብአዊ ቀውስን ማባባሱን እና የስደተኞች እና የሀገር ውስጥ … [Read more...] about ኢትዮጵያ በትህነግ ላይ ለምትወስደው እርምጃ ልትደገፍ ይገባታል፤ የሩሲያ መንግሥት
ለትህነግና ሸኔ ገንዘብ ሲያስተላልፉና ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ሲፈጽሙ የነበሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ለአሸባሪዎቹ የህወሓትና ሸኔ ቡድኖች በተለያዩ ህገወጥ መንገዶች ገንዘብ ሲያሰባስቡና ሲያስተላልፉ የነበሩ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ አሻጥር በመፈጸም ህብረተሰቡን ለአመጽ ለማነሳሳት ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩ በአዲስ አበባ 51 እንዲሁም በአፋር ክልል 6 በድምሩ 57 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡ ግብረሃይሉ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤አዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች ተሰማርተው ከአሸባሪዎቹ ህወህትና ሸኔ ቡድን ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት በመፍጠር በህገወጥ መንገድ ገንዘብ ሲያሰባስቡና ሲያስተላልፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ ማስረጃዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ አንድ አንድ ተጠርጣሪዎች በህግ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በመሰማራት ለሸብርተኛው … [Read more...] about ለትህነግና ሸኔ ገንዘብ ሲያስተላልፉና ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ሲፈጽሙ የነበሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ
በክምር ድንጋይ የተሠራ ጀብድ
በክምር ድንጋይ አንድ የአማራ ጀግና 11 የአሸባሪው ትህነግ ታጣቂዎችን ደመሰሰ። የአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ታጣቂዎች በክምር ድንጋይ ከተማ ወደ አንድ ግለሰብ ቤት በመሄድ ለማጥቃትና ለመዝረፍ ተዘጋጁ። ታጣቂዎች ግለሰቡ ቤት ደረሱ። ይህንን ቀድሞ የተረዳው ግለሰብም በጥበብና በብልሃት የመጡትን የአሸባሪውን ቡድን ታጣቂዎች አዘናጋቸው። ሌላ ኃይል አብሯቸው እንደሌለ ወደ ውጪ ወጣ በማለት ካረጋገጠ በኋላ ወደ ጓዳው በመግባት ተቀባብሎ የነበረውን መሣሪያ ይዞ በመውጣት እርምጃ ወስዶባቸዋል። ሊያጠቁትና ሊዘርፉት እንደመጡ የተረዳው ይህ ግለሰብ ያለውን መሣሪያ በመጠቀም በቤቱ የተሰበሰቡትን 11 የአሸባሪውን ትህነግ ታጣቂዎች እንዳልሆኑ በማድረግ ጀግንነቱን አሳይቷል። አሁን ላይም ይህ ጀግና ቀሪ የአሸባሪውን ቡድን አባላትን እያሳደደ ይገኛል። ጠላትን አይቀጡ … [Read more...] about በክምር ድንጋይ የተሠራ ጀብድ