የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737-800 ማክስ አውሮፕላን የመከስከስ አደጋ በደረሰበት ስፍራ ለሚገነባው ሀውልትና ፓርክ የወጣውን ዓለም አቀፍ የንድፍ ውድድር የኢትዮጵያዊው አርክቴክት አለበል ደስታ ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ታውቋል። በምስራቅ ሸዋ ዞን ግምቢቹ ወረዳ ለሚሰራው ይሄው የመታሰቢያ ሀውልት እና ፓርክ በ4 ሄክታር መሬት ላይ ሊገነባ የታሰበ ሲሆን ቦታው የማስታወሻ፣ የአረንጓዴ ቦታና የውጪ መሰብሰቢያ ስፍራ ያካተተ ነው ተብሏል። የአርክቴክት አለበል ደስታ ድርጅት ውድድሩን በማሸነፉ የ10 ሺህ ዶላር ሽልማት ሲያገኝ ሁለተኛ የወጣው ባይቦን አማካሪ አርክቴክቶችና መሀንዲሶች ድርጅት 7ሺህ ዶላር እንዲሁም በረከት ተስፋዬ አማካሪ አርክቴክቶችና መሀንዲሶች ድርጅት ሶስተኛ በመውጣት የ5 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ሆነዋል። አርክቴክቱ ከዚህ ቀደምም … [Read more...] about የቦይንግ አዉሮፕላን በተከሰከሰበት ስፍራ ለተጎጂዎች መታሰቢያ ሊገነባ ነው