ሀብትና የገቢ ምንጫቸውን ለማስመዝገብ ፈቃደኛ ያልሆኑ 62 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ሰራተኞች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በኮሚሽኑ የፀረ-ሙስና ህግ ምክር፣ ትግበራና ልምድ ቅመራ ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ጋሻው እንደገለፁት ሀብትና የገቢ ምንጫቸውን ለማስመዝገብ ፈቃደኛ ያልሆኑት 16 የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የኒቨርሲቲና 46 የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ናቸው፡፡ ማንኛውም የመንግስት ተሿሚ፣ የህዝብ ተመራጭ እና የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርቶች እንዲሁም የህዝባዊ ድርጅት ሰራተኞች የቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ሀብትና የገቢ ምንጫቸውን ማስመዝገብ እንዳለባቸው ቢደነገግም ህጉን የሚተላለፉ በመኖራቸው ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ዳይሬክተሩ … [Read more...] about ሀብትና የገቢ ምንጫቸውን ያላስመዘገቡ በህግ ሊጠየቁ ነው
Right Column
ሕገ-ወጥ የዶላር መንዛሪዎች ተያዙ፤ ዳያስፖራው እንዳይተባበር ጥሪ ቀረበ
በሀገራችን ላይ የተለያዩ ሴራዎችን ሲያካሂድ የቆየው የአሸባሪው የህወሃት ጁንታ ቡድንና ተላላኪዎቹ ፊት ለፊት ከሚያካሂዱት ሀገር የማፍረስ ሴራ ጎን ለጎን በሀገሪቱ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት እንዲፈጠርና ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲማረር የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ መሆናቸው ተደርሶበታል። በዚህ መሰረት የሽብር ቡድኑ ስልጣን ላይ በነበረባቸው አመታት በዘረጋቸው ኔትዎርኮችና ቅጥረኞች አማካኝነት ከአዲስ አበባ ቶጎ ውጫሌን፣ ሞያሌን፣ መተማንና ሌሎች የመውጫ በሮችን በመጠቀም ኮንትሮባንድ ዝውውር ላይ በመሳተፍና ዶላርን በጥቁር ገበያ እየገዛ የዶላር እጥረት እንዲከሰት ከማድረግ ባሻገር በርካታ የጥፋት ተግባራትን ሲያካሄድ የቆየ መሆኑን ቀደም ሲል በህገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ ስድስት ድርጅቶች ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ስለመሆኑ ባስተላለፍነው መረጃ ተደራሽ … [Read more...] about ሕገ-ወጥ የዶላር መንዛሪዎች ተያዙ፤ ዳያስፖራው እንዳይተባበር ጥሪ ቀረበ
በአምቦ ከተማ ጥይቶችን በአምቡላንስ ሲያጓጉዙ የተገኙ ተያዙ
በአምቦ ከተማ 1 ሺህ 377 ተተኳሽ ጥይቶች በህገ ወጥ መንገድ በተሽከርካሪ ጭነው ሲያጓጉዙ የተገኙ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። ግለሰቦቹ ጥይቶቹን በመንግስት አምቡላንስ ተሽከርካሪ ጭነው ሲያጓጉዙ እንደተገኙ የከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሲሳይ ሂርጳ ገልጸዋል። ከከተማዋ ወጣ ብሎ በሚገኘው አዋሮ ቆራ አካባቢ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ትናንት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ ነው ግለሰቦቹን ከነጥይቶቹ መቆጣጠር የተቻለው ብለዋል። ኮማንደር ሲሳይ እንዳመለከቱት፤ ግለሰቦቹ ጥይቶቹን በሴቶች "ታይት" አልባሳት ጠቅልለው በማዳበሪያ ውስጥ መድሃኒት አስመስለው በመጫን ከቡራዩ ከተማ ወደ አምቦ ለማሳለፍ ሲሞክሩ ነው የተደረሰባቸው። በዚህም አሽከርካሪው፣ ፋርማሲስት እና ሁለት የጥይቱ ተቀባዮች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳዩ እየተጣራ … [Read more...] about በአምቦ ከተማ ጥይቶችን በአምቡላንስ ሲያጓጉዙ የተገኙ ተያዙ
ዘመቻ: “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ – #Handsoffethiopia”
ባለፉት 24 ሰዓታት “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ - #Handsoffethiopia” በሚል መሪ ቃል በተካሄደ የትዊተር ዓለም አቀፍ ዘመቻ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸው ተገለፀ። 100 ሺህ ገደማ የትዊተር መልዕክት በተሰራጨበት ዘመቻ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንዲከበር የሚጠይቁ እና አሸባሪው ህወሓት አገር ለማፍረስ እየሰራ ያለውን ሴራና ግፍ የሚያወግዙ መልዕክቶች ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እና መገናኛ ብዙሃን ጭምር ተላልፈዋል። በትዊተር ዘመቻው በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት እየተንቀሳቀሱ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሚጠይቀው መልዕክት ዐቢይ አጀንዳ ነበር። የትዊተር ዘማቾቹ በተለይም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡትን የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፊልትማን እየጠቀሱ፣ … [Read more...] about ዘመቻ: “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ – #Handsoffethiopia”
ወንድማማቾቹ የኢትዮጵያ ዘማቾች
ወጣት አለኸኝ ይመኑ እና ወጣት ግርማ ብሩ ከአንድ ማህጸን የተወለዱ ወንድማማቾች ናቸው። ውልደትና እድገታቸው ደግሞ በአዳማ አቅራቢያ በሚገኘው ልዩ ስሙ ቆቃ በተባለው አካባቢ ነው። ምንም እንኳን የእናት አንጀት ለልጆቿ ምን ያህል እንደሚራራ ቢተወቅም አገር ጥሪ ባቀረበች ጊዜ ግን ከሰንደቅ ዓላማ የሚበልጥ የለምና ኢትዮጵያን ከጠላት እንዲታደጉ እናታቸው መርቀው በደስታ ለውትድርና እንደላኳቸው ይናገራሉ።ቤተሰብና የአካባቢው ሰዎችም ልጆቻቸው ለአገር መከታ ይሆኑ ዘንድ በምርቃትና በደስታ ሸኝተዋቸዋል። (ኢብኮ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ወንድማማቾቹ የኢትዮጵያ ዘማቾች
“ምዕራቦች በምዕራብ —– የትንታጎች ድል”
ሽብርተኛው የህወሀት ሽብርተኛ ቡድን አገራችንን ለመበታተንና ህዝባችንን አንገት ለማስደፋት የከፈተብንን ጦርነት ለመመከት በማይፀብሪ ግንባር የተሰማሩት የምዕራብ ዕዝ ፣ የአማራ ልዩ ሀይል ፣ ህዝባዊ ሚሊሻ ፣ ፋኖ እና የክተት ጥሪውን ተቀብለው የተሰለፉ ሀይሎች አንፀባራቂ ጀግንነት በመፈፀም ላይ ይገኛሉ። ጁንታው ባለፉት ቀናት የሰነዘረውን ማጥቃት በመመከትና ወደ መልሶ ማጥቃት በመሸጋገር በተወሰደው እርምጃ 222 የጠላት ሀይል ተደምስሷል። 01 ዲሽቃ፣ 04 መትረየስ፣ 01 ስናይፐር፣ 04 ተተካይ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 31 ኋላቀር መሳሪያ፣ 25 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 4 ሺ የብሬን ጥይት፣ 3ሺ800 የብሬን ጥይት፣ 100 የዲሽቃ ጥይት በመማረክ በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ችሏል። የምዕራብ ትንታጎቹ በግንባሩ ከተሰማራው ሀይል ጋር በመሆን … [Read more...] about “ምዕራቦች በምዕራብ —– የትንታጎች ድል”
ትውስታ ዘ ዳንሻ – ታላቁ ጥቁር!
አምስተኛ መካናይዝድ ክፍለጦር ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ እንደ ወትሮው ከዋርድያዋች ውጭ ሁሉም ተኝቷል። አንድ ታላቅ ፣ ጥቀር የሌሊት ልብሱን እንደ ለበሰ መፅሃፍ ያነባል ድንገት የቶክስ ድምፅ ሰማ በአካባቢው ሁሌም የቶክስ ድምፅ መስማት የተለመደ ቢሆንም ወታደር ነውና ምልልስ ካለ ብሎ ለማዳመጥ ሞከረ ከሁለት አቅጣጫ መሆኑን ተረዳ። ስልኩን አነሳ ወደተለያየ ቦታ ደወለ ሁሉም አይሰራም ስልኩን አየው ኔትወርክ የለውም አሁን ችግር እንዳለ ተራዳ ካለበት ክፍል ግድግዳ እየታከከ ወደ በሩ ተጠጋና በሩን ሲከፍተው የተመታ ጓዱ ከነክላሹ በጀርባው ወደቀ ወዲያው የቶክስ ሩምታ ወደ በሩ አቅጣጫ ተከፈተበት እንደምንም ከወደቀው ጓዱ ካላሹን ተቀብሎ እየተኮሰ በቅርብ ቀን ወደተሰራች የብሎኬት ግቢ ዘሎ ገባ። በግቢው ውስጥ አንደ ገባ የራሱ ጓድ የሆነች ሴት ወታደር በብሎኬት አጥር ቀዳዳ … [Read more...] about ትውስታ ዘ ዳንሻ – ታላቁ ጥቁር!
ጥቁር ውሃ ላይ አስጨርሶ፣ እንደገና የፈረጠጠው ጄኔራል ከበደ ፈቃዱ ማን ነው?
የህወሃቱ ታጋይ ጄ/ል ከበደ በ1988 ዓም የ31ኛ ክ/ጦር 3ኛ ብርጌድ ፓራ ኮማንዶ፣ የ1ኛ ሻለቃ አዛዥ ሆኖ ሰርቷል። በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት በ31ኛ ክ/ጦር ምክትል ብርጌድ አዛዥ ሆኖ አገልግሏል። በ1992 ዓም 35ኛ ክ/ጦር ስትፈጠር የ35ኛ ክ/ጦር 3ኛ ብርጌድ አዛዥ ሆኖ ተሹሟል። በ1997 ዓም ኮር የሚባለው አጀረጃጀት ፈርሶ ዕዝ የሚባል አደረጃጀት ሲቋቋም፣ ግለሰብ የ35ኛ ክ/ጦር ም/አዛዥ ቀጥሎም የ33ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ሆኖ እስከ 2006 ዓ/ም ሠርቷል። በ2006 ዓ/ም እነ ጄኔራል አበባው ታደሰን ለማስወጣት በተደረገው ግምገማ፣ ግለሰቡ የአበባው አሽከር ነህ ተብሎ ተፈርጇል። ይህን ተከትሎም ከክፍለ ጦር አዛዥነቱ ተነስቶ፣ የዕዙ ማሰልጠኛ ት/ት ቤት አዛዥ ሆኖ ተመድቧል። የጡረታው ጊዜ ሲደርስ “ተጠቅሞ ይውጣ” ተባለና … [Read more...] about ጥቁር ውሃ ላይ አስጨርሶ፣ እንደገና የፈረጠጠው ጄኔራል ከበደ ፈቃዱ ማን ነው?
የፎቶ ሌብነትና የአምነስቲ ቅሌት
አምንስቲ ኢንተርናሽናል ለምርጫ ያነሳሁትን ፎቶ ወስዶ የተጠቀመበትን መንገድ እንዲያስተካክል የተቻለውን ጥረት አድርጎ የማይፈታ ከሆነ ጉዳዩን በተመለከተ ተቋሙን ለመክሰስ እገደዳለሁ ሲል የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ አማኑኤል ስለሺ አስታወቀ። ጋዜጠኛ አማኑኤል በጉዳዩ ዙሪያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገረው፤ አምንስቲ ኢንትርናሽናልን ለማነጋገር ጥረት እያደረገ ነው። "በስልክና በኢ-ሜይል ለማግኝት ጥረት እያረግን ቢሆንም እስካሁን ምንም ምላሽ አልሰጡንም። አሁን 22 ሰዓታት አልፎታል። በርካታ አለም አቀፍ ሚዲያዎችና ተቋማት ይህንን የተቀናበረ ምስል ተቀባብለውታል። ለራሳቸው ዓላማ የሚያውሉት እንኳን ቢሆን መቀየር የተከለከለ ነው" ሲል ተናግሯል። አምነስቲ ለመረጃው የተጠቀመውን ፎቶ ግራፍ በተመለከተ በውይይት ለመፍታት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ … [Read more...] about የፎቶ ሌብነትና የአምነስቲ ቅሌት
አሜሪካ በኢትዮጵያ ምን እያደረገች ነው? ምንስ ነው የምትፈልገው?
ምዕራባውያን ሌሎች አገራትን እንዳፈረሱ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚፈልጉበት ምክንያት ምዕራባውያን በዕርዳታ ሰበብ እንደ ሊቢያ፣ ሶሪያ፣ የመን ያሉ አገራትን እንዴት አፈረሷቸው? ተራዛሚ ተረጂነት በአንድ አገር ላይ እንዴትና ለምን እንደሚፈቅዱ? በኤርትራና በሶማሊያ የተደረገው እንዴት በኢትዮጵያም ለመፈጸም እያሤሩ እንደሆነ? ዕርዳታን ለጦር ጣልቃገብነት እንዴት እንደሚጠቀሙበት? በዚህ ሁሉ ውስጥ የኦባማ አስተዳደር የፈጸመው ሤራ፤ በተለይ ሊቢያን በማፍረስ በኩል እንዴት የፈጸመው ደባ እና አሁንም በኦባማ ዘመን የነበሩ ሰዎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚያደርጉት ሤራ ምን እንደሆነ በዚህ የሸገር ራዲዮ ዝግጅት ላይ ያገኙታል፤ ያድምጡት። https://youtu.be/Rsl980bo_Tw ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about አሜሪካ በኢትዮጵያ ምን እያደረገች ነው? ምንስ ነው የምትፈልገው?