የጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ 45 ቶን የአቮካዶ ምርት ወደ ውጭ በመላክ ምንዛሬ ለማግኘት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
ምርቱን ወደ ስፔን፣ ፈረንሳይና የተባበሩት አረብ ኤሚሬት እንደሚልክ ነው የገለፀው።
ወረዳው የተሻሻሉ የአቮካዶ ዝርያዎችን በ350 ሄክታር መሬት ላይ እያለማ እንደሚገኝም አስታውቋል።
የመስቃን ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መሀመድ ሳኒ÷ ወደውጭ ለመላክ ከታቀደው የአቮካዶ ምርት እስካሁን 20 ቶን መላኩን አስታውቀዋል።
አቮካዶ በአመት ሁለት ጊዜ ምርት እንደሚሰጥ ያመለከቱት አቶ መሀመድ በአምናው የምርት ዘመን 26 ቶን የአቮካዶ ምርት ወደ ውጭ መላኩንም መናገራቸውን ከጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በወረዳው የሚገኙ 2ሺህ 100 አርሶ አደሮች በ10 ክላስተር ተደራጅተው በአቮካዶ ልማቱ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ያስታወቁት አቶ መሀመድ በወረዳው ከተተከለው የአቮካዶ ዛፍ መካከል በ200 ሄክታር ላይ የተተከለው ምርት እየሰጠ ነው ብለዋል። (ኤፍቢሲ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply