የዕርዳታ አቅራቢዎች ከኢትዮጵያ ኢትዮጵያ በአፍራሽ ስራ ላይ ተሰማርተዋል ያለቻቸውን አንዳንድ የእርዳታ አቅራቢዎችን ከሀገር ልታባርር እንደምትችል አስጠነቀቀች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥረው ነበር። አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፥ "አንዳንድ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪዎች በሌሎች ሀገራት እንደተለመደው በኢትዮጵያም ከዚህ በፊት እንደታየው ከእርዳታ እህልና ከእርዳታ አቅርቦት ጋር በማያያዝ ሌላኛውን ወገን የማስታጠቅ ፣ ትግሉ፣ እንቅስቃሴው እንዳይቆም፣ ቀውሱ እንዳይበርድ ለማድረግ የሚያስችል አፍራሽ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል" ብለዋል። አክለውም፥ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ባለፉት 8 ወራት ይህ ሌላኛውን ወገን ለማስታጠቅ የሚደረገው ሙከራ እንዳጋጠመ ፤ ይህ ጉዳይ መልክ መያዝ እንዳለበት መንግስት ሲያሳስብ … [Read more...] about በአፍራሽ ሥራ የተጠመዱ የረድኤት ድርጅቶች ሊባረሩ ይችላሉ
Right Column
የመንግሥት ሚዲያዎች ፍትሃዊነታችንን አጉድላችሁብናል – ወ/ት ብርቱካን
“ዛሬ እዚህ የምትቀርጹን የመንግስት ሚዲያዎች በጣም በትህትና ልነግራችሁ እፈልጋለሁኝ። የመንግስት ባለሥልጣናት ኮታቸው ላይ የተሰካው ማይክራፎን የማይወልቅ ይመስል ሌት ተቀን የእነሱን ካምፔን እና ቅስቀሳ ስታስተላልፉ ቆይታችሁ የተቃዋሚዎችን 10 እና 15 ደቂቃ ማድረጋችሁ ፍትሃዊነታችንን አጉድሎብናል። እንዳላየ ያለፍነው ግማሹ የኛ ሥልጣን ስላልሆነ ነው። የእኛን ስልጣን እንደምናከብር የሌሎችንም እናከብራለን” የምርጫ ውጤት በማሳወቂያ መርሃግብር ላይ ይህንን የተናገሩት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ ሰብሳቢዋ "ኢትዮጵያ ሁልጊዜ በምርጫ ብቻ ስልጣንን የምታሸጋግር አገር መሆኗን አሳይታለች" ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የውጤት ማሳወቂያ መርኃ-ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። መርኃ-ግብሩን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር … [Read more...] about የመንግሥት ሚዲያዎች ፍትሃዊነታችንን አጉድላችሁብናል – ወ/ት ብርቱካን
አዲስ አበባን በፓርላማ የሚወክሏት ተመራጮች
አዲስ አበባ ከተማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 23 መቀመጫዎች አሏት፡፡ ሰኔ 14፤ 2013 በተካሔደው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ፤ ከ23 የፓርላማ መቀመጫዎች ገዢው ብልጽግና ፓርቲ በ22 የምርጫ ክልሎች ማሸነፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትላንት ቅዳሜ ምሽት አስታውቋል፡፡ብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ያላቀረበበት ብቸኛ የአዲስ አበባ ምርጫ ክልል በሆነው ምርጫ ክልል 28 ደግሞ፤ የግል ተወዳዳሪው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ማሸነፋቸው ተገልጿል፡፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ናቸው፡፡ የምርጫ ውጤት ብልጽግና ፓርቲ በከፍተኛ ውጤት፣ አብላጫውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበርን በማግኘት አሸንፏል። በዚህ መሰረት ብልጽግና ፓርቲ ከ436 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ 410 መቀመጫ ማግኘቱን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የአማራ … [Read more...] about አዲስ አበባን በፓርላማ የሚወክሏት ተመራጮች
አዲስ አበባ ሳያርፉ በቀጥታ ወደ ትግራይ ክልል በአየር ዕርዳታ ማድረስ አይቻልም
ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ማስጠንቀቂያ መስጠቱን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ። መንግሥት ዓርብ ሐምሌ 2 ቀን 2013 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ እንዳሰታወቀው፣ የተባበሩት መንግሥትታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ የሆነው ተቋም፣ የኢትዮጵያን ሕግ ያላከበረ ድርጊት በተደጋጋሚ እየፈጸመ ከመሆኑም በላይ፣ በትግራይ ክልል ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የሚያዛባ መግለጫ እያወጣ መሆኑን በመግለጽ ለተቋሙ ማስጠንቀቂያ ጽፏል፡፡ “በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀውን ድርጅት የትግራይ መከላከያ ኃይል በማለት በሚያወጣው መግለጫ በተደጋጋሚ ጊዜ እየጠቀሰ ነው፡፡ በትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ የሚያወጣው መረጃ የተዛባና ሕገወጥ የተባለውን ኃይል የሚያበረታታ ነው” በማለት ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ … [Read more...] about አዲስ አበባ ሳያርፉ በቀጥታ ወደ ትግራይ ክልል በአየር ዕርዳታ ማድረስ አይቻልም
የትግራይ ጉዳይ፤ በረከተ መርገም!
የኢትዮጵያ መንግሥት ሰኔ 21 ቀን ያወጀውን የትግራይ ክልል የተኩስ አቁም አዋጅ በተመለከተ የተለያዩ ሀሳቦች እየተሠነዘሩ ይገኛሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ መንግስት መተቸት ያለበት በመዘግየቱ ነው። የሕግ ማስከበር ዘመቻው በተጠቃለለ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ የተኩስ አቁም አዋጁን አውጆ ወደ ፖለቲካዊ መፍትሄ ቢያመራ መልካም ነበር። ምናልባት ግን ከፊት ለፊቱ የነበረው ሐገራዊ ምርጫ ውሳኔውን እንዲያዘገይ እንዳደረገው ይታመናል። የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ በላይ የትግራይን ጉዳይ መሸከም አልነበረበትም። ቀድሞም የተለያዩ የውስጥና የውጭ አካላት ይሄንን ጉዳይ አንስተው ሞግተዋል። አውሮፓና አሜሪካ ጠንካራ ማእቀብ ለመጣል እየተዘጋጁ ነው። ይህ ማእቀብ የኢትዮጵያን ምርቶች እስካለመግዛት የሚደርስ ነው። ይህ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከባድ ሸክም ነው። አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት የትግራይ ችግር … [Read more...] about የትግራይ ጉዳይ፤ በረከተ መርገም!
“መቀሌን ከሽሬ ወይም ከበሻሻ የሚለያት የስበት ማዕከል የለም”
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ከትናንት በስቲያ አመሻሹን ከጋዜጠኞች ጋር ተገናኝተው ነበር። ሚዲያው በምርጫው ላደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለማመስገን በተዘጋጀው በዚህ መርሀ ግብር ላይም ሚዲያውን ካመሰገኑ በኋላ ስለ ምርጫው እና ስለ ትግራይ ሁኔታ ለጋዜጠኞች አብራርተዋል። ካነሷቸው ነጥቦች መሀከልም የተወሰኑትን በግርድፍ እንዲህ አስታውሻቸዋለሁ በምርጫው እኛም ሆነ ተቃዋሚዎች የተመኘነውን ያህል ቡራቡሬ ፓርላማ አላገኘንም! ተቃዋሚዎች በምርጫው ውጤት ደስተኛ ባይሆኑም በምርጫ ቦርድ፥ በፍርድ ቤት እና በሚዲያ ላይ ቅሬታ እንደሌላቸው ተስማምተናል! ሚዲያው የትርክት ለውጥ ላይ በደንብ መስራት አለበት። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ከዚህም በላይ መስበክ አለበት! በትግራይ ባካሄድነው ዘመቻ ተይዘውብን የነበሩትን መሳሪያዎች በሙሉ አስመልሰናል። ማስተካከል የምንፈልገውንም … [Read more...] about “መቀሌን ከሽሬ ወይም ከበሻሻ የሚለያት የስበት ማዕከል የለም”
ምርጫው ተአማኒና ሰላማዊ ነበር – የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢ
ኢትዮጵያ ያካሄደችው ምርጫ ተአማኒና ሰላማዊ ነበር ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪና የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ተናገሩ። ታዛቢ ቡድኑ ከምርጫ ቅስቀሳው አንስቶ እስከ ምርጫው እለት ያለውን ሂደት መከታተሉን የጠቀሱት የታዛቢ ቡድኑ መሪ የጸጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በቀር የቅስቀሳ ሂደቱ በፓርቲዎች ዘንድ ፍትሃዊነቱ የተጠበቀ ነበር ብለዋል። የተመረጡ ጣቢያዎች ላይ ምልከታ አድርገናል ያሉት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ምርጫውን ተዘዋውረን በተመለከትንበት፣ የምርጫ ቦርድን ተቋማዊ ጥንካሬ ተመልክተናል፣ መንግስት ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን አስፈላጊ የጸጥታ እርምጃ ተግባራዊ አድርጓል ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን ያደረገው ጥረትም የሚመሰገን መሆኑን ነው የገለጹት፡፡ ምርጫው ከሞላ ጎደል ሰላማዊ በሆነ መልኩ ነው … [Read more...] about ምርጫው ተአማኒና ሰላማዊ ነበር – የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢ
“ቀኑ ለመራጮችና ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን ለአገራችንም ጥሩ ነው” ወ/ሪት ብርቱካን
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እኩለ ቀን ላይ ምርጫውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ ‹‹ቀኑ ለመራጮች፣ ለፓርቲዎችና በአጠቃላይ ለአገራችን ጥሩ ነው፤›› ብለዋል፡፡ በመጀመርያው ዙር የምርጫ ሒደት እስካሁን አንድም የፀጥታ ችግር አልገጠመንም፡፡ አምቦ አንድ ጣቢያ ላይ ምንም የተፈጠረ ነገር ሳይኖር ለአስፈጻሚዎች በደረሳቸው መረጃ በመደናገጥ ለጊዜው ገለል ብለዋል፡፡ ነገር ግን እናስቀጥለዋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ከባድ ችግር የለም፡፡ ምርጫው መደረግ ባለባቸው ሁሉም ሥፍራዎች እየተካሄደ ነው፡፡ ዜጎችም እየመረጡ ይገኛሉ፡፡ ምርጫው መደረግ ባለባቸው ጣቢያዎች በአብዛኛው በሚባል ሁኔታ በሰዓቱ ከፍተው መራጮችን ሲያስተናግዱ ቆይተዋል፡፡ አዲስ አበባ ላይ 9 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ኃላፊነት የጎደላቸው አስፈጻሚዎች በቦታቸው ባለመገኘታቸው ጣቢያዎቹ ሳይከፈቱ ቆይተዋል፡፡ … [Read more...] about “ቀኑ ለመራጮችና ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን ለአገራችንም ጥሩ ነው” ወ/ሪት ብርቱካን
ከ6ሺ ኩንታል በላይ በቆሎ በግለሠብ መጋዘን ውስጥ ተገኘ
በደብረ ማርቆስ ከተማ ከ6ሺ ኩንታል በላይ በቆሎ በአንድ ግለሠብ መጋዘን ውስጥ ተከዝኖ ተገኘ። በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ ዐ5 ልዩ ቦታው ኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ በሚገኝ ለሙጫና እጣን ማቀነባበሪያ መጋዘን ውስጥ ከ6ሺ ኩንታል በቆሎ በላይ ተከዝኖ መገኘቱን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ገልጿል። የተገኘውን እህል በከተማው ለሚገኙ አስራ አራት ሸማች ህብረት ስራ ማህበራት እንደሚከፋፈል እና በዛሬው ዕለት ሁለት ሸማች ማህበራት ከአራት መቶ በላይ ኩንታል መውሰዳቸውን እና ለህብረተሰቡ እንደሚከፋፈል የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ብርሀኑ መኩሪያው ገልጸዋል። የወንጀሉ ጉዳይም ፖሊስ አስፈላጊውን ምርምራ እያጣራ መሆኑን አስረድተዋል። (የደብረ ማርቆስ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከ6ሺ ኩንታል በላይ በቆሎ በግለሠብ መጋዘን ውስጥ ተገኘ
በበጀት ዓመቱ 272 ማንሆል ክዳኖች ተሰርቀዋል – የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በበጀት ዓመቱ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው 272 ማንሆል ክዳን እንደተሰረቀበት አስታውቋል። ባለስልጣኑ በአሁኑ ሰዓት ከ1500 ኪሎ ሜትር በላይ የፍሳሽ መስመሮች በመዲናዋ ተዘርግተዋል ያለ ሲሆን የፍሳሽ መስመሮቹን የፍሰት መቆጣጠሪያነት እና ጽዳት ለመከታተል የሚያስችል ማንሆሎች በመገንባት እንዲከደኑ ቢያደርግም 272 ክዳኖች በህገወጥ ሰዎች ተሰርቀዋል ብሏል። ይህም በፍሳሽ መስመሩ ላይ ባዕድ ነገር እንዲገባ በማድረግ የማጣሪያ ጣቢያዎች ህልውና እየተፈታተነ እንደሚገኝና ከዚህም ባሻገር ህብረተሰቡ ክፍት በሆነ ማንሆል ውስጥ ገብቶ ጉዳት እየደረሰበት እንደሆነ ገልጿል። ድርጊቱ ህገ-ወጥ ድርጊቱ የከተማዋን የዘመናዊ ፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ላይ አደጋ የደቀነ መሆኑን በመረዳት ከምንም በላይ ህብረተሰብ እና የጸጥታ አካላት … [Read more...] about በበጀት ዓመቱ 272 ማንሆል ክዳኖች ተሰርቀዋል – የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን