የአገር መከላከያ ሰራዊት "ርዝራዥ" ሲል የሚጠራውን ሃይል መደምሰሱን አስታወቀ። ሃይሉ የተደመሰሰው ድንበር አቋርጦ ወደ ሱዳን ለመሸሽ በሞከረበት ወቅት እንደሆነ ታውቋል። ከተገደሉት በፍተሻ "የኦሮሞ ማንነት መታወቂያ ተሰርቶላቸው ነበር" ተብሏል። የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት የግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት፤ እነዚህ የጁንታው አባላት ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ የሌላ ክልል መታወቂያ በመያዝ ከሀገር ሊሸሹ ሲሉ ሰራዊቱ በደረገው ከፍተኛ ጥረት ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ የዚህ ድርጊት ዋነኛ አላማ እነዚህን አባላት ወደ ሱዳን በማሸሽ ከዚያ ሆኖ ሀገር ውስጥ ያሉትን ተጣቂ ሀይሎች በሽምቅ ውጊያ በማሰማራት ሀገር ለመበጥበጥ የታቀደ እንደነበር ሌ/ጄነራል ባጫ በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡ እርምጃ በተወሰደባቸው … [Read more...] about “የጁንታው አባላት ከአገር ውጭ ለመውጣት ያደረጉት ጥረት ከሽፏል” – ሌ/ጄነራል ባጫ
News
የዓለም ባንክ የ907 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ አደረገ
የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ለሚተገበሩት ሶስት ፕሮጀክትች የሚውል የ907 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ዛሬ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና ዓለም ባንክ ግሩፕ ምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሚ/ር ዲዮን ነው የተፈራረሙት። የገንዘብ ድጋፉ በኢትዮጵያ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ፤ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎትን አሰጣጥንና ተደራሽነትን ለማሳደግ እንዲሁም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚውል ነው ተብሏል። የመጀመሪያው የ200 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በኢትዮጵያ ውስጥ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚውል ነው። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ክፉኛ የተጎዱ እንተርፕራይይች አዋጭ በሆነ መንግድ እንዲቀጥሉና በንግድ ውስጥ እንዲቆዩ ለማድረግ … [Read more...] about የዓለም ባንክ የ907 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ አደረገ
ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ማዘጋጀት ትፈልጋለች፡- አቶ ደመቀ መኮንን
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሩሲያ-አፍሪካ የትብብር ጉባኤ ዋና ጸሐፊ አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭ ጋር በጽ/ቤታቸው በተወያዩበት ወቅት ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ማዘጋጀት እንደምትፈልግ ተናግረዋል። በቀጣይ ዓመት በአፍሪካ ሊካሄድ ስለታሰበው ሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤን ኢትዮጵያ ለማዘጋጀት ዝግጁ መሆኗን ነው አቶ ደመቀ መኮንን የገለፁት። አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭ ስለ ጽ/ቤታቸው ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የአፍሪካና ሩሲያ ኩባንያዎች በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችል የኢኮኖሚ ትብብር ማህበር መቋቋሙን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አያይዘውም የጉባኤው ዝግጅት አካል የሆነ ውይይት በመጪው ክረምት ከአፍሪካ ህብረትና ከአፍሪካ አገራት ጋር ምክክር እንደሚደረግም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ያላትን … [Read more...] about ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ማዘጋጀት ትፈልጋለች፡- አቶ ደመቀ መኮንን
የአብን “ፀሐይ” ጎንደር ላይ ጠለቀች
ሤራ አክሻፊው ጎንደር ዛሬም ታሪክ ሠራ የኦህዴድ ጽንፈኞችና “አክራሪ” የሚባለው አብን በአንድነት የጠመቁት ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ ሴራ ዛሬ ጎንደር ላይ ተገለበጠ። ጎንደር የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማርሽ ቀያሪነቱን አሳየ። ሰልፉ ክልሉን ለማናወጥና ሕዝብ እንዲጋጭ ሌት ተቀን ለሚሰሩ ፖለቲካዊ ሞት እንደሆነ ተመልክቷል። ሰሞኑንን በደረሰው ዘገናኝ ዕልቂትና የንብረት ውድመት ማግስት የሽግግር መንግስት የጠየቁ አሉ። አብን መንግሥት እንደሌለ ሲያውጅና ክተት ሲጠራ “የሞሳድ ሥራ አስፈጻሚ” የሚባሉት፣ ቀደም ብለው አገራቸውን ከድተው የሸሹትና በውድ የኢትዮጵያ ጄኔራሎች የተመራውን መፈንቅለ መንግሥት እንዳከሸፉ የሚታወቁት ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ፤ አበበ በለው በሚመራው የአዲስ ድምጽ ሬዲዮ በኩል የሽግግር መንግሥት ለማቋቋም የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን ይፋ አድርገዋል። አያይዘውም … [Read more...] about የአብን “ፀሐይ” ጎንደር ላይ ጠለቀች
ፍፁም ብርሃኔና ታምራት የማነ በቁጥጥር ሥር ዋሉ
የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ጋዜጠኛ ፍፁም ብርሃኔ እና የአይጋ ፎረም ዋና አዘጋጅና የኢትዮጵያ ተወካይ ጋዜጠኛ ታምራት የማነ በቁጥጥር ሥር መዋላቸዉ ተነግሯል፡፡ ልዩ ዘመቻዎች ሃይል 2ኛ ኮማንዶ ብርጌድ 3ኛ ኮማንዶ ሻለቃ በትግራይ ክልል ህግ በማስከበር ዘመቻ አመርቂ ግዳጅ መፈፀማቸው ተገልጿል፡፡ በዚህም የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ጋዜጠኛ ፍፁም ብርሃኔ እና የአይጋ ፎረም ዋና አዘጋጅና የኢትዮጵያ ተወካይ ጋዜጠኛ ታምራት የማነ በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ የ3ኛ ሻለቃ ዋና አዛዥ ሻለቃ ደረጄ ዴቢሳ እንደገለፁት ፣ በትግራይ በተደረገው ህግን በማስከበር ዘመቻ ጠላት የሚመካባቸውን ምሽጎች በሶሮቃ፣ በዳንሻ፣ በባካር፤ በመሶበር፤ በጨርጨርና በአይደፈር ተራሮች ላይ የተገነቡ ምሽጎችን በመስበር የጠላትን ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን መቆጣጠር ተችሏል ብለዋል፡፡ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር … [Read more...] about ፍፁም ብርሃኔና ታምራት የማነ በቁጥጥር ሥር ዋሉ
“ተዋግተን አይደለም ስንተኛ ብንውል እንኳን መቀሌና አዲስ አበባ አይገቡም” ጄኔራል ባጫ
በትግራይ ክልል በስምንት ቡድኖችና አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የነበረው የሕወሓት ቡድን ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን፣ በአገር መከላከያ ሠራዊት የደቡብ ግንባር ዋና አዛዥ ሌተና ጄኔራል ባጫ ደበሌ ማክሰኞ ሚያዝያ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. አስታወቁ፡፡ “በትግራይ ውስጥ በስምንት ቡድኖች የተደራጀ ኃይል በአንድ ጊዜ ለመደምሰስ በሠራዊታችን ዘመቻ ተደርጎበታል፡፡ አካባቢዎቹም በምሥራቅ ትግራይ አፅቢ፣ ሐይቅ መሳል፣ ደሴአ፣ በደቡብ ትግራይ ዋጅራት፣ ቦራ፣ በሰሜን ምሥራቅ ትግራይ ጽጌረዳ፣ ሐውዜን፣ እንዲሁም በሰሜን ትግራይ ውቅሮ ማርያም፣ ዛና ናቸው፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች ሰፋ ያለ የጥቃት ድርጊት ሲፈጽሙ ስለነበር ወታደራዊ ዘመቻ ተካሂዶባቸው ተደምስሰዋል” ሲሉ ጄኔራል መኮንኑ አስረድተዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ሠራዊቱ ባደረገው ዘመቻ ትንንሽ ማሠልጠኛዎችንና የሕወሓት መሪዎችን እንደ ጠባቂ … [Read more...] about “ተዋግተን አይደለም ስንተኛ ብንውል እንኳን መቀሌና አዲስ አበባ አይገቡም” ጄኔራል ባጫ
የስኳር ፋብሪካዎች ተሽጠው ዕዳቸውን እንዲከፍሉ ተወሰነ
በመንግሥት ባለቤትነት ሥር ከሚገኙት 13 ስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ አሥሩ ለግል ባለሀብቶች ተሸጠው፣ ከሽያጩ የሚገኘው ገቢ በከፍተኛ የዕዳ አጣብቂኝ ውስጥ ናቸው ተብለው ለተለዩ ሰባት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ዕዳ ክፍያ ጥቅም ላይ እንዲውል ተወሰነ። ሪፖርተር ያገኘው መንግሥታዊ መረጃ እንደሚያመለክተው ሰባቱ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ካለባቸው አጠቃላይ ዕዳ ውስጥ፣ አመዛኙ እንደ አዲስ ወደ … [Read more...] about የስኳር ፋብሪካዎች ተሽጠው ዕዳቸውን እንዲከፍሉ ተወሰነ
“ኤርትራዊ ነን” በማለት የመኖሪያ ፈቃድ ሲቀበሉ የኖሩ የትግራይ ሰዎችን መለየት ተጀመረ
ጀርመን መረጃ መጠየቅ ጀምራለች “የማንፈልገው ጉዳይ ውስጥ እየገባን ነው” ይላሉ ዜናውን ያረጋገጡት ዲፕሎማት። ተቀማጭነታቸው አውሮፓ የሆነው የጎልጉል የዘወትር ተባባሪያችን እንዳሉት አንዳንድ አገራት የስደተኞች መረጃ ለመጠየቅ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። ጀርመን ወደ ሥራ ገብታለች። በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ድንበር አካባቢ ባሉ የኤርትራ ስደተኞች ካምፕ በተመዘገቡ ስደተኞች ስም በርካታ የትግራይ ተወላጆች “ስደተኛ ናቸው” በሚል ከአገር እንዲወጡ መደረጉን እንደ አንድ ምክንያት ጠቅሰው የዓለምአቀፉ የስደተኞች ተቋም ትግራይ ድንበር 20 ኪሎ ሜትር ላይ ያሉት ካምፖች እንዲዘጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው ጥያቄው የተነሳው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ንግግራቸው የኤርትራን ወደ ትግራይ መግባት አስመልክቶ ሲናገሩ ይህንኑ ማለታቸውን ተከትሎ የጀርመን … [Read more...] about “ኤርትራዊ ነን” በማለት የመኖሪያ ፈቃድ ሲቀበሉ የኖሩ የትግራይ ሰዎችን መለየት ተጀመረ
ምርጫ ቦርድ የኦነግን ጥያቄ ውድቅ አደረገ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች መካከል በተፈጠረ መከፋፈልና ውዝግብን የተመለከቱ እግዶች፣ አቤቱታዎችና ከሁለቱም ወገን የሚመጡ ማሳወቂያ ደብዳቤዎችን ሲቀበል መቆየቱ እንዲሁም ችግሩን ለመፍታት ቡድኖቹን በተናጠል እንዲሁም የፓርቲውን የስነስርአትና የቁጥጥር ኮሚቴን በማነጋገር ያሉትን አስተዳደራዊና ህጋዊ መንገዶች ሁሉ እንደተጠቀመና መፍትሄዎችን ለመስጠት ጥረት ሲያደርግ እንደነበር አስታውሶ፣ በመጨረሻም ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ፓርቲው ካለበት ችግር ብቸኛ መውጫ መንገድ መሆኑን በመረዳትና በውዝግብ ውስጥ ያሉ አመራር ክፍሎችም ያመኑበት በመሆኑ፣ በአመራሮች መካከል ያለው ችግር በጠቅላላ ጉባኤ እንዲፈታ መወሰኑ ይታወሳል። ኦነግ መጋቢት 7 ቀን 2013 ዓ.ም በቁጥር 19/ABO/2013 በተጻፈ ደብዳቤ ድርጅቱ መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ጠቅላላ … [Read more...] about ምርጫ ቦርድ የኦነግን ጥያቄ ውድቅ አደረገ
“እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ መንግሥት ኮሮጆ አይሰርቅም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
መንግሥት በምርጫ ዙሪያ በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ካድሬ እስካለፈው እሑድ ድረስ ማሠልጠኑን፣ ማክሰኞ መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም. በተካሄደው የአዲስ ወግ ውይይት ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ተናግረው፣ ዘንድሮ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው አገራዊ ምርጫ ፓርቲያቸው ብልፅግና ከተሸነፈ ሥልጣን ለማስረከብ ዝግጁ መሆኑን አስታወቁ። “እንደ ብልፅግና ፓርቲ ከተሸነፍን ሥልጣን ለማስረከብ ተዘጋጅተናል። ይህንን ካደረግን ደግሞ ከምርጫ በኋላ ሰላም የማይኖርበት ምክንያት አይኖርም። አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ካድሬ እስካለፈው ቅዳሜና እሑድ ድረስ ሥልጠና ላይ ነበር። ዋናው መልዕክት ኢትዮጵያ አሸናፊ መሆን አለባት ነው” ብለዋል። ኢትዮጵያ አሸናፊ የምትሆነው ሽንፈት ሲኖር በማመሥገንና መልካም በመመኘት ሥልጣን መስጠት ከተቻለ መሆኑን … [Read more...] about “እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ መንግሥት ኮሮጆ አይሰርቅም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ










