• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የአብን “ፀሐይ” ጎንደር ላይ ጠለቀች

April 22, 2021 09:48 pm by Editor 3 Comments

ሤራ አክሻፊው ጎንደር ዛሬም ታሪክ ሠራ

የኦህዴድ ጽንፈኞችና “አክራሪ” የሚባለው አብን በአንድነት የጠመቁት ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ ሴራ ዛሬ ጎንደር ላይ ተገለበጠ። ጎንደር የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማርሽ ቀያሪነቱን አሳየ። ሰልፉ ክልሉን ለማናወጥና ሕዝብ እንዲጋጭ ሌት ተቀን ለሚሰሩ ፖለቲካዊ ሞት እንደሆነ ተመልክቷል።

ሰሞኑንን በደረሰው ዘገናኝ ዕልቂትና የንብረት ውድመት ማግስት የሽግግር መንግስት የጠየቁ አሉ። አብን መንግሥት እንደሌለ ሲያውጅና ክተት ሲጠራ “የሞሳድ ሥራ አስፈጻሚ” የሚባሉት፣ ቀደም ብለው አገራቸውን ከድተው የሸሹትና በውድ የኢትዮጵያ ጄኔራሎች የተመራውን መፈንቅለ መንግሥት እንዳከሸፉ የሚታወቁት ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ፤ አበበ በለው በሚመራው የአዲስ ድምጽ ሬዲዮ በኩል የሽግግር መንግሥት ለማቋቋም የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን ይፋ አድርገዋል። አያይዘውም ተቃውሞው እስከ አራት ኪሎ ቤተመንግሥት እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ይህንኑ ተከትሎ ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ የኦፌኮ ወጣት ክንፍ አመራር “ምንም እንኳን አመራሮቻችን ቢታሰሩና በምርጫው ባንሳተፍም በክልላችን ጉዳይ ማንም እንዲፈተፍት በር አንከፍትም። ተቀባይነት የለውም። የሚሰሙት አንዳንድ ሃሳቦች ወቅቱን ካለመገንዘብ የመጣ ነው” ሲል ተናግሮ መሪዎችም ቢጠየቁ የተለየ መልስ እንደማይኖራቸው አመልክቷል። “ኦሮሙማ ይወደም” እያሉና እያስባሉ በኅብረት መንግሥት ስለመለወጥ ሲያስቡ መደነቁንና ሌሎች ክልሎች ምን ሊያስቡ እንደሚችሉ ለማወቅ አለመሞከራቸው እንደሚያሳስበው አክሎ ጠቁሟል።

በሰሜን ሸዋ በተለይ አጣዬ በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን ዘር የለየ ጭፍጨፋ በመቃወም አደባባይ የወጡት የጎንደር ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች “የከዳን ኦህዴድ እንጂ ወንድም የኦሮሞ ሕዝብ አይደለም” የሚል መፈክር አጉልተው በማሳየት ያሳዩት ተቃውሞ “ሥልጡን” ተብሏል። ጽንፈኛ አመለካከት ላላቸው ደግሞ ታላቅ መልዕክት እንደሆነ ነው የተጠቆመው።

ከሌሎች አካባቢዎች ዘግየት ብሎ በስከከነ መንፈስ መካሄዱ፣ በተለይም ከራያ በተጨማሪ ላለፉት 30 ዓመታት መከራ ለተፈራረቀበት የጎንደርና፣ የወልቃይት ህዝብ ነጻ መሆን አመራር የሰጡና ኤርትራና ጎንደርን ድንበረተኛ እንዲሆኑ ሰፊ ሥራ የሰሩ መሪዎችን በጎንደሩ የተቃውሞ ሰልፍ ስማቸው እየተነሳ ሲሰደቡ አልተሰማም።

አብን “ከፊት እመራዋለሁ” ሲል ድርጅታዊ መግለጫ አውጥቶ፣ መግለጫው አስቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩን “አሸባሪ ብሎና የክልሉን ነባርና አዲስ አመራሮች” ለአማራ ሕዝብ የማይቆረቆሩና የማያዝኑ “ተላላኪዎች” በሚል ፈርጆ በቀጣይ ባዘጋጀው የሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ “ኦሮሙማ (ኦሮሞነት) ይወደም” የሚል መፈክር መስተጋባቱ ቅሬታ አስነስቶ ነበር። ከዚያም በላይ የአማራን ምትክ አልባ መሪዎች ህይወት ያባከነው ጄኔራል አሳምነው ጽጌን እንደ ጀግና እንዲወደስ ማስደረጉ በክልሉም ውስጥ አሉታዊ አስተያየት እንዲነሳ ምክንያት ሆኖ ነበር።

የአማራ ክልል መስተዳድር በሰልፈኞቹ ቅሬታ ሙሉ ስምምነት እንዳለው፣ ሰልፉ በጨዋነት መደረጉን ዋጋ እንደሚሰጠው፣ የተነሳው የፍትህ ጥያቄ የመጨረሻ እልባት እስኪያገኝ ድረስ ዕረፍት እንደማይኖረው ጠቅሶ አንድነት በጠየቀበት መግለጫው አብንን ጠርቶ ጠንካራ ምላሽ ሰጥቷል።

ክልሉ ከህዝብ ነጥሎ “አደገኛ” ሲል አብን እያካሄደ ያለውን የፖለቲካ ገበያ አውግዟል። የአማራ ክልል ዛሬ ላይ ከየአቅጣጫው ችግር እንደገጠመውና በስከነ መንገድ ሕዝባዊነቱን ጠብቆ መፍትሄ መፈለግ እንደሚገባው ያመለከተው መግለጫው “በድርጅቱ ፕሬዚዳንት፣ በባለሥልጣናትና አመራሮች ላይ ስም እየተጠራ የተካሄደው ማጠልሸት ትናንትን የዘነጋ ጸያፍ ተግባር ነው” ሲል መንግሥትን በህግ እንዲጠይቅ አሳስቧል። የምርጫ መቀሰቀሻ ፖስተር ሳይቀር እየተመረጠ እንዲወድም መደረጉን ጠቅሶ ምርጫ ቦርድ በድንቡ መሰረት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።

ከለውጡ በፊት የነበረውን ኦሮሙማ እንቅስቃሴ “የኦሮሞ ደም የኔም ደም ነው” በሚል ገልብጦ ለውጡን አገር አቀፍ ይዘት እንዲኖረው ማርሻ የቀየረው ጎንደር፣ የፖለቲካውን ትግል እንዲነድና የትህነግ/ህወሃት መጥፊያ እንዲቃረብ በማድረጉ ሲጠቀስ እንደሚኖር ያወሱ ወገኖች፣ የአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በምላሹ “የአማራ ደም የኔም ደም ነው” ሲሉ የትግሉን አቅጣጫ በመቀበልና በማስተጋባት፣ በትህነግ የተፈራውን የኦሮሞና የአማራ ሕዝብ የትግል አንድነትን በማግነን ታሪክ መሠራቱን ገልጸዋል።

ዛሬም ከደረሰው ከፍተኛ ቀውስና ዘግናኝ ጭፍጨፋ ስሜት መውጣት ሳይቻል፤ ከግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በተበተነበት ሁኔታ የሽግግር መንግሥት ለማዋቀር ለሚደክሙ ክፍሎች የዛሬው የጎንደር ሰልፍ እንዳልተመቻቸው አስተያየት እየተሰጠ ነው።

ቀደም ሲል አዲስ አበባ ገብተው አንድ ወር የተቀመጡት ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ሥልጣን ጠይቀው በኢትዮጵያ ጉዳይ መጥፎ ሪኮርድ ስላላቸው፣ አገር ከድተው የነበሩ፣ ለዕርዳታ የመጣ ገንዘብ እንደዘረፉ የሚነገርባቸው በመሆኑና ለሌሎች የውጭ ኃይሎች እንደሚሰሩ መረጃ በመኖሩ በለውጡ ኃይል “ዞር በሉ” ሲባሉ አኩርፈው እንደወጡ በወቅቱ ተገልጾ ነበር።

በዚህ ጉዳይ በስፋት በጥሩ ሞጋች ጋዜጠኛ ያልተፈተኑት ዳዊት ያደራጇቸው ክፍሎች አማራ ክልል ላይ ዘመቻ ከጀመሩ መቆየታቸውን ጠቅሰው አስተያየት የሰጡ ጥቂት አይደሉም። ዛሬ ጊዜ ቆጥረው በሰጡት ዲስኩር ህዝብ መንግሥትን እንዲያስወግድ ጠይቀዋል። ሕዝብ ሲሉ ግን ኦሮሞውን፣ ሶማሌውን፣ ቢኒሻንጉሉን፣ አፋሩን፣ ደቡቡን፣ ሲዳማውን፣ ሶማሌውን ስለመሆኑ አላብራሩም። በጠያቂነት አብሯቸው ሲያወራ የነበረውም አበበ በለውም አላነሳባቸውም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው የነበሩት የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ከተማቸው በድንጋይና በአጠና ተዘጋግቶባቸው ነበር። በማኅበራዊ ሚዲያዎች የታዩት ምስሎች እንዳመለከቱት ባህር ዳር ቆሻሻ ነበር። ጉዳዩን ከአብን ጋር የተያያዘ መሆኑ ደግሞ አብን ወዴት እና የማንን ሥልት እየተከተለ ነው? የሚለውን እያጎላው መጥቷል። (ኢትዮ 12)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News

Reader Interactions

Comments

  1. ነፃ ሕዝብ says

    April 22, 2021 11:50 pm at 11:50 pm

    የአብን “ፀሐይ” ጎንደር ላይ ጠለቀች ፦ ምን ዓይነት አባባል ነው ? ይህ መፈክር በ2008 ዓ/ም ጭምር የተነገረ መሆኑን እንዴት ዘነጋችሁት ? አብን የተቋቋመው የአማራን ሕዝብ ዕልቂትና ጭፍጨፋ ለማስቆም ብሎም ለአማራ ሕዝብ ጠበቃ ለመሆን መሆኑን የዘነጋችሁት ይመስላል ! ጎልጉል ምንድነው ዓላማው ? የአማራ ሕዝብ እልቂት ያስደስታችኋል ማለት ነው ? አብን አማራ ነው ፥ ስለአማራ ሕዝብ ሞትና ሲቃይ መናገር ምንድነው ሃጢአቱ ? ሃጢአት የሚሆነው እንደ እናንተ ያለው የነፍሰ_ገዳዩና የአማራው ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት የሆነው የግራኝ አህመድ የጥፋት ዘር የሆነው አብይ አፈቀላጤዎች የውሸት ቃላት እየመነዘራችሁ ስትጽፉ በጣም ታሳዝናላችሁ ፥ የኦሮሞ ጽንፈኞች አማራ ዳውን _ዳውን ሲል ምን ብላችሁ ነበር ? የሰበሩንን ሰበርናቸው ፥ ነፍጠኛ ከኦሮሚያ ይውጣ ፥ ነፍጠኛ የኦሮሞ ጠላት ነው ፥ ኦሮምኛ ካልተናገረ እቃ አትግዙ ፥ ከአማራ ጋር አትጋቡ … አያሌ ጸያፍ ቃላትን ሲነገሩ ትንፍሽ ያላላችሁ አሁን “ኦሮሙማው ይውደም” የምትለዋን ቃላት ሰበብ አድርጋችሁ ከሰላሌው አህያ እረኛ ታየ ደንድኣ ጋር በመናበብ በአብን ላይ ያላችሁን ጥላቻ ለማንጸባረቅ እንጂ ኦሮሙማው ይውደም ማለት ትርጉሙ ጠፍቶዋችሁ አይደለም ፥ ኦሮሙማው ማለት የኦሮሞ ሕዝብ ሳይሆን የአማራው ሕዝብ አስገዳዮች የነአብይና ሽመልስ ርዕዮተ ዓለም መሆኑን በተደጋጋሚ ለመግለፅ ተሞክሯል ፥ ለመብላት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ናት ይሏታል እንደሚባለው በአብን ላይ ያላችሁን ጥላቻ ለመግለፅ እንጂ ሌላ አይደለም ፥ አብን’ን መጥላት የአማራን ሕዝብ መጥላት ነው ፥ የአማራን ሕዝብ እንደምትጠሉት ደግሞ በተግባር እያየን ነው ፥ ሕዝብ መፍጀት ብቻ ሳይሆን ከተማም አውድማችኋል ፥ አንድም የኦሮሞ ሕዝብ ይህንን አረመኔያዊ ተግባር ሲቃወም አላየንም ፥ የአማራ ርጉዝ ሴት ሆዷ ተቀዶ ሽል አውጥታችሁ የምትጥሉ የ21ኛው ክ/ዘመን አራዊቶች ናችሁ ፥ ይህ ያልተሰማችሁ የአብን ፀሐይ ጎንደር ላይ ጠለቀች ብላችሁ ጥላቻችሁን ለመግልፅ ለጠፋችሁ ፥ አዎ አሁንም ኦሮሙማው ርዕዮተ ዓለም የአማራ ሕዝብ ጠላት ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያውያን ጠላት ስለሆነ መጥፋት አለበት ፡፡

    Reply
  2. ነፃ ሕዝብ says

    April 23, 2021 09:12 am at 9:12 am

    ከሙክታሮቪች ኡስማኖቫ _ በጣም የሚገርመኝ አባባል “አብን የአማራን መጠቃት ለፖለቲካ ትርፍ ተጠቀመበት” ብለው የሚወቅሱ አካላት ናቸው ፡፡ አብን ማለት የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ነው ፡፡ የተቋቋመው የሚወክለው ሕዝብን መብት ሊያስከብር ነው ፥ አማራ ሲሞት ካልተናገረ ሃዲያ ለምን ተቋቋመ ? አማራን ዝም ብለን እንፍጅ ነው ? በብሄር በተደራጀ ሀገርና መንግሥት የአብን ምኑ ይደንቃል ፥ በአብን ላይ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም ፥ የአብን ጥፋት ማንም ለማይናገርለት የአማራ ሕዝብ ድምፅ መሆኑ ብቻ ነው ፡፡ አራት ነጥብ !! ለነፍሰ_ገዳዩና በአማራ ሕዝብ ደም ለሰከረው አብይ አህመድ አሊ አፈቀላጤዎቹ የጎልጉል አዘጋጆች የአብን “ፀሐይ” ጎንደር ላይ ጠለቀች ለሚለው ጋጠወጥ ሃሳብ ተጨማሪ ለጥፌላችኋለሁ @

    Reply
  3. tata says

    May 1, 2021 04:22 pm at 4:22 pm

    u trying to twist the truth

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule