• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

Left Column

በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ

April 13, 2023 03:21 am by Editor 1 Comment

በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ

የውጪና የውስጥ ደጋፊዎቹንና አይዞህ ባዮቹን፣ ለዘመናት ከኢትዮጵያ የዘረፈውን ገንዘብና የጦር መሣሪያ የተማመነው ት ህነግ በእብሪት ጦርነት ውስጥ በገባበት ወቅት የአክሱምን አየር ማረፊያ በግሬደር ማረሱ የቅርብ ጊዜ ፅታ ነው። ማሰብ የተሳነው ትህነግ ይህንን ያደረገው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና እና አየር ኃይል የአክሱምን ኤርፖርት ለጦርነቱ እንዳይጠቀሙበት በሚል የጨነገፈና ኋላቀር አስተሳሰብ ነበር። ጦርነቱ የተካሄደው ት ህነግ ፈጽሞ ባልጠበቀው፣ እነ ስዬ አብርሃ ባለቀሱበት የአየር የበላይነትና በድሮን ነበር። የአክሱም ኤርፖርት ግን ምንም ላይፈይድ ፈርሶ ቀረ፤ ሕዝቡ አሁን በውጤቱ እያማረረ ይገኛል። በከፍተኛ ደረጃ የከተማው የንግድ እንቅስቃሴ በቱሪዝም መስህቦች ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው በአጼ ዮሃንስ 4ኛ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የደረሰው ጉዳት የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ላይ … [Read more...] about በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ

April 4, 2023 10:07 am by Editor Leave a Comment

አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ

በአዲስ አበባ፣ በባህርዳር፣ በአዳማና በድሬዳዋ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችን ኢላማ ያደረገ ጥቃቶች በመፈጸም ሀገራዊ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረሐይል  አስታወቀ፡፡ የጋራ ግብረ ሐይሉ ለመገናኛ ብዙኅን  በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣  በአማራና በሌሎች ክልሎች ውስጥ መቀመጫቸውን ያደረጉ እንዲሁም አዲስ አበባ ጭምር የሚገኙ ምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶችን ያካተተ ህቡዕ መዋቅር በምስጢር ሲንቀሳቀስ እንደነበር ተደርሶበታል። ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው፣ ፕሮፌሰር ማዕረጉ ቢያበይን፣ ዶ/ር መሰረት፣ ወርቁ ተስፋዬ ወ/ማርያም፣ ተስፋዬ የኋላሸት ፋሲል፣ ሰለሞን ልመንህ ከተማና መንበረ የተባሉ ግለሠቦችም በህቡዕ አደረጃጀቱ ሲሳተፉና ሲያስተባብሩ በቁጥጥር ስር … [Read more...] about አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: amhara terrorists, ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል

April 4, 2023 09:26 am by Editor Leave a Comment

በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል

በ10 ዓመቱ ወደ ውጪ ሸሽቷል የተባለው ሀብት ከባለፈው 44 ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ10 ዓመቱ እንደሚበልጥ የጥናት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ለሸገር ነግረዋል፡፡ በጉዳዩ የማክሮ ኢኮኖሚ ተንታኝና ተመራማሪው ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ከሸገር ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፦በኢትዮጵያ በ10 ዓመት ውስጥ ብቻ 45 ቢሊየን ዶላር ከሀገር መውጣቱን ገልጸው ይህም የ10 ዓመቱን ወደ ውጪ የሸሸ ኃብት ከባለፈው 44 ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ10 ዓመቱ እንደሚበልጥ ተነግረዋል። የማክሮ ኢኮኖሚ ተመራማሪው በ44 ዓመት ውስጥ ከኢትዮጵያ የሸሸው ሀብት 31 ቢሊየን ዶላር ነው የተባለ ሲሆን፣ ይህም በጥናት ተረጋግጦ መታተሙን አንስተዋል፡፡ በተጨማሪም በከተማው ውስጥ ከመደበኛው ሥርዓት ውጪም ከፍተኛ ዶላር እንደሚገላበጥ አስረድተዋል። ለመሆኑ ዋናው ምክንያት … [Read more...] about በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል

Filed Under: Left Column, News Tagged With: illegal money, operation dismantle tplf

አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ

March 22, 2023 12:57 pm by Editor Leave a Comment

አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ

በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ ታሸጉ፤ 68 ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል። በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስነዋሪ ድርጊት እና ትውልድን በሚጎዳ ስራ ላይ የተሰማሩና ሲጠቀሙ የተገኙ 68 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማው አስተዳደር አሳውቋል። ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ በማህበረሰቡ ተቀባይነት የሌላቸው አፀያፊ ድርጊቶች ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲፈፅሙ በመገኘታቸው ቤቶቹ መታቸጋቸው ተገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እና የሠላምና ፀጥታ ቢሮ በጋራ በመሆን ትላንት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ነው ህገወጥ ተግባራት ሲፈጸምባቸው የተገኙት የምሽት ቤቶች እንዲታሸጉ … [Read more...] about አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ

Filed Under: Left Column, News, Social Tagged With: Bass Addis, Pyramid Club, SeyTan Bet, Shisha

ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ

March 22, 2023 12:06 pm by Editor Leave a Comment

ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ

የህ.ወ.ሓ.ት ከሽብርተኝነት መሰረዝ ዘላቂ ሰላምን፣ እፎይታንና ቅቡልነትን የሚያመጣ አይደለም! ኢዜማ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው «ልዩ ጉባኤ» ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት)ን ከአሸባሪነት እንደሰረዘው ማወቅ ችለናል፡፡ ኢዜማ የትኛውም አይነት በሀገራችን ላይ የሚፈጠሩ ልዩነቶች በውይይት መፈታት እንዳለባቸው በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። በህ.ወ.ሓ.ት ጸብ አጫሪነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተነሳውም ጦርነት ላይ ከዚህ የተለየ አቋም አልነበረውም፡፡ በኢዜማ እምነት ውይይት ተደርጎ ችግሮችን መፍታት የሚቻለው የሃሳብ ልዩነት ያላቸው አካላት በሙሉ ልብ ፈቃደኛ እስከሆኑ እና የመንግሥት ስልጣን በኃይል እንደማይያዝ መተማመን ሲኖር ብቻ ነው፤ ሕ.ወ.ሓ.ት እነዚህን ሃቆች ለመቀብል ሳይፈልግ ቀርቶ ጦርነትን ሲያውጅ … [Read more...] about ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ

Filed Under: Left Column, Politics Tagged With: ethiopian terrorists, ezema, operation dismantle tplf, tplf, tplf terrorist

ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው

March 19, 2023 02:44 am by Editor Leave a Comment

ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው

በኤርሚያስ ለገሰ እና በሃብታሙ አያሌው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው ውዝግብ በርካታዎችን ሲነጋግር የቆየ ነበር። በተለይ በመካከላቸው ጥል እንዳለ በግልጽ በሚታይ መልኩ በአደባባይ እየወጡ የሚናገሩት ከበስተጀርባ ምን እየተደረገ ነው የሚል ጥያቄ ብዙዎች እንዲያነሱ አድርጓቸዋል። አሁን ግን ሁኔታው ግልጽ እየሆነ የመጣ ይመስላል። በኤርሚያስ እና በሃብታሙ መካከል ሰሞኑን የታየው ልዩነት አስመልክቶ ጥቂቶቹን ቪዲዮዎች እንመልከት፤ ከዚህ ሌላ የጌታቸው ሹመት በተሰማበት ቅዳሜ ዕለት እንደተለመደው ከሃብታሙ ጋር ለውይይት መውጣት የነበረበት ኤርሚያስ አልወጣም። ሃብታሙ ከሌላ ግለሰብ ጋር ለወሬ የወጡ ሲሆን በበረከት እና ጌታቸው ሥልታዊ የካድሬ ትንታኔው የበርካታዎችን ቀልብ የሚስው ኤርሚያስ በዚህ ወሳኝ ቀን ለትንታኔ አለመከሰቱ ምናልባት ለጌታቸው “ሹመት ያዳብር” … [Read more...] about ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው

Filed Under: Left Column, Politics Tagged With: ermias legesse, Ethio 360, getachew reda, habtamu ayalew, operation dismantle tplf, tplf terrorist

ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ

March 15, 2023 08:48 am by Editor Leave a Comment

ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤን ያሰናከሉ የህግ አስፈጻሚ አካላት ላይ ፍትሕ ሚኒስቴር ክስ እንዲመሰረት ጠየቀ። በመንግስት መስሪያ ቤቶች ስር የሚተዳደሩ ስብሰባ ቦታዎች እና አዳራሾች ለፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ ክፍት እንዲሆኑም ውሳኔ አሳልፏል። ቦርዱ ይህን ያስታወቀው፤ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ ያጋጠሙ መስተጓጎሎችን በተመለከተ ዛሬ ረቡዕ መጋቢት 5፤ 2015 በአዲስ አበባው ሃይሌ ግራንድ ሆቴል በሰጠው መግለጫ ነው። በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ መሰረት፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤያቸውን ቢያንስ በሶስት ዓመት አንድ ጊዜ ማካሄድ አለባቸው። የፖለቲካ ፓርቲዎች ይህን ግዴታቸውን ለመፈጸም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ወቅት መስተጓጎል እየገጠማቸው እንደሚገኝ … [Read more...] about ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: balderas, Election Board, enat party

አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች 

March 10, 2023 10:45 pm by Editor 2 Comments

አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች 

“መዓዛን ከሕግም፣ ከዕምነትም አንጻር የሽልማቱን መሥፈርት ጠይቁልኝ" በአሜሪካ የሩሲያ አምባሳደር አናቶሊ አንቶኖቭ የዚህ ዓመቱ ደፋር ሴቶች ዓለምአቀፍ ሽልማት (2023 International Women of Courage Award) ለናዚ አባል መሰጠቱን በጥብቅ አወገዙ። አምባሳደሩ ያወገዙት ሽልማቱ ለዩክሬናዊቷ ዩሊያ ፓዬቭስካ በመሰጠቱ ነው። ከኢትዮጵያ ይኸው ሽልማት ለመዓዛ መሐመድ ተሰጥቷል። ዜናውን የተከታተሉ “ሽልማቱን ተከትሎ ወለል ብለው የሚታዩ ጉዳዮች አሉ” እያሉ ነው። ዓለምአቀፉ የሴቶች ቀን በተከበረበት ማርች 8 ቀን 2023ዓም “ደፋር ሴቶች” በመባል በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት መራጭና አቅራቢነት የተለየ ሥራ የሠሩ ሴቶች ሽልማታቸውን ከቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን ተቀብለዋል። ይህ ሽልማት ከተሰጣቸው መካከል ዩክሬይናዊቷ ዩሊያ ፓዬቭስካ … [Read more...] about አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች 

Filed Under: Left Column, News Tagged With: 2023 International Women of Courage Award

አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት

February 24, 2023 10:44 am by Editor Leave a Comment

አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት

ቢያንስ አንድ ቢሊዮን ብር ወይም ወደ ሃያ ሚሊዮን ዶላር አካባቢ የተዘረፈባቸው አውቶቡሶች የተገዙት ለዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ መሆኑ ታወቀ። ኤሊያስ ሳኒ ዑመር እና ያደታ ጁነዲን በክሪ (ብራይተን ትሬዲንግ) የመጨረሻ ተጫራች ሆነው በቀረቡበት ጨረታ ኤሊያስ ሳኒ ዑመር በኢትዮጵያ ውስጥ መኪና አስመጪነት ይቅርና በአጠቃላይ በአስመጪነት ያልተመዘገበ ድርጅት ነው። ሆኖም ለአንድ አውቶቡስ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ብር ዋጋ አስገብቷል። ባልተመዘገበ ድርጅት የተወዳደረው ኤሊያስ ሳኒ ዑመር ከፍተኛ ዋጋ አቀረበ ተብሎ 19 ሚሊዮን ብር ያቀረበው ያደታ ጁነዲን በክሪ (ብራይተን ትሬዲንግ) አሸነፈ ተብሎ ግዢውን ፈጽሟል። ከንቲባዋም የያደታ ጁነዲን በክሪ (ብራይተን ትሬዲንግን) ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል። ሆኖም ይህንን የመሰለ አደገኛ የሌብነት አሠራር ከመፈጸሙ በፊት የአውቶቡሶቹ … [Read more...] about አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት

Filed Under: Left Column, News Tagged With: Adanech Abebie, addis ababa city buses, Ethiopia corruption, mayor of addis ababa, prosperity party

በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት

February 17, 2023 06:39 pm by Editor 3 Comments

በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት

ካለፉት አራት ወይም አምስት ዓመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ የሚታየው የፖለቲካ መካረርና ጡዘት የሁለትዮሽ የተናበበ የገፊና ጎታች ሤራ (Pull and Push Conspiracy) ነው ለማለት የሚያስችሉ በርካታ ጠቋሚዎች አሉ። የዚህ ሤራ ዓላማ ሕዝብን መስዋዕት በማድረግ መስዋዕትነቱ በሚፈጥረው ቁጭትና ሐዘን ሕዝብን ስሜት ውስጥ በማስገባት ሥርዓት አፍርሶ ሥልጣን ባቋራጭ ለመጨበጥ ያለመ ነው። ለነገሩ ይህ ዓይነት የፖለቲካ አካሄድ አመጽ በተቀላቀለበት መልኩ ሁልጊዜ ባይታይም ሠለጠነ በሚባለው ዓለም የተለመደ አካሄድ ነው። ፓርቲዎች ጎራ ለይተው ይናቆራሉ፣ ይሰዳደባሉ፤ ሚዲያው ጉዳዩን የተካረረ ፖለቲካ ያደርገዋል፤ ደጋፊዎች በስሜት በመነዳት ብዙ ርቀው ይሄዳሉ፤ አታጋይ የተባሉት ፖለቲከኞች ግን አብረው ሲበሉ፣ ሲጠጡ፣ ሲሳሳቁ ይገኛሉ። “የሠለጠነ ፖለቲካ” በማለት ይህንን ድራማ ሚዲያው ሌላ ቅኝት … [Read more...] about በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት

Filed Under: Left Column, Politics Tagged With: Ethiopia, Pull and Push Conspiracy

  • « Previous Page
  • Page 1
  • …
  • Page 8
  • Page 9
  • Page 10
  • Page 11
  • Page 12
  • …
  • Page 33
  • Next Page »

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው! November 17, 2026 11:54 pm
  • “የጫካ ቱጃሮች!”— የፋኖ አመራሮች ስለተሰማሩበት የገንዘብ ዝርፊያ አስደንጋጭ መረጃ November 17, 2026 05:43 pm
  • በየወሩ 4 ሚሊዮን ብር እየተከፈለው ሀገር ሲያፈርስ የነበረው ሪፖርተር November 16, 2026 01:17 am
  • ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት November 14, 2026 12:42 am
  • የመለስ ዜናዊን ጭንብል የገፈፈው የትህነግ ሚዲያ (EMF) ምስክርነት November 13, 2026 03:32 pm
  • ትህነግ በወታደራዊና በፖለቲካዊ መስክ እንደሞተ ሁሉ በሪፖርተር በኩል የሚዲያ ግብዓተ መሬቱ ተፈጽሟል November 13, 2026 01:13 am
  • በከባድ ታክስ ማጭበርበር የሚፈለጉት አቶ አበባው ደስታ፣ አማራጭ የቴሌኮም ጌትዌይ ፕሮጀክትን ሊጠቀልሉ ነው November 12, 2026 03:50 am
  • “ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ገብቶ ሕዝብ እየገደለ ነው” የኦነግ ሸኔ (OLF/OLA) ተወካይ ጃል ጅረኛ November 10, 2026 05:12 pm
  • ከትህነግ የተማረኩና ከውጭ ሀገራት የገቡ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በቃሊቲ ለእይታ ቀረቡ November 6, 2026 03:36 pm
  • የመንግሥት ኃላፊዎች ወደ ሁርሶ የተወሰዱበት ምሥጢር November 5, 2026 12:43 pm
  • መንግሥት ሰማ፤ ሪፖርተር ተዘጋ፤ ግን ለምን? ምሥጢሩ ምንድነው? November 3, 2026 12:09 am
  • ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው October 30, 2026 08:57 am
  • ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር October 29, 2026 10:26 am
  • ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች October 28, 2026 11:00 am
  • ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ October 27, 2026 11:14 pm
  • ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው October 27, 2026 08:41 pm
  • በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ October 27, 2026 09:17 am
  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
  • ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ October 20, 2026 03:20 pm
  • ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ October 20, 2026 09:21 am
  • በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት October 19, 2026 08:58 pm
  • ዜግነት ሊያሰርዝ በሚችለው የኢልሃን ዑመር ምርመራ ላይ አዳዲስ መረጃ ተገኝቷል October 19, 2026 04:45 pm
  • በትግራይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ስም በአስቸኳይ ሊቀየር ይገባል! October 19, 2026 02:55 am
  • በትግራይ ሕዝብ ደም የሚደረገው የሥልጣን ቁማር ያብቃ! October 14, 2026 11:04 pm
Copyright © 2026 · Goolgule