• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

Left Column

የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ

December 14, 2022 02:49 pm by Editor 1 Comment

የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ

ትግራይ አሁን ያለችበት ሁኔታ እንዴት እንደደረሰችና በትህነግ የተፈጸመውን ከአእምሮ ያለፈ ግፍ ምን እንደ ሆነ በጥቂቱ ለማወቅ ይህንን ፕሮፌሰር ሐረገወይን አሰፋ የሰጡትን ቃለምልልስ መስማት የግድ ይላል። ባለ ማህተምነታቸው አንገታቸው ላይ የሚታይና ሃይማኖተኛ ነን ለማለት ቀዳሚ ተሰላፊ የሚሆኑት ትህነግ የላካቸው የትግራይ ወራሪዎች በአማራና በአፋር ክልል መነኩሴ እስከመድፈር የደረሱት ለምን ይሆን ለሚለው ጥያቄ በቂ ፍንጭ የሚሰጥ ነው ቃለ ምልልሱ። እውነተኛው የትግራይ ባሕል ሌላ ሳይሆን ይኽ ወረርሽኝ ነው። ሌላው ሥር የሰደደ ነውረኝነትን ለመሸፈን የሚሰጥ ማባበያ ነው። ትግራይ በዚህ ልክ ከሞራል ልዕልና የወረደች ሆና ትጥቅ መፍታትም ሆነ ለውጥ ማምጣት የማይታሰብ ነው። ሐረገወይን እንደሚሉት በትግራይ በተለይ በእናቶችና ሴቶች ላይ ሥርነቀል የባሕል አቢዮት ማካሄድ የግድ … [Read more...] about የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ

Filed Under: Interviews, Left Column Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, rape in tigray, tigray, tigray culture, tplf terrorist

“የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “

December 13, 2022 10:30 am by Editor Leave a Comment

“የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በተሿሚዎች፣ በተመራጮች ወይም በመንግሥት ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል። በ2002 ዓ/ም በወጣው የሀብት ማሳወቂያና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ድንጋጌ መሠረት፦* የአገሪቱ ፕሬዚዳንት፣* ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣* ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣* ሚኒስትሮች፣* ሚኒስትር ዴኤታዎች፣* ኮሚሽነሮች፣* ምክትል ኮሚሽነሮች፣* ዋና ዳይሬክተሮች፣* ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፣ እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ግዴታ ጥሎባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ ግለሰቦቹ ለኮሚሽኑ ያስመዘገቡትን ሀብት መረጃ በሚስጥር መያዝና ለሕዝብ ይፋ አለማድረግ ከአዋጁ ጋር  የሚፃረር ድርጊት እንደሆነ … [Read more...] about “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “

Filed Under: Left Column, News Tagged With: Ethiopia Institution of the Ombudsman, operation dismantle tplf

ይህ ሌብነት ሲፈጸም መዐድን ሚኒስቴር የት ነው?

December 2, 2022 12:03 pm by Editor 1 Comment

ይህ ሌብነት ሲፈጸም መዐድን ሚኒስቴር የት ነው?

በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 4 ነጥብ 18 ኪግ የሚመዝን ‹‹አኳ ማራይን ››የተባለ ማእድን ተያዘ። በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬድዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም በድሬድዋ ከተማ ባደረገው ክትትል በተለምዶ ሶስት ኪሎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 4 ነጥብ 1 ኪ.ግ የሚመዝን ‹‹አኳ ማራይን›› የተባለ ማዕድን በቁጥጥር ስር አውሏል። ህገ ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ማእድኑን ወደ ውጭ ሀገር ለማስወጣትና ለመሸጥ በዝግጂት ላይ እንዳሉ በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች፣ ሰራተኞችና በብሄራዊ መረጃ ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ኢፕድ ዘግቧል። በዚህ ህግ የማስከበር ስራ ይህንን የሃገር ሐብት ሲያዘዋውሩ የተገኙ አራት ተጠርጣዎች የተያዙ ሲሆን የተያዘው ማእድንም በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ቀጣይ … [Read more...] about ይህ ሌብነት ሲፈጸም መዐድን ሚኒስቴር የት ነው?

Filed Under: Left Column, News Tagged With: anti-corruption campaign, olf shanee, olf shine, operation dismantle tplf

በሌብነት “አደገኛ ወረርሽኝ” ላይ አገራዊ ጦርነት ታወጀ

November 17, 2022 10:25 am by Editor 1 Comment

በሌብነት “አደገኛ ወረርሽኝ” ላይ አገራዊ ጦርነት ታወጀ

የክልል መስተዳድሮችም በየደረጃው ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ተነግሯቸዋል ሙስና ሀገርን የሚበላ ነቀዝ ነው፡፡ የሀገርን አንጡራ ሀብት እየቦረቦረ ጥሪቷን ባዶ ለማስቀረት ሌት ተቀን የሚማስን ተባይ ነው። ዋልጌ ባለሥልጣናት፣ በፍቅረ ነዋይ የታወሩ ደላሎች እና ባለሃብቶች አንድ ላይ ሲገጥሙ፤ ከነዚህ የሌብነት ፊታውራሪዎች ጀርባ ብዛት ያላቸው ዜጎች መሰለፍ ሲጀምሩ ሙስና የተባለው ነቀዝ ሀገርን እንደ ወረርሽኝ ያጠቃታል፡፡ ሙስና በየትኛው ቦታና በየትኛውም ዘመን ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን የሀገርን ልማት አጥንቱ ድረስ እስከ መጋጥ ከደረሰ ሙስና አንድ አደገኛ ወረርሽኝ ሆኗል ማለት ነው፡፡ ሙስና ሀገርን ሊያፈርስ የሚችል የደኅንነት ሥጋት መሆኑን ያስመሰከሩ ሀገሮችን በዘመናችን አይተናል፡፡ የአደንዛዥ ዕጽ፣ የኮንትሮባንድ፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ንግድ፣ … [Read more...] about በሌብነት “አደገኛ ወረርሽኝ” ላይ አገራዊ ጦርነት ታወጀ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: corruption, ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

የወልቃይት-ጠገዴ ትግል መቋጫው ገና ነው

November 16, 2022 05:37 pm by Editor Leave a Comment

የወልቃይት-ጠገዴ ትግል መቋጫው ገና ነው

"እናንተ የመለስናችሁ ለእረፍት እንጂ ጥያቂያችን መቋጫ አግኝቶ ትግል ስላበቃ አይደለም ። የወልቃይት-ጠገዴ ነፍጥ ገና ይጠብቃል እንጂ አይወርድም። እኔ በዚህ እድሜዬ ጋቢ ለብሼ ከዘራ ይዤ ቤተክርስቲያን ሲሄድ ነበር የሚያምርብኝ። ነገር ግን አሁንም በዚህ እድሜዬ ጠበንጃ ተሸክሜ የምታዩኝ የወልቃይት-ጠገዴ ትግል መቋጫው ገና ስለሆነ ነው። ጥያቄው እልባት ሲያገኝ እናንተም በሙሉ ልብ ወደ ልማታችሁ እኔም ገዘራ ይዤ ጋቢ ለብሸ የምሄድ ይሆናል"ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱየወ/ጠ/ሰ/ሁ/ዞን ም/አስተዳዳሪና ሰላምና ደህንነት ሃላፊ "የወልቃይት-ጠገዴ ህዝብ ሲኖርም በምክንያት ሲሞትም በምክንያት ነው። አሁን እየተዳደርን ያለነው በምንፈልገው የቤጌምድር አማራ ማንነት ነው። በዚህም እንቀጥላለን። በህግ ጥያቄ ያለው ካለ በህግ ይጠይቀን።በህዝብ ፍላጎት መሰረት እስከሆነ ድረስ አስተዳደራችንም ድሮም … [Read more...] about የወልቃይት-ጠገዴ ትግል መቋጫው ገና ነው

Filed Under: Left Column, News Tagged With: demeke, demeke zewdu, wolkayit

ስምምነቱን በማይቀበሉ ወይም ዕንቅፋት በሚፈጥሩ ላይ አሜሪካ ዕርምጃ ትወስዳለች

November 4, 2022 04:55 pm by Editor 1 Comment

ስምምነቱን በማይቀበሉ ወይም ዕንቅፋት በሚፈጥሩ ላይ አሜሪካ ዕርምጃ ትወስዳለች

በተጀመረ በአስረኛው ቀን ይፋ የሆነውን የሰላሙን ስምምነት ማክበር ለአሜሪካ ቀዳሚ አጀንዳ እንደሆነ በተለያዩ ኃላፊነት ላይ ያሉ ባለሥልጣኖች ቢናገሩም፣ ስምምነቱ ከመፈረሙ ከቀናት በፊት የስምምነቱን ውጤት በተመለከተ አሜሪካ አስቀድማ ውጤት አመላካች የሆነ ማስጠንቀቂያዋ ከወትሮው የከረረ ነበር። ይኸው ማስጠንቀቂያ ዛሬ የተገላቢጦሽ የሚሠራ መሆኑ ደግሞ ዜናውን ትኩስ አድርጎታል።  ለትህነግ ያላትን ወገንተኝነት ያለ ኃፍረት በዓለምአቀፍ መድረኮች ስታስተጋባና አጀንዳ እየተከለች ኢትዮጵያ ላይ ጫናዋን ስታበረታ የነበረችው አሜሪካ፣ የሰላሙ ንግግር ከመጀመሩ ቀናት በፊት ውጤቱን አስመልክታ ያወጣቸውን መግለጫ ወይም አቋም ቁጣ ቀላቅለው ያስታወቁት በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ ነበሩ። ከትህነግ ጋር ቤተሰባዊ ግንኙነት እንዳላቸው በሥፋት በፎቶ … [Read more...] about ስምምነቱን በማይቀበሉ ወይም ዕንቅፋት በሚፈጥሩ ላይ አሜሪካ ዕርምጃ ትወስዳለች

Filed Under: Left Column, News, Politics Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf, tplf terrorist

የፕሪቶሪያው ስምምነት ትርጉም 360 ለዞረባችሁ

November 4, 2022 01:04 pm by Editor 2 Comments

የፕሪቶሪያው ስምምነት ትርጉም 360 ለዞረባችሁ

በመጀመሪያ ደረጃ መተማመን ያለብህ በራስህ አቅም ነው። አቅም አልባ ከሆንክ ማንም የማይፈልግህ ውዳቂ ትሆናለህ። የራስህን አቅም በሚገባ ከገመገምክ በኋላ ማን ነው አጋሬ ወደሚለው ትዞራለህ። አጋርህ ከጠላትህ እና ከአንተ ጋር ያለውን መስተጋብር ትገመግማለህ። አጋርህ ከጠላትህ ይልቅ አንተን ለምን እንደመረጠ አንተም ለምን እንደመረጥከው በተጨባጭ መረጃ ላይ ተንተርሰህ መገምገም የአንተ ድርሻ ነው። አንተም ለምን አጋርህ እንዳደረከው ማወቅ ይኖርብሃል። ታማኝ አጋር እንደምትሻ ሁሉ ለአጋርህ ታማኝ መሆንም የግድ ነው። እዚህም እዚያም የምትዘል ከሆነ ለአጋርነት አትመጥንም ብሎ ሜዳ ላይ ያሰጣሃል አንዳንዴ የጠላቴ ጠላት አጋሬ ነው የሚለው ብሂል ገዥ ነው። ዘላቂ ጠላትም ሆነ ዘላቂ ወዳጅ እንደሌለ ተረድተህ ግምገማህን በየጊዜው መተንተን ግን ከአንተ የሚጠበቅ ነው። ያልተተነተነ ፖለቲካ … [Read more...] about የፕሪቶሪያው ስምምነት ትርጉም 360 ለዞረባችሁ

Filed Under: Left Column, Opinions Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

የትህነግ ታጣቂዎችና የጦር አመራሮች የጅምላ መቃብር ስፍራ የተገኘ

October 28, 2022 09:57 am by Editor Leave a Comment

የትህነግ ታጣቂዎችና የጦር አመራሮች የጅምላ መቃብር ስፍራ የተገኘ

በመከላከያ ሰራዊት መስዋዕትነት ከህወሓት እየተላቀቁ በሚገኙት አካባቢዎች የአሸባሪው ህወሓት ድብቅ ገመና መጋለጡን ቀጥሏል። የሽብር ቡድኑ ቁንጮ አመራሮች አስገድደው በጦርነት ላሰለፏቸው ታጣቂዎች እንኳ ምንም አይነት ርህራሄ እንደሌላቸው በጨርጨር የተገኘው ጅምላ መቃብር ለዚህ ማሳያ ነው፡፡ ከጨርጨር ከተማ በስተምስራቅ በኩል በሺዎች የሚቆጠሩ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎችና የጦር አመራሮች የጅምላ መቃብር ስፍራ የተገኘ ሲሆን፥ ይህም የሽብር ቡድኑ ቁንጮ አመራሮች በትግራይ ህዝብ ደም በስልጣን ለመቆየት የማይፈነቅሉት ድንጋይ እንደሌለ ማሳያ ሆኗል፡፡ የጅምላ መቃብር ስፍራው መለያ ኮድ ያለውና በአንዳንዱ መቃብር ከ3 እስከ 5 አስከሬን በጋራ የተቀበረበት ሲሆን፥ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎቹን የቀበራቸው እንደ ኃላፊነታቸው እና ማዕረግ ደረጃቸው በመቃብራቸው ላይ ምልክቶችን በማድረግ … [Read more...] about የትህነግ ታጣቂዎችና የጦር አመራሮች የጅምላ መቃብር ስፍራ የተገኘ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf, tplf terrorist

ነገረ ወዲ ገብረ ትንሳኤ – ”አባዬ ምን በድለን ነው ህወሃት የምትቀጣን?”

October 28, 2022 09:26 am by Editor 1 Comment

ነገረ ወዲ ገብረ ትንሳኤ – ”አባዬ ምን በድለን ነው ህወሃት የምትቀጣን?”

ወደ ገደለው ስንሄድ፦ የራያው ልጅ ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ አራት ኪሎ የባዮሎጂ ተማሪ ነበረ። ከዛም ትግል ስታይሌ ነው አለና ደደቢት በረሃ ወረደ።[ውጊያ ተለማመደ]ወያኔ ከደርግ ጋራ ስትዋጋ ከጦር ፊታውራሪዎች አንዱ ሆነ፤ ፃድቃን ገብረትንሳኤ። ከገቡም በኋላ ለአስር አመታት ያህል፣ በሌተና ጀነራል ማዕረግ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የጦር ኤታማዦር ሹም (Chief of Staff) ነበረ።ፃድቃን ቀጥተኛ፣ ቅን እና ሆደ ቡቡ ነው ይሉታል የሚያውቁት።[አንዴ]የካህሳይ አብርሃን 'የአሲምባ ፍቅር' መፅሃፍን ካነበብክ፣ ያኔ ኢህአሠ አሲምባ እንደገባ በብሄር ፌድራሊዝም ጉዳይ ኢህአፓና ህወሃት ሲከራከሩ፣ ''የብሄር ፌዴራሊዝም የታክቲክ ጉዳይ ነው። ማታገያ ነው እንጂ End አይደለም'' ብሎ የሞገተ ነው። ''የትግራይ ገባር የመሬት ላራሹ ጥያቄው ስለተመለሰለት፣ አሁን መደብ ምናምን ከምንለው ጨቋኝ … [Read more...] about ነገረ ወዲ ገብረ ትንሳኤ – ”አባዬ ምን በድለን ነው ህወሃት የምትቀጣን?”

Filed Under: Left Column, Opinions Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf, tplf terrorist, tsadkan gebretinsae, tsadqan

“በመከላከያ ኃይላችን መሥዋዕትነት” የሰላም ንግግሩ ይቀጥላል – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

October 24, 2022 03:09 am by Editor Leave a Comment

“በመከላከያ ኃይላችን መሥዋዕትነት” የሰላም ንግግሩ ይቀጥላል – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቁልፍ የሚባሉ የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠሩን ቀጥሏል ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። ይህንን ሲያደርግም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በከተሞች ውጊያ ሳይደረግ የህወሓትን ወታደራዊ ዐቅም ለማሽመድመድ የሚያስችል ስልት ተጠቅሟል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰብአዊ የርዳታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ሰብአዊ ርዳታ እንዲደርስ እየሠራ ይገኛል። የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በእነዚህ አካባቢዎች አገልግሎት ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት እንዲያፋጥኑ እያደረገ ነው። ከየአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመነጋገር ሕዝባዊ አስተዳደር የሚቋቋምበትንና ማኅበራዊ አገልግሎቶች የሚጀምሩበትን መንገድ እያመቻቸ ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፍሪካ ኅብረት በኩል በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የሰላም ንግግር የሚሳተፍ ይሆናል። አጋጣሚውንም … [Read more...] about “በመከላከያ ኃይላችን መሥዋዕትነት” የሰላም ንግግሩ ይቀጥላል – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Filed Under: Left Column, News Tagged With: endf, ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf, tplf terrorist

  • « Previous Page
  • Page 1
  • …
  • Page 9
  • Page 10
  • Page 11
  • Page 12
  • Page 13
  • …
  • Page 32
  • Next Page »

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule