የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛው መስቀል አደባባይ ሲል የጠራው "ለሚ ፓርክ" የተሰኘ ግዙፍ ግንባታ ዛሬ በይፋ መጀመሩን አሳውቋል። ግንባታውን ያስጀመሩት የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ናቸው። አስተዳደሩ ፕሮጀክቱ "ብቸኛ የህዝብ አደባባይ የነበረውን የመስቀል አደባባይ የሚደግም ሁለተኛ ታላቅ ፕሮጀክት ነው" ብሏል። ፕሮጀክቱን በየመለከተ ይፋ በተደረገ መረጃ ፦ ለግንባታው 1.3 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞለታል።ግንባታው 14 ሺህ 400 ካሬሜትር ላይ የሚያርፍ ይሆናል። ለሚ ፓርክ የሚኖሩት:የህዝብ ስፍራ አደባባይ (public space) የመኪና ማቆምያ፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ ጂምናዝየሞችን፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ የህዝብ መሰባሰቢያ ስፍራ (public space)፣ የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ፣ የሰርግና ሌሎች አገልግሎቶች … [Read more...] about ሁለተኛው መስቀል አደባባይ