የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛው መስቀል አደባባይ ሲል የጠራው “ለሚ ፓርክ” የተሰኘ ግዙፍ ግንባታ ዛሬ በይፋ መጀመሩን አሳውቋል።
ግንባታውን ያስጀመሩት የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ናቸው።
አስተዳደሩ ፕሮጀክቱ “ብቸኛ የህዝብ አደባባይ የነበረውን የመስቀል አደባባይ የሚደግም ሁለተኛ ታላቅ ፕሮጀክት ነው” ብሏል።
ፕሮጀክቱን በየመለከተ ይፋ በተደረገ መረጃ ፦
- ለግንባታው 1.3 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞለታል።
- ግንባታው 14 ሺህ 400 ካሬሜትር ላይ የሚያርፍ ይሆናል።
ለሚ ፓርክ የሚኖሩት:
የህዝብ ስፍራ አደባባይ (public space) የመኪና ማቆምያ፣
የመዝናኛ ስፍራዎች፣
ጂምናዝየሞችን፣
የስብሰባ አዳራሽ፣
የህዝብ መሰባሰቢያ ስፍራ (public space)፣
የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ፣
የሰርግና ሌሎች አገልግሎቶች የሚውል መናፈሻ፣
ሱፐርማርኬት፣
የቢሮ አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎች፣
መጽሀፍት የማንበቢያ ስፍራና የመሳሰሉት ይኖሩታል፡፡
በግንባታው ወቅት እስከ 1100 ያህል ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።
በቀጣይ በቋሚነት ለ400 ዜጎች የስራ ቦታቸው ይሆናል።
ፕሮጀክቱ በ10 ወራት ተገንብቶ የሚጠናቀቅ መሆኑ ተገልጿል። (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ይስሃቅ አበበ says
ጥሩ ነገር ሲሰራ እናመስግን እናበረታታ ! አቃቂር ማሳነስ ማጥላላት የደካሞች የሰነፎች መገለጫ ነው ! እናመሰግናለን በርቱ ተበራቱ !!