• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች 

March 10, 2023 10:45 pm by Editor 1 Comment

“መዓዛን ከሕግም፣ ከዕምነትም አንጻር የሽልማቱን መሥፈርት ጠይቁልኝ”

በአሜሪካ የሩሲያ አምባሳደር አናቶሊ አንቶኖቭ የዚህ ዓመቱ ደፋር ሴቶች ዓለምአቀፍ ሽልማት (2023 International Women of Courage Award) ለናዚ አባል መሰጠቱን በጥብቅ አወገዙ። አምባሳደሩ ያወገዙት ሽልማቱ ለዩክሬናዊቷ ዩሊያ ፓዬቭስካ በመሰጠቱ ነው። ከኢትዮጵያ ይኸው ሽልማት ለመዓዛ መሐመድ ተሰጥቷል። ዜናውን የተከታተሉ “ሽልማቱን ተከትሎ ወለል ብለው የሚታዩ ጉዳዮች አሉ” እያሉ ነው።

ዓለምአቀፉ የሴቶች ቀን በተከበረበት ማርች 8 ቀን 2023ዓም “ደፋር ሴቶች” በመባል በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት መራጭና አቅራቢነት የተለየ ሥራ የሠሩ ሴቶች ሽልማታቸውን ከቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን ተቀብለዋል።

ይህ ሽልማት ከተሰጣቸው መካከል ዩክሬይናዊቷ ዩሊያ ፓዬቭስካ (Yuliia Paievska) አንዷ ነች። “ታዪራ” (“Taira”) በመባል የምትታወቀው ፓዬቭስካ ከተጀመረ ዓመት ባሰቆጠረው የሩሲያ ዩክሬይን ጦርነት ቁስለኞችን ለማከም የ“ታዪራ መላዕክት” የተሰኘ የፈቃደኛ የአምቡላንስ አገልግሎት የጀመረች ናት። ጦርነቱ እንደተጀመረ በሩሲያ ወታደሮች ተይዛ ከሁለት ወር እስር በኋላ ተለቅቃለች።

ፓዬቭስካ የዛሬ አምስት ዓመት የዩክሬይንን መከላከያ የተቀላቀለች ሲሆን በወቅቱም ስድሳ አንደኛውን (61ኛ) ተንቀሳቃሽ ወታደራዊ ሆስፒታል ስትመራ ነበር። በመቀጠል ግን ከሚሊታሪው በመውጣት የራሷን የፈቃደኛ አምቡላንስ አገልግሎት ጀምራለች።

ለዓለምአቀፍ ሚዲያ በተደጋጋሚ የዩክሬይን ቀኝ አክራሪ ጽንፈኛ ቡድኖች አባል እንደነበረች የምትናገረው ፓዬቭስካ በኒዎ-ናዚነት የሚታወቀው አዞቭ ባታሊዮን (Azov Battalion) የተሰኘው እጅግ አረመኔና ጨካኝ ገዳይ ወታደራዊ ቡድን አባል ወይም ደጋፊ ነች በማለት ሩሲያ ትናገራለች።

የተለያዩ የሩቅ ምስራቅ ታይኳዶና ጁዶ ልዩ ችሎታ ያላት ፓዬቭስካ በፈቃደኝነት የአምቡላንስ አገልግሎት የተሰማራችበት ቦታ የጽንፈኛው አዞቭ ባታሊዮን ቤዝ ባለበት ማሪፑል (Mariupol) ሲሆን በሩሲያ ቁጥጥር ሥር የዋለችውም እዚያው ነበር።

ለዚህ ዓመቱ የደፋር ሴቶች ሽልማት የበቃችውን ፓዬቭስካ የአሸባሪ ድርጅት አባል ነች በማለት ሩሲያ ትከስሳለች። ከዚያ ባለፈም የአሸባሪው አዞቭ ባታሊዮን ጦር አባል ነች በሚልም ተጨማሪ ክስ ታቀርባለች።

የፓዬቭስካን ሽልማት በተመለከተ አምባሳደሩ ሲጠየቁ የመለሱት “በነጩ ቤተ መንግሥት ግድግዳዎች ውስጥ ናዚ ሲወደስና ሲከበር ማየት እጅግ አስጸያፊ ነው” በማለት ነበር።

አምባሳደሩ ሲቀጥሉም “ምናልባት ለማታውቁ ሰዎች ፓዬቭስካ በቅጽል ስሟ ታዪራ ተብላ የምትጠራ ሲሆን ጉሮሮ ቆራጭ፣ አንገት በጣሽ እና እጇ በበርካታ አዛውንቶች፣ ሴቶች እና ሕጻናት ደም የተበከለ የዩክሬይን ወንበዴ አሸባሪ ነች” ብለዋል። “ይቺ ሴት” ይላሉ አምባሳደሩ ሲያብራሩም፤ ይቺ ሴት ማለት አሁን በሩሲያ ቁጥጥር ሥር በሆነው ማሪፑል ከተማ የሁለት ልጆችን ወላጆች ከገደለች በኋላ የልጆቹ እናት መስላና ራሷን ቀይራ ልታመልጥ የሞከረች ናት፤ በኋላ ልጆቹ ሲጠየቁ ካልተባበሩ እነሱንም እንደምትገላቸው ስላስፈራራቻቸው እሺ እንዳሏት ተናግረዋል።

የአዞቭ ባታሊዮን አባላት በ2014 (የዛሬ ዘጠኝ ዓመት) አካባቢ በዩክሬይን ሥልጣን በኃይል ለመያዝ የሞከሩ ሲሆን ከዚያ በመቀጠል በ2018 በዶንባስ ግዛት ኒዎ-ናዚዎችን ሲያሠለጥን የነበረ ድርጅት ነው። እሷም የዚያ ባታሊዮን አባል ሆና በሰብዓዊ ፍጡራን ላይ የከፋ ወንጀል ፈጽማለች በማለት አምባሳደር አንቶኖቭ ተናግረዋል።

“ሌላው መታወቅ ያለበት ጉዳይ” አሉ አምባሳደሩ “የአዞቭ ባታሊዮን ማለት ጸረ ሰው ርዕዮት የሚያራምድ መሆኑ ነው። የባታሊዮኑ መለያ ምልክት ኤስ ኤስ (SS) ተብሎ የሚታወቀው የናዚ ጀርመን ወታደሮች ምልክት ነው። ይህንን የአሜሪካ ባለሥልጣናት ያውቃሉ። በ2019 ዓም አንድ የአሜሪካ የሕዝብ እንደራሴ ይህ ባታሊዮን የውጪ አገር አሸባሪ ተብሎ እንዲፈረጅ ለስቴት ዲፓርትመንት ጥያቄ አቅርበው ነበር። አሁን ግን ሩሲያን ለመጉዳት ስትል አሜሪካ ናዚን ለማወደስና ከፍ ከፍ ለማድረግ ፈቀደች። የአሜሪካ ባለሥልጣናት “ቡናማው መቅሰፍት” ተብሎ ከሚጠራው ሕይወታቸውን ሰውተው ዓለምን ነጻ ባወጡት የአሜሪካና የሶቪየት ወታደሮች ፊት መቆም የማይችሉ ወራዳ መሆናቸውን ነው ያሳዩት” ብለዋል።

በጭከናው እጅግ የሚታወቀው የአዞቭ ባታሊዮን አባል ከሆነችው ፓዬቭስካ ጋር የደፋር ሴቶች ሽልማት ከተቀበሉ መካከል ከኢትዮጵያ መዓዛ መሐመድ ትገኛለች።

በዕለቱ ከተሸለሙት 11 ሴቶች መካከል ከአርጀንቲና የአልባ ሩዌዳ ሽልማት በማኅበራዊ ሚዲያ ውዝግብ ያስነሳ ሆኗል። በአርጀንቲና የመጀመሪያ ትራንስ (transgender) ወይም በጾታ ወንድም ሴትም ወይም ወንድ ወይዘሮ የሆነችው እንደ ሴት ተቆጥራ በሴቶች ቀን ሽልማቱ መሰጠቱ ሴቶችን “የሰረዘ ተግባር” ነው በማለት መሳለቂያ ያደረጉት አጀንዳ ሆኗል።

የአሜሪካ ፖለቲከኞች በበኩላቸውም ወቀሳቸውን አሰምተዋል። የአርካንሳ አገረ ገዢና በጾታም ሴት የሆኑት ሳራ ኸከቢ ሳንደርስ “ለዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን እንኳን አደረሳችሁ፤ ዕለቱን ዴሞክራቶች ሴት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የረሱበት ቀን አድርገን ለማክበር ጥሩ ጊዜ ነው” ብለዋል። ቅኔው ወንድና ሴት (transgender) ተሸላሚዋን ከመወረፍ ባለፈ አንድም ዴሞክራቱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በእርጅና ምክንያት ነገሮችን መርሳታቸውን የጠቆመ ሲሆን ችግሩ በዕለቱ ሽልማቱን ወደሰጡት ባለቤታቸው መሄዱን ያሳየ ሽንቆራ ነው ተብሏል።

በድንገት በዚህ ዓለም አቀፍ ሽልማት ላይ ከኢትዮጵያ “ተሸለሙ” ተብሎ ስማቸው የተጠሩ ሰዎችን አስመልክቶ የገባቸው ወዲያው፣ ያልተረዱ ዘግይቶም ቢሆን ሲገባቸው  “ሽልማቱ አሜሪካ ምን፣ ለምንና እንዴት እንደምታበረታታ የሚያሳይ ነው” በሚል ስም አንስተው በቁጭት ሲናገሩ እንደነበር ይታወሳል።

ታዋቂዋ የሬዲዮ አዘጋጅ ዳና ሎሽ ደግሞ “በዓለምአቀፉ የሴቶች ቀን ሴቶችን እያነሱ መሄድ ወይም መኮሰስ በማበረታታቸው ቀዳማይ እመቤት መልካም አድርገዋል። ሴቶችን መሰረዝ ግን አግባብ አይደለም” በማለት በጻፈችው የትዊተር መልዕክት ተሳልቃለች።

በዚሁ መነሻ ይመስላል የመዓዛን ሽልማት አስመልክቶ “አገር ቤትም ያላችሁ ሆናችሁ፣ ከአገር ውጭ የምትገኙ የሚዲያ ሰዎች መቼም መዓዛን መጋበዛችሁ አይቀርምና ሁለት ጥያቄ ጠይቁልኝ” ብለዋል።

ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ ሕግ ወንጀል፣ በኢትዮጵያ እምነቶች ዘንድ እስላም ክርስቲያን ሳይል ደግሞ የተረገመ እንደሆነ በማስታወስ የሽልማቱን መሥፈርትና ተሸካሚዎቹን አስመልክቶ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ፣ ከዛም አልፎ እንደ አንድ ሙስሊም እንዴት እንደምትመለከትው፣ በዝርዝር እንዲጠይቅላቸው በጎልጉል በኩል ጥያቄ ያቀረቡት አቶ ያሲን ሳኒ ናቸው። ይህን ያሉትም አዲስ አበባ ለሚገኘው ተባባሪ መረጃ አቀባያችን ነው።

ስቴት ዲፓርትመንት ባለፈው ዓመት በዚሁ ሽልማት ወቅት ሁለት ግብረሰዶማዊያን ወይም ደጋፊዎችን መሸለሙ ይታወሳል። ይህ በተደጋጋሚ እየታየ ያለው የሽልማት ምዘና ብዙዎችን ያነጋገረ ሲሆን “የኢትዮጵያውስ መመዘኛ ሁለት ኪሎ ጥሬ ሥጋ ጭጭ ማድረግ ይሆን?” ሲሉም ተደምጠዋል። የሩሲያው አምባሳደር አሜሪካኖቹን “ወራዳ መሆናቸውን ያሳዩበት ነው” ሲሉ የገለጹበትን አግባብ ወደ ኋላ ሄድ ብሎ የተሸላሚዎችን ዝርዝር መመልከት ለቻለ ግልጽ እንደሆነም አመልክተዋል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, News Tagged With: 2023 International Women of Courage Award

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    March 12, 2023 08:38 am at 8:38 am

    ስመ ዲሞክራሲ አናርኪ ሲፈጥር እንዲህ ነው፡፡ ሴት ሴት አደለሁም፤ ወንድ እንዲሁ ተፈጥሮውን ጠልቶ ሴት መሆን የሚሻበት የዝብርቅ አለም ውስጥ ነው ያለነው ጎበዝ፡፡ በጭራሽ ወደኋላ የምንመለስበትም መንገድ የለም፡፡ ወደፊት እነጉዳለን፡፡ እውነት ውሸት፤ ውሸቱ እውነት የሆነበት የጋሃድ አለም ከፊታችን ቁጭ ብሏል፡፡ Transgender ማለት በአጭሩ ተፈጥሮ ከሰጠው ጾታ ጋር የተጣላ ሰው ማለት ነው። ሌላው ትርጉም ሁሉ ማከያ እንጂ ማጣፈጫ አይሆንም። ያለ ቅጥ ዘምኛለሁ የሚለው የአሁኑ ዓለም ጉራውና የመንኮራኩሩ ውጤት ባንድ ቀን የሚጠፋ መሆኑን አልተረዳም። ይህን ስል ከሰማይ የመጣ ፍርድ ይህን ያረጋል ማለቴም አይደለም። የሰው ልጅ ራሱን በራሱ ነው የሚያጠፋውና። እውቁና በጣም የምወደው ኢትዮጵያዊ ሃያሲና ደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ በአንድ መድረክ ላይ እንዲህ ሲል አደመጥኩት “መጥፊያችን ደርሶአል”። ልክ ብሏል። ቀኑም ቅርብ ነው። ከ8ሺ ጋርም አይያያዝም!
    ዛሬ ሰው ከሰው መገናኘቱ ቀርቶ በሶሻል ሚዲያ ብቻ ሰዎች ነገሮችን የሚፈጽሙበት፤ ተንኮልና ንግዳቸውን የሚያከናውኑበት እንደሆነ ለሁሉ ግልጽ ነው። ሰው ለሰው መድሃኒት መሆኑ ቀርቶ በፈጠራ ዓለም ውስጥ ሰው እየተንሳፈፈ ራሱን ለመከራና ለችጋር እያጋለጠ ይገኛል። ይህ ከሰው ግንኙነት ውጭ የሆነው ጊዜአዊ የሶሻል ሚዲያ ሩጫ ደግሞ ተመልሶ በሽታ እየሆነ ሰዎችን ለተስፋ መቁረጥ፤ አልፎ ተርፎ ራስን እስከማጥፋት፤ ትዳርን እስከመናድ ደርሷል። በሚሊዪን የሶሻል ሚዲያ ተከታይ አለኝ የሚሉን የንዋይ ፍቅረኞች ያጠራቀሙትን ገንዘብ በውሉ ሳይጠቀሙበት ራሳቸውን የሚያጠፉት ዓለም ስለማትጣፍጣቸው እንጂ በረሃብ ተጎድተው አይደለም።
    እንሆ አሁን ደግሞ ከሰው የላቀ እሳቤ የሚያደርገው ChatGTP, Augmented Reality, Virtual reality, DeepFake etc… ዓለምን የበለጠ እንደሚያመሳቅሏት እውን ነው። የሰው ልጅ እውነትና ውሸትን መለየት የማይችልበት ደረጃ ላይ ይደርሳል። እየተቃረበም ነው። በዘመነ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ የድሮን አዋጊ የሆነው ፓይለት ቀኑን ሙሉ ሰው በድሮን ሲገል ውሎ ያለምንም ሰዋዊ ስሜት ሥራውን ጨርሶ ወደ ሚስቱና ልጆቹ የሚሄደው ሥራውን እንደ ኮምፒውተር ጫወታ ስለሚያየው ነው። አሁን የዘመነው ዓለም ከመግደሉና ከገደለህ በህዋላም በፊልም ቀርጾ አሟሟትህን ያሳያል። የደነዘዘ ትውልድ እየፈጠርን ነው። እርግጥ ነው የሰው ልጅ ባህሪ አራዊቶችን ይመስላል። በአንደኛውና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የታየው ክፋት ለዚ ቋሚ ምስክር ነው። የዛሬውን ጭካኔ ካለፈው የሚለየው ሟች እና ገዳይ በተለያየ ምቾት ላይ መሆናቸው ነው። የቀበሮ ጉድጓድ ውጊያ እያከተመለት በመሆኑ በሩቅ ሆኖ መወራወር ሆኗልና! የወደፊቱ ውጊያ ሰውም አይኖርበት። ውጊያው በኮምፒውተር እየታገዘ በሮቦቲክ ቴክኖሎጂ የሚፈጸም ይሆናል። ጊዜው እየመሸ ነው። ሰው ግን ዝም ብሎ ይንጋጋል። ቆም ብሎ ከየት ተነስተን ወዴት እየሄድን ነው በማለት የሚጠይቅ የለም። ቆሞ ተሳፋሪ በሚጠይቀው ባቡር ላይ ሁሉም ይሳፈራል። መውረጃ ጣቢያውንና የት ላይ እንደሚቆም ግን አያውቅም። ስለዚህ የአሜሪካ መንግስት እንዲህ ያለ ዓይን ያወጣ ቅጥፈት የሚፈጽመውም ለፓለቲካ ትርፍ እንጂ ለሌላ አይደለም። በሴቶች ቀን ጾታው ለተማታበት ሽልማት መስጠቱ የፓለቲካ ገበጣ ጫወታ ነው። ልብ ላለው ጫወታው ጠጠር አልባ መሆኑ ነው። ለዚህ ነበር የሃገሬ ገጣሚ “ሊቃውንት አዋቂ ከሆናችሁማ በሉ ቀን ቁጠሩ ሳይመጣ ጨለማ” በማለት ያላዘነው። ግን የማን ጀሮ ሰምቶ ይታዘዛል። ልብ ያለው በዚህ ዘመን ጸጥ፤ ረጭ ባለ ሁኔታ ላይ ሆኖ ራስን ይመረምራል። እንደተባረከች ደሮ ለንዋይና ለቀሪ ሃብት መንደፋደፉ ትርፉ ድካምና ከንቱነት ይሆናልና። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm
  • “ሙሽራው እስኪመጣ የምትቆይ ቤተክርስቲያን እናድርጋት” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ February 15, 2023 03:13 pm
  • በመዝገበ ቃላት የችጋር መጠሪያ የነበረችው ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስንዴ ወደ ውጭ ላከች February 13, 2023 03:28 am
  • ውዝግቡን በሐዋሪያት መንገድ ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷል February 10, 2023 09:06 am
  • የሚከተልህ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም – መልዕክት “ለመንፈሳዊው ቄሮ” መሪ ዘመድኩን በቀለ! February 10, 2023 12:48 am
  • በሰማዕትነት ጥሪ ቤተመንግሥቱን ባቋራጭ መቆጣጠር February 9, 2023 01:25 pm
  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule