ሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ 2.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣውን፤ በ4 ወራት ይጠናቀቃል የተባለውን እና 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ በዓመት ማምረት ይችላል ተብሎ የተነገረለትን የማዳበሪያ (የዩሪያ) ፋብሪካ ለመገንባት ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር ስምምነት ሲፈረም በሰጡት አጭር መግለጫ ፋብሪካው እንደ ዓባይ ግድብ እንደማይሆን ተናግረው ነበር። ይህ ፕሮጀክት “በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚመራ ስራቴጂክ ፕሮጀክት ነው፤ በከፍተኛ ዲሲፒሊንና ቁጥጥር የሚደረግ ነው፤ እንደ ሕዳሴ ግድብ ሜጋ ፕሮጀክት ነው፤ ሕዳሴ ላይ የነበረው ስህተት እዚህ አይደገምም፤ በጥንቃቄና በጥናት የተጀመረ ፕሮጀክት ነው፤ በዕውቀትና በጥንቃቄ ብቻ ነው የሚመራው፤ ምክንያቱም አንድ ፕሮጀክት መጀመራችን ሳይሆን በጥንቃቄ ካልመራነው ተጨማሪ ኃብትና ጊዜ ስለሚያባክን እንደዚህ ዓይነት ስህተት … [Read more...] about ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው
Archives for August 2025
መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ
* “ዓለም እያዘነብን እየሳቀብን ነው አንድ እንሁን” - ዘመነ ካሤ አርበኛ ዘመነ ካሴ “ዓለም እያዘነብንም እየሳቀብንም ነው” በማለት “መተው ነገሬን ከተተው" እንደሚባለው በመተው "አንድ እንሁን" የሚል ጥሪ አሰማ። ፋኖ ኢትዮጵያን ሠርቶ ምስራቅ አፍሪካን ያረጋጋል ብሏል፤ አንድነት ለመፍጠር “አንድ ማንኪያ ቅንነት” ነው የሚያስፈልገው አለ። በጎጃም እና በደቡብ ጎንደር የተሰማራው የአገር መከላከያ በበኩሉ ስም፣ ቦታና ኃላፊነት ጠቅሶ በፋኖ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አስታውቋል። የዘመነ መልዕክት የተሰራጨው የመከላከያ መረጃዎች እኩል ቀን ነሐሴ 16 በሪፖርት መልክ ይፋ ከሆነ በኋላ ነው። "የዕለቱ መልዕክት" በሚል የአማራ ፋኖ በጎጃም መሪ ዘመነ ካሴ "በቃ መተው እንልመድ" ሲል የተለያዩትን የፋኖ አመራሮችና አደረጃጀቶች ዘርዝሮ " ... አንድ መሆን አለበት" … [Read more...] about መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ
ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው
* ከደመቀ መኮንን ጋር የተበቀ ግንኙነት ያላቸው ባለሃብቶች መመለስ “ከዚያስ” አስብሏል * ባለሃብቶቹ በፋኖ ስም ለሚንቀሳቀሰው ሚዲያ በሙሉ “ዩኤስኤይድ” ናቸው በውል የሚታወቁ የጎጃም ባለሃብቶች ከፋኖ ጋር በተያያዘ አስቀድመው ሀገር ለቀው መውጣታቸው ይታወሳል። እነዚሁ ክፍሎች ናቸው ወደ አገራቸው ለመመለስ እንቅስቃሴ ማድረጋቸው የተሰማው። ከቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያላቸው የጎጃም ባለሃብቶች ተመልሶ ወደ አገር ቤት መግባት “ከዚያስ?” የሚል ጥያቄ አስነስቷል። በፋኖ ስም የሚንቀሳቀሰውን ሚዲያ በመደገፍ የሚታወቁትና “የሚዲያው ዩኤስኤይድ” በሚል ቅጽል ስም የሚጠሩት ባለሃብቶች ከተመለሱ የብዙዎቹ የሚዲያ እንቅስቃሴዎች የሚከስም ይሆናል ተብሏል። ወደ አገር ቤት ለመመለስ እየተንቀሳቀሱ ያሉት ባለሃብቶች ከፋኖ ጀርባ ሆነው በፋይናንስና … [Read more...] about ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው
የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ
* ይግባኝ ለማለት ወደ ፖለቲካው መመለስ የግድ ሆኖበታል በአሜሪካ የጥገኝነት ማመልከቻ ያስገባው አቶ በቀለ ገርባ የስደት ፈቃድ ማመልከቻው ውድቅ ተደረገ። በድጋሚ እንዲታይለት ይግባኝ መጠየቁም ታውቋል። ዳግም ወደ ፖለቲካ ተሳትፎ የተመለሰውም በዚህ ሳቢያ እንደሆነ ተመልክቷል። ከእስር ከተፈታ በኋላ ምስጋና ለማቅረብ ወደ አሜሪካ ከጃዋር ጋር ያመራው አቶ በቀለ በምስጋና ጉዞው ወቅት ከአቶ ጃዋር ሲራጅ መሐመድ ጋር ባለመግባባት መለያየቱና ይህ አለመግባባት አዲስ አበባ እያሉ የተጀመረ እንደነበር ጉዳዩን የሚያውቁ ማስታወቃቸው አይዘነጋም። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በግል እና በፓርቲ ደረጃ ተሳታፊ የነበረው አቶ በቀለ ገርባ ከፓርቲው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በመልቀቅ በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቁን ይፋ ያደረው ራሱ በቢቢሲ በኩል ነበር። ወደ አሜሪካ ከመጣ … [Read more...] about የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ
ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ
ሰሞኑን ሞዐ ተዋሕዶ አየሩን ሞልቶታል። በተለይ በቅርቡ ከሞዐ ተዋሕዶ አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ፋንታኹን ዋቄ የሰጡት ቃለ ምልልስ ወደኋላ ሄደን ብዙ ነገሮችን እንድንዳስስ የሚያስደርግ ሆኗል። የዛሬ ሦስት ዓመት በቀነኒሳ ሆቴል ዶ/ር ወንደሰን በሚመራው ስብሰባ መግለጫ በሰጡበት ወቅት የተናገሩትና ሰሞኑን የተሰማውን ጉዳይ ባጭሩ ለማስቀመጥ እንሞክራለን። ይህንን በማድረግም የሞዐ ተዋሕዶን ሁኔታ ለየት ባለ ሁኔታ ለማየት እንሞክራለን፤ እንደተባለው ሞዐ ሃሳብ የሚያመጣና ወደ ሕዝቡ የሚያሰርጽ ንቅናቄ ነው? ወይስ ሌላ ተልዕኮ አለው? የሚለውን በንጽጽር እናያለን። የዛሬ ሦስት ዓመት አካባቢ በቀነኒሳ ሆቴል ከተካሄደው የሞዐ ተዋሕዶ ስብሰባ በኋላ የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ከሶስት የሞዐ ተዋሕዶ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጎ ነበር። በውይይቱ የተገኙት መምህር ገብረመድኅን እንየው፣ … [Read more...] about ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ
የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?
የሃይማኖትና የመንግሥትን መጣመር የሚደግፉም ሆነ ጥምረታቸውን በጽኑ የሚቃወሙ ጠንካራ የመከራከሪያ ነጥቦችን ያነሳሉ። ይህ ዘመናትን ያስቆጠረ ክርክር ባለንበትም ዘመን ሠለጠነ ከሚባለው ዓለም እስከ አገራችን የመወያያና የመከራከሪያ አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል። ይህ አጭር ጽሑፍ በሁለቱ ጽንፎች መካከል የሚካሄደውን ክርክር ለማቅረብ ወይም ለአንዱ ለመወገን ያሰበ ሳይሆን የሁለቱ ጥምረት ምን ውጤት አመጣ? ታሪክስ ምን ያስተምረናል? የሚለውን በጣም በጥቂቱ ለማንሳት ነው። ለማሳያነትም የክርስትና እምነትና መጽሐፍ ቅዱስ የምንጠቀም ሲሆን ይህ ማለት ግን ስለ ሌሎች ሃይማኖቶች ታሪክ ምንም አይልም በሚል እንዳይወሰድ አደራ ለማለት እንወዳለን። የሦስቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች አባት የሚባለው አብርሃም ይኖርበት ከነበረው ባቢሎን (የከለዳውያን ዑር) ወይም ያሁኗ ኢራቅ አካባቢ እግዚአብሔር … [Read more...] about የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?






