በኦሮሚያ በየጊዜው እያጋጠመ ለሚገኘው የህይወትና ንብረት ውድመት በህወሓት ጁንታና ተላላኪዎቹ የሚፈፀም መሆኑንና ይህንንም ለማስወገድ ብሎም የቡድንን ዕድሜውን ለማሳጠር በ‹ጂ ፒ ኤስ› ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ እያከናወነ መሆኑን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መምሪያ አስታወቀ። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መም ሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር እንዳለ ቁምላቸው ለበሪሳ ጋዜጣ እንደገለፁት፤ የህወሓት ጁንታ እና የኦነግ ሸኔን ሴራ ለማክሸፍና ዕድሜ ለማሳጠር ‹‹ጂ ፒ ኤስ›› ቴክኖሎጂ እየተጠቀመ መሆኑን አብራርተዋል። እነዚህ አካላት ዜጎችን ለምን እንደሚገድሉ እን ደማያውቁ በመጠቆም በህግ ቁጥጥር ሥር ለማዋልም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል። ቴክኖሎጂው እነዚህ አካላት ያሉበትን ቦታ ለመከታተል የሚያስችል እንደሆነም አመልክተዋል። በዚህ ቴክኖሎጂ … [Read more...] about የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው
olf shanee
ከኦነግ ሸኔ ጀርባ ህወሃት መሪውን የያዘው መሆኑ ታወቀ
“ከኦነግ ሸኔ ጀርባ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) መኖሩን የሚያሳዩ መረጃዎች በፖሊስ ተደርሶባቸዋል” ሲሉ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ገለጹ። ጀኔራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ የደረሰውን ጥቃት በተመለከተ ከትላንት በስቲያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው እንዳመለከቱት፤ “በህወሃት ስልጠና ተሰጥቷቸው በኦሮሚያ ክልል ሽብር እንዲፈጽሙ ከተላኩት መካከል የተያዙ ሰዎች እንዳሉ አረጋግጠናል” ብለዋል። ድምጸ ወያኔ ቲቪ እና ኦኤንኤን ቲቪ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ዘገባዎች በመስራት ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል። የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ሃይል ባለፉት ሁለት ዓመታት በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች የመንግስት ሰራተኞችን፣ አመራሮችን፣ ነጋዴወችን ጨምሮ በንጹ ዜጎች ላይ ግድያ ሲፈጽም መቆየቱን አስታውሰዋል። አሁንም … [Read more...] about ከኦነግ ሸኔ ጀርባ ህወሃት መሪውን የያዘው መሆኑ ታወቀ
የተረሳው የኢሬቻ ግፍና ከህወሓት ጋር የተዘለቀው ፍቅር እሽሩሩ
የዛሬ አራት ዓመት የኢሬቻን በዓል ለማክበር በወጣው ሕዝብ ላይ ያኔ ምኒልክ ቤተመንግሥት የነበረው አሁን መቀሌ ሆቴል የመሸገው ሕወሓት የተሰኘው የበረኻ ወንበዴዎች ቡድን ያደረሰው እጅግ ሰቅጣጭ ግፍ ፈጽሞ የሚዘነጋ አይደለም። ዓመት ባለፈ ቁጥር ይህንን የግፍ ናዳ ስናስብ ተመሳሳይ ዕልቂት በአገራችን እንዲፈጸም የሚሹ የዚህ ዓመቱን ኢሬቻ ክብረበዓል በሰላም መጠናቀቁን በፍጹም የፈለጉት አልነበረም። ሆኖም ፍጹም ሰላም በሰፈነበት መልኩ በዓሉ ተጠናቅቋ። ዓመታት አልፈው ያኔ የደረሰውን ግፍ ዘንግተው፤ ለኦሮሞ እንታገላለን የሚሉ ከህወሓት ጋር “ፍቅር እሹሩሩ” ማለታቸው ሕዝብን መናቅና መስደብ ብቻ ሳይሆን በቁሙ መግደልም ነው። ከሁሉ በላይ ለኦሮሞ ሕዝብ እታገላለሁ የሚለው በቀለ ገርባ ህወሓት ያደረሰበት ግፍና ስቅየት (ቶርቸር) ረስቶ መቀሌ በመሄድ ከህወሓት ሹሞች ጋር ስብሰባ … [Read more...] about የተረሳው የኢሬቻ ግፍና ከህወሓት ጋር የተዘለቀው ፍቅር እሽሩሩ
ቪኦኤና ጀርመን ድምጽ – የክልሎችን ኅልውና እንደ ህወሓት እየጣሱ ነው
በተለይ ካለፉት ሦስት ወራት ወዲህ የአሜሪካና የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ብሎ የሚጠራውን መቀሌ የመሸገውን የወንበዴዎች ስብስብ (ትህነግን) እያገለገሉ ስለመሆኑ ከሚያቀርቡት ያልተመጣጠነ መረጃ መረዳት አያዳግትም። ለዚህም ይመስላል የተጠቀሱት ሚዲያዎች በተለይም የጀርመን ድምጽ ተቃውሞ እየቀረበበት ይገኛል። የጎልጉል የአዲስ አበባ መረጃ አቀባይ እንዳለው “አለቃና ተቆጣጣሪ ያለ አይመስልም” ሲል በተጠቀሱት ሚዲያዎች ከሚሰሩ ዜና አቅራቢዎች ጋር ቅርብ መሆኑንን የጠቀሰ አስተያየት ሰጪ እንደነገረው ይገልጻል። የአንድ ጋዜጣ ኤዲተር እንደነበር ገልጾ አስተያየት የሰጠው ባለሙያ “ሚዲያዎቹ አንዳንድ ጊዜ የሚያቀርቧቸው፣ በተለይም ከክልል ሪፖርተሮቻቸው የሚተላለፉት መረጃዎች ያስደነግጡኛል። ሁሉም እንዳሻቸው ሪፖርት የሚያቀርቡና የኤዲተሮች ሚና የሚታይባቸው … [Read more...] about ቪኦኤና ጀርመን ድምጽ – የክልሎችን ኅልውና እንደ ህወሓት እየጣሱ ነው
“ኦነግ ሸኔ የህወሓት መጠቀሚያ ዕቃ ነው” ታዬ ደንደኣ
የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ፍሬ እንዳያፈራ ትልቁ ተግዳሮት የነበረው ኦነግ ሸኔ መሆኑን የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደኣ አስታወቁ። ህወሓት ኦነግ ሸኔን በአደባባይ እንደ ጠላት እየፈረጀ በተግባር ግን የኦሮሞን ትግል ለማክሰም እንደ መሣሪያ ይጠቀምበት እንደነበረም አመለከቱ። አቶ ታዬ ደንደኣ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ያካሄደው የፍትህ የእኩልነትና የነፃነት ትግል ፍሬያማ እንዳይሆን ኦነግ ሸኔ ከህወሃት ጋር የነበረው ከሕዝብ የተሰወረ ህብረት ዋንኛ ምክንያት ነው ብለዋል። ኦነግ ሸኔ የኦሮሞ ታጋዮች አንድ ወጥመድ ሆኖ ለህወሃት ሲያገለግል እንደነበርም አመልክተዋል። ብዙዎች ኦነግ ሰፊ የሕዝብ ድጋፍ እያለው የዚህ ድርጅት ትግል ለምንድን ነው ወደፊት ገፍቶ የማይመጣው? የሚል ጥያቄ ነበራቸው። … [Read more...] about “ኦነግ ሸኔ የህወሓት መጠቀሚያ ዕቃ ነው” ታዬ ደንደኣ