በነሐሴ ወር ብቻ በተወሰደ ወታደራዊ ኦፕሬሽን 180 የሸኔ አባላት መደምሰሳቸውን በመከላከያ ሰራዊት የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ አሰታወቀ። የዕዙ የኋላ ደጀን አሰተባባሪ ኮለኔል ግርማ አየለ እንደገለጹት፣ በተያዘው ወር ቡድኑ ይንቀሳቀስባቸው በነበሩ ምዕራብ ጉጂ፣ ምሥራቅ ጉጂ እና በቦረና ዞኖች በተካሄደ አራት ወታደራዊ ዘመቻዎች 180 አባላቱ ሲደመሰሱ 94ቱ ቆሰለዋል፣ 2ቱ ደግሞ ተማርከዋል። እርምጃው ከተወሰደባቸው የሠራዊት አባላቱ ወስጥ የህወሓት የሽብር ቡድን ያሰለፋቸው ታጣቂዎች መገኘታቸውንም ኮለኔል ግርማ አስረድተዋል። በወታደራዊ ዘመቻው የተማረከው የሼ አባል ሞርከታ ጎበና በሸኔ ጉዳይ አሰፈፃሚዎች ተመልምሎ ኬንያ ሀገር ስልጠና ወስዶ መመለሱን እና በስሩ 50 የሸኔ ሚሊሻዎችን ይመራ እንደነበር ለኢቲቪ ገልጿል። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት … [Read more...] about በነሐሴ ወር ብቻ 180 የሸኔ አባላት ተደምስሰዋል
olf shanee
ለትህነግና ሸኔ ገንዘብ ሲያስተላልፉና ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ሲፈጽሙ የነበሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ለአሸባሪዎቹ የህወሓትና ሸኔ ቡድኖች በተለያዩ ህገወጥ መንገዶች ገንዘብ ሲያሰባስቡና ሲያስተላልፉ የነበሩ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ አሻጥር በመፈጸም ህብረተሰቡን ለአመጽ ለማነሳሳት ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩ በአዲስ አበባ 51 እንዲሁም በአፋር ክልል 6 በድምሩ 57 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡ ግብረሃይሉ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤አዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች ተሰማርተው ከአሸባሪዎቹ ህወህትና ሸኔ ቡድን ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት በመፍጠር በህገወጥ መንገድ ገንዘብ ሲያሰባስቡና ሲያስተላልፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ ማስረጃዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ አንድ አንድ ተጠርጣሪዎች በህግ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በመሰማራት ለሸብርተኛው … [Read more...] about ለትህነግና ሸኔ ገንዘብ ሲያስተላልፉና ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ሲፈጽሙ የነበሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ
አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ህወሓት መደምሰስ አለባቸው፡- ዶ/ር ዓለሙ
በወሎ ግንባር የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ህወሓት ለኢትዮጵያ የማይጠቅሙ በመሆናቸው መደምሰስ አለባቸው ብለዋል። የወያኔ እና ሸኔ ጥምረት ለኦሮሞና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ነው ያሉት ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ትህነግም ሸኔን በአንድ ላይ መደምሰስ አለባቸውም ነው ያሉት። የሸኔና የህወሓት ጋብቻ አዲስ ሳይሆን ህወሓት መንግሥት ሆኖም ሳለ ኦሮሞን ለማተራመስ ሲፈልግ ሸኔን ይመሩት እንደነበር ነው ያስታወሱት። አሸባሪው ህወሓት በግንባር ጀግንነት እንደሌለው የገለጹት ዶክተር ዓለሙ ለሚያሠራጨው የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ጆሮ ሳይሰጥ ህብረተሰቡ እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል። አሸባሪው ህወሓት ወጣቶችን በሀሽሽ እያደነዘዘ እየላከ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ብዙ የአሸባሪው … [Read more...] about አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ህወሓት መደምሰስ አለባቸው፡- ዶ/ር ዓለሙ
“ሸኔ ኦሮምኛ የሚናገር አሸባሪ ህወሓት ነው”
አሸባሪው ህወሓትን ለማጥፋት የሚደረገው ትግል በአሸባሪው ሸኔ ላይም ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደአ አሳሰቡ። አቶ ታዬ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ አሸባሪው ህወሓትም ሆነ ሸኔ ለሀገር እና ለህዝብ ጠንቅ በመሆናቸው አሸባሪው ህወሓትን ለማጥፋት የሚደረገው ትግል ሁሉ በአሸባሪው ሸኔ ላይም በተመሳሳይ መልኩ ሊተገበር ይገባዋል። የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎቹ ወንድሞቹ ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለመጠበቅ፣ ሉዐላዊነቷን ለማስከበር፣ ብልጽግናዋን እውን ለማድረግ መረባረብ ይገባዋል። የቡድኖቹ በጋራ ለመንቀሳቀስ መስማማት ‹‹በግልጽ አብረን ስንሰራ ነበር፣ ኦሮሞን ስናሰቃይ፣ ኢትዮጵያ ላይ ወንጀል ስንፈጽም የነበረው በጋራ ነው፣ ወንጀሎቹ ሁለታችንንም እኩል ይመለከቱናል የሚል መልዕክት አለው›› … [Read more...] about “ሸኔ ኦሮምኛ የሚናገር አሸባሪ ህወሓት ነው”
ዓለምአቀፉ አሸባሪ ትክክለኛ ስሙን አገኘ
ድልድይ በማፍረስ፤ መሠረተ ልማቶችን በማውደም ከየቦታው በተለቃቀሙ ወንበዴዎች መሪነት ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም በግፍ ሲገዛ የነበረው ህወሃት/ትህነግ ዛሬ ትክክለኛ ስሙን አገኘ። ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው። ከዚህ በታች የሚገኘው መረጃ በዓለምአቀፉ የአሸባሪዎች ቋት ተመዝግቦ የሚገኝ የህወሃት ወንጀል ዝርዝር ነው። የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ “ህወሓት” እና “ሸኔ” … [Read more...] about ዓለምአቀፉ አሸባሪ ትክክለኛ ስሙን አገኘ
“በተለምዶ ‘ሸኔ’ የሚባለው ራሱን ‘የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት’ ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው”
በርካቶች 'ሸኔ' እያለ እራሱን የሚጠራ ድርጅት በሌለበት እንዴት አሸባሪ ተብሎ ይሰየማል ሲሉ ይጠይቃሉ። ይህ ስያሜ አንዳች ነገር ለመሸፈን ተፈልጎ ነው በሚል ጥርጣሬያቸውን የሚገልፁ ምሁራንም አልጠፉም። ለመሆኑ 'ሸኔ' ማነው? በዚህ ጉዳይ ላይ በዛሬው ዕለት የተጠየቁት የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዮስ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል፦"በተለምዶ 'ሸኔ' የሚባለው እራሱን ደግሞ 'የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት' ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው። በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በሌሎችም ክልሎች እየተንቀሳቀሰ ጥቃት የሚያደርስ ድርጅት ነው። እራሱ ለእራሱ የሰጠውን ስያሜ ግን እኛ የምናፀድቅበት ምክንያት የለንም፤ ተገቢም አይሆንም ብለን እናምናለን። ይህ ቡድን ከዚህ በፊት እንደ 'ህወሓት' ተመዝግቦ፣ ህጋዊ እውቅና፣ ህጋዊ ሰውነት እና ሰርተፊኬት ኖሮት የሚያውቅ አይደለም፤ … [Read more...] about “በተለምዶ ‘ሸኔ’ የሚባለው ራሱን ‘የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት’ ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው”
ሸኔ የሚባል የፖለቲካ ፓርቲ የለም፣ ህወሃትና ሸኔ አሸባሪ መባላቸው ለውጥ አያመጣም፤ መረራ ጉዲና
ውሳኔ ከመዘግየቱ በስተቀር ተገቢ ነው፤ የህግ ባለሙያዎች የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ተቀዳሚ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ መንግስት “ሸኔ” እና “ህወሓት” ቡድንን በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ለማድረግ መዘጋጀቱ መሰረታዊ ለውጥ አያመጣም ብለዋል፡፡ እንዲህ አይነት ፍረጃ የቀድሞ መንግስትም ሲያደርገው የነበረ ነዉ የሚሉት ፕሮፌሰሩ፣ ይህ ዓይነቱ ፍረጃ መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ቢሆን እዚህ ደረጃ ላይ አንደርስም ነበር፤ ይህም ተግባር ቀድሞ ከነበረው መንግስት የተለየ ነው ብዬ አላስብም ብለዋል ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፡፡ “ሸኔ የሚባል የፖለቲካ ፓርቲ የለም፣ በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን በተዘዋዋሪ መጥራት ይመስለኛል የሚሉት ፕሮፌሰር መረራ በዚህ ስም ራሱን የሚጠራ ድርጅት በሌለበት፣ መንግስት ግን በኦሮሚያ አካባቢ በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን ኢላማ … [Read more...] about ሸኔ የሚባል የፖለቲካ ፓርቲ የለም፣ ህወሃትና ሸኔ አሸባሪ መባላቸው ለውጥ አያመጣም፤ መረራ ጉዲና
መንግሥት ካልደረሰልን አሁንም ግድያ ይኖራል – ነዋሪዎች
በምዕራብ ወለጋ ዞን በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። ግድያው የተፈጸመው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እያለ መሆኑን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ “እኛ የፖለቲካ ሰዎች አይደለንም፤ ገበሬዎች ነን ፤ መንግስት ለምን አይደርስልንም?” ብለዋል። በኦሮሚ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል ወረዳ፣ ቦኔ ቀበሌ፣ ትናንትናምሽት 3 ሰዓት ላይ በርካታ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን የአካባቢ ነዋሪዎችየተናገሩት። ነዋሪዎቹ ፤ አሁን ላይ አስክሬኖች በየቦታው ተጥለው መገኘታቸውን ገልጸው ቁጥሩ ምን ያህል ነው የሚለውን ለመግለጽ አስቸጋሪ እንደሆነ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል። ሕጻናትና ሴቶች አሁን ላይ ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ጫካዎች መግባታቸውንየገለጹት አስተያየት ሰጭዎቹ፤ መንግስት የማይደርስላቸው ከሆነ አሁንም ሌላግድያ ሊኖር እንደሚችል ስጋታቸውን … [Read more...] about መንግሥት ካልደረሰልን አሁንም ግድያ ይኖራል – ነዋሪዎች
ቪኦኤ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ለተጨፈጨፉ ኦነግ ሸኔን ከደሙ ንጹህ አደረገ
ቪኦኤ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል ጃል መሮ በሚል ስም የሚታወቀውን ሽፍታ ሽፋን ሲሰጠው ስለምንነቱና በትክክልም እሱ ስለመሆኑ መረጃ ሰጥቶ አያውቅም። በቢቢሲ አማርኛና በቪኦኤ እንዳሻው ጊዜ መርጦ ወንጀሉን የሚያስተባብለው ጃል መሮ፤ ሲያሻው የሰጠውን ቃለ ምልልስ ስልክ ደውሎ እንዳይተላለፍ የሚያዝ ለመሆኑ ናኮር መልካ “ጃል መሮ ቃለ ምልልሱ እንዳይተላለፍ በጠየቁት መሠረት ትቼዋለሁ” ሲል ያረጋገጠው ሃቅ ነው። ቀደም ሲል በሃጫሉ ግድያ ኦነግ ሸኔ እጁ እንዳለበት በመታወቁ እጅግ የተቆጣውን ህዝብ ለማብረድ በናኮር መልካ አመቻችነት የቪኦኤ ዘጋቢ የሆነችው ጽዮን ግርማ ጃል መሮ በሬዲዮ ጣቢያው ቀርቦ ሳይፈተን እንዲፈነጭና ሃጢያቱን እንዲያራግፍ ፈቅዳለት እንደነበር ይታወሳል። ቢያንስ ማንነቱን መጠየቅ ሲገባ፣ ንጹሃንን በየቦታው እያደፈጠ ለሚጨፈጭፍ ሽፍታ፣ ሚዲያውንም ሌላ ጫካ በማድረግ … [Read more...] about ቪኦኤ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ለተጨፈጨፉ ኦነግ ሸኔን ከደሙ ንጹህ አደረገ
በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ
በጋምቤላ ክልል የኦነግ አባላት ናችሁ በሚል እና ህወሀትን ትረዳላችሁ በሚል የታሰሩ ዜጎች በአፋጣኝ እንዲፈቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አሳሰበ። ኮሚሽኑ በጋምቤላ ክልል የእስረኞች አያያዝ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ሊሻሻል እንደሚገባም አሳስቧል። ኮሚሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በጋምቤላ ክልል ያለው የእስረኞች አያያዝ እና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት ሊረጋገጥ ይገባል ብሏል። ኮሚሽኑ በታኅሣሥ ወር በጋምቤላ ከተማ እና በአኝዋህ ዞን በመገኘት፣ በአካባቢው ስላለው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ክትትል አድርጎ ከክልሉ ኃላፊዎች ጋር መወያየቱን ገልጿል። ኮሚሽኑ በጎበኛቸው የክልሉ ማረሚያ ቤቶች በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች አያያዝና ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ሁኔታ በአፋጣኝ ሊሻሻል የሚገባው ነው። በተለይም በኦነግ … [Read more...] about በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ