
አሸባሪው ህወሓትን ለማጥፋት የሚደረገው ትግል በአሸባሪው ሸኔ ላይም ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደአ አሳሰቡ።
አቶ ታዬ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ አሸባሪው ህወሓትም ሆነ ሸኔ ለሀገር እና ለህዝብ ጠንቅ በመሆናቸው አሸባሪው ህወሓትን ለማጥፋት የሚደረገው ትግል ሁሉ በአሸባሪው ሸኔ ላይም በተመሳሳይ መልኩ ሊተገበር ይገባዋል።
የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎቹ ወንድሞቹ ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለመጠበቅ፣ ሉዐላዊነቷን ለማስከበር፣ ብልጽግናዋን እውን ለማድረግ መረባረብ ይገባዋል።
የቡድኖቹ በጋራ ለመንቀሳቀስ መስማማት ‹‹በግልጽ አብረን ስንሰራ ነበር፣ ኦሮሞን ስናሰቃይ፣ ኢትዮጵያ ላይ ወንጀል ስንፈጽም የነበረው በጋራ ነው፣ ወንጀሎቹ ሁለታችንንም እኩል ይመለከቱናል የሚል መልዕክት አለው›› ብለዋል።
በመሆኑም ሕዝቡ ሸኔ ኦሮምኛ የሚናገር አሸባሪ ህወሓት ነው የሚለውን እሳቤ ተገንዝቧል፣ አሸባሪ ህውሓት ነኝ ያለው እራሱ ሸኔ ነው፤ በዚህም ማንነቱ ለሕዝቡ ግልጽ ሆኖለታል። ኦሮሞን ሲያጋጭ የነበረው ሸኔ ህወሓትን ወክሎ እንደነበር አሁን የአደባባይ ሚስጥር ሆኗል ሲሉ ገልጸዋል።
ኦሮሞን ከሌሎቹ ወንድሞቹ ጋር እንዲጣላና ግጭት ውስጥ እንዲገባ ያደረገው አሸባሪው ህወሓት ነው፤ ጉዳዩን የፈጸመው ደግሞ አሸባሪው ሸኔ ነው፣ በመሆኑም ሸኔና ህወሓት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን ህዝቡ አሁን በግልጽ ሊገነዘበው እንደሚገባ አመልክተዋል። (ኢብኮ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply