
በነሐሴ ወር ብቻ በተወሰደ ወታደራዊ ኦፕሬሽን 180 የሸኔ አባላት መደምሰሳቸውን በመከላከያ ሰራዊት የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ አሰታወቀ።
የዕዙ የኋላ ደጀን አሰተባባሪ ኮለኔል ግርማ አየለ እንደገለጹት፣ በተያዘው ወር ቡድኑ ይንቀሳቀስባቸው በነበሩ ምዕራብ ጉጂ፣ ምሥራቅ ጉጂ እና በቦረና ዞኖች በተካሄደ አራት ወታደራዊ ዘመቻዎች 180 አባላቱ ሲደመሰሱ 94ቱ ቆሰለዋል፣ 2ቱ ደግሞ ተማርከዋል።
እርምጃው ከተወሰደባቸው የሠራዊት አባላቱ ወስጥ የህወሓት የሽብር ቡድን ያሰለፋቸው ታጣቂዎች መገኘታቸውንም ኮለኔል ግርማ አስረድተዋል።
በወታደራዊ ዘመቻው የተማረከው የሼ አባል ሞርከታ ጎበና በሸኔ ጉዳይ አሰፈፃሚዎች ተመልምሎ ኬንያ ሀገር ስልጠና ወስዶ መመለሱን እና በስሩ 50 የሸኔ ሚሊሻዎችን ይመራ እንደነበር ለኢቲቪ ገልጿል።
ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተወሰደባቸውን ፈጣን ኦፕሬሽን መቋቋም ተስኗቸው አብዞኞቹ ሲደመሰሱ እሱ መማረኩን ተናግሯል።
በዚህም ሸኔ እንኳን ኦሮሚያን ነፃ ሊያወጣ በአመራር ደረጃ ተግባብቶ እና ተማምኖ የማይሠራ ቡድን እንደሆነ ማረጋገጥ መቻሉን ገልጿል።
የኦሮሚያ ወጣቶች ለማይጨበጥ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ጆሮ ባለመስጠት ቡድኑ በኦሮሚያ ንፁሃን ላይ የሚፈፀመውን ግፍ ለማስቆም እንዲታገሉ ምርኮኛው ጥሪ አቅርቧል። (ኢብኮ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply