• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ

January 25, 2021 03:07 pm by Editor 1 Comment

በጋምቤላ ክልል የኦነግ አባላት ናችሁ በሚል እና ህወሀትን ትረዳላችሁ በሚል የታሰሩ ዜጎች በአፋጣኝ እንዲፈቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አሳሰበ። ኮሚሽኑ በጋምቤላ ክልል የእስረኞች አያያዝ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ሊሻሻል እንደሚገባም አሳስቧል።


ኮሚሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በጋምቤላ ክልል ያለው የእስረኞች አያያዝ እና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት ሊረጋገጥ ይገባል ብሏል።

ኮሚሽኑ በታኅሣሥ ወር በጋምቤላ ከተማ እና በአኝዋህ ዞን በመገኘት፣ በአካባቢው ስላለው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ክትትል አድርጎ ከክልሉ ኃላፊዎች ጋር መወያየቱን ገልጿል።

ኮሚሽኑ በጎበኛቸው የክልሉ ማረሚያ ቤቶች በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች አያያዝና ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ሁኔታ በአፋጣኝ ሊሻሻል የሚገባው ነው።

በተለይም በኦነግ ሸኔ አባልነት ተጠርጥረው በጋምቤላ ከተማ ማረሚያ ቤት ከታኅሣሥ መግቢያ ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙ ሁለት የ 11 እና የ 12 ዓመት ሕፃናት ወንዶች፣ እንዲሁም አንድ የ14 ዓመት ሕፃን ሴት በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቀቁ አሳስቧል።

በተጠርጣሪዎች ሕፃናት ወንዶች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ያደረሱ የፀጥታ አባላት ላይ አፋጣኝ ምርመራ በማካሄድ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድም ኮሚሽኑ ጠይቋል።

ይህ ሪፖርት እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ሕጻናቱ በእስር ላይ መሆናቸውን ገልጿል።

በተጨማሪም “ሕወሓትን በገንዘብ እና በተለያየ መንገድ ይረዳሉ፣ በክልሉ ውስጥ በሕዝብ መካከል ግጭት የመቀስቀስ ዓላማ ይዘው ተንቀሳቅሰዋል” በሚል ምክንያት፣ ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በአቦቦ ከተማ፣ በአኝዋህ ዞን ማረሚያ ቤት 20 ሰዎች፤ እንዲሁም በጋምቤላ ከተማ ማረሚያ ቤት 70 ሰዎች፣ በአጠቃላይ በአብዛኛው የትግራይ ተወላጅ የሆኑ 90 ሰዎች፣ በክልሉ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ።

በኢሰመኮ ጉብኝት ወቅት፣ በእነዚህ 90 ተጠርጣሪዎች ላይ በፌዴራል ፖሊስም ሆነ በክልሉ ፖሊስ በኩል የተጀመረ የወንጀል ምርመራ ሂደት አለመኖሩ በመገለጹ፣ ኮሚሽኑ ይህንኑ አሳሳቢ ጉዳይ ለሚመለከታቸው የክልሉ ኃላፊዎች አሳውቆ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በአፋጣኝ ምርመራ እንዲጀመርና የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲለቀቁ አሳስቧል።

ይህ ሪፖርት እስከወጣበት ጊዜ ድረስም እነዚህ ዜጎች በእስር ላይ የሚገኙ መሆናቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል፣ ኮሚሽኑ በጉብኝቱ ወቅት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችን አነጋግሯል።

ኢሰመኮ ያነጋገራቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች ‘የምርጫ ሥነ ምግባር መግባቢያ ሰነድ’ የፈረሙ መሆናቸውን ገልጸው፣ ቢሮና የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ለማግኘት፣ በክልሉ ልዩ ልዩ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ ለመስራትና፣ የፓርቲያቸውን ዝግጅቶችን ለማድረግ እንግልት እንደሚገጥማቸውና በአንዳንድ አባላቶቻቸው ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ መድረሱን እንደገለጹለት ኮሚሽኑ በመግለጫው ጠቁሟል።

በተጨማሪም አንድ የፖለቲካ ፓርቲ በተለያየ ወቅት 35 አባላቱ በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ለእስር መዳረጋቸውን ገልጿል።

እንዲሁም የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባል ቤተሰብ በመሆናቸው ከመንግስት ስራ የታገዱ እና ያለፈቃዳቸው ‘ለብልጽግና ፓርቲ መዋጮ’ በሚል ከደሞዛቸው ላይ የመዋጮ ክፍያ የተቆረጠባቸው ሰዎች መኖራቸውን አስረድተዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በክልሉ የሚገኙ የምርጫ ወረዳ ተወካዮች ብዛት አወሳሰን ዙሪያ ያላቸውን ቅሬታ ለክልሉ ባለሥልጣናት ቢያሳውቁም፣ ምላሽ አለማግኘታቸውንም ለኮሚሽኑ አሳውቀዋል።

ኢሰመኮ በእነዚህና ሌሎችም የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ ከክልሉ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በተወያየበት ወቅት፣ የክልሉ ኃላፊዎች ለሰብአዊ መብቶች መሻሻል በጎ ምላሽ ሰጥተው፣ በተለይም የገዢው ፓርቲ አባል ካልሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ላይ ሲሰበሰብ የነበረው የፓርቲ አባልነት ክፍያ በተመለከተ አስፈላጊው የእርምት እርምጃ እንደተወሰደ ገልጸዋል። (ኢትዮ ኤፍ ኤም)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, News, Politics Tagged With: Gambella, olf shanee, olf shine, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    January 27, 2021 10:00 am at 10:00 am

    ነገሩ በሃበሻ ምድር የተገላቢጦሽ ነው እያለን ለዘመናት የኖረነው ከምናየውና ከምንሰማው ተነስተን ነው። አልፎ ተርፎም ኑረንበት ነበርና ነው። ግን የሚሰማ የለም። በመሰረቱ ሃበሻ ሲባል ምቀኛ፤ ተጠራጣሪ፤ በሁለት ቢለዋ የሚበላ አንድም ነገር ከአፉ የማይደርስ ለሌላውም እንዳይደርስ በምቀኝነት የሚንቀሳቀስ ህዝብ የሚበዛባት ምድር ናት። ሰው እያለቀሰ ስለ ህዝብ መበደል ሲናገር የሚስቁ፤ የሚቀልድ በብሄራቸው ካለሆነ በስተቀር የሰው ህይወት ምንም የማይመስላቸው ድርቡሾች የፈሉባት ሃገር ናት። በቆንጨራና በእሳት፤ በጥይትና በግርግር ሰውን እያፈናቀለና እየገደለ ዙሮ ተመልሶ ራሱ መልሶ ማቋቋም ይልና እርዳታው እጅ ሲገባ ይነግድበታል። ባጭሩ ስብዕና የሌላቸው የዘርና የክልል አውሬዎች የሚራወጡባት ይህች የሃበሻ ምድር ገና እልፍ ፈተና ይጠብቃታል። ቀልደኛው የወያኔ ካድሬ እንዳለው ነው። “እኔ ሱዳንና ግብጽ የሚያደርጉትን የህግ ማስከበር ዘመቻ በሙሉ ልቤ እደግፋለሁ” ይህ አይነት አስተሳሰብ እኔ ካልኖርኩ እሳት ይብላው በመሆኑ ዝርፊያው ግድያው መፈናቀሉ፤ በተገኘው ሚዲያ ላይ መዘነጣጠሉ ሁሉ ይቀጥላል። ሙት ይዞ ይሞታልና! ልፊያው አያባራም።
    የሰው ልጅ ሰቆቃ ሙዚቃው ከሆነ ወገን ጋር እንዴት ነው ስለ ፍትህና ስለ አብሮነት መስራት የሚቻለው? የደነዘዘ ትውልድ ቢቆነጥጡት አይሰማም። ጫቱ፤ ሲጋራው፤ ዝሙቱ (ሴት ከሴት/ወንድ ከወንድ ጭምር)፤ ያበለዘው አዕምሮ የዛሬን እንጂ የነገን ማየት አይችልም። በየከተሞቹ በሴት እህቶቻችን ላይ የሚፈጸመው ግፍ ለዚህ ዋንኛ ማሳያ ነው። አባት ልጅን እናት ልጆቿን፤ ልጆች ወላጆቻቸውን የሚክድበትን ዘይቤ እያየን ነው። የክልል ፓለቲካ የዘር ተኮር እይታ ገና ስንቶችን አይን ያጠፋል። ለጉራ የሰው ዘር መገኛ እያልን እናቅራራለን። የሰው ልጅ ማፈሪያ ብንል ይሻል ነበር። አሮጊቶችን በእሳት፤ በጥይት፤ በስለት እንደ እንስሳ የሚገድል የውጭና የውስጥ ቅጥረኛ በሚራወጥባት ምድር ስለ ሰው ልጆች መብትና ነጻነት በመድረክ ላይ ቢለፉት ዋጋ ቢስ ነው።
    አሁን በጋምቤላ ወያኔንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱ መጠየቁ ከሴራው ጋር የቀኑ አለቆች ምን ያህል ትስስር እንዳላቸው አመላካች ነው። አዙሪቱ በወረፋ የዛሬን ገዳይና አስገዳይ፤ የዛሬን የአደባባይ ደስኳሪዎችና አራጊ ፈጣሪዎች መልሶ አፈር ያለብሳቸዋል። ታሪካችን የሚያሳየው ይህኑ ነው። ጉረኞችና ያለ እኛ ማን አለ የምንል መሆናችን ዋናው ማሳያ የወያኔ በአለቀ ሰአት የሰሜኑን ጦር ማጥቃት ነው። ልብስ ያወለቀ የአማኑኤል እብድ እንኳን አያስበውም። ግን አረጉት፤ ተደረጉ፤ እየተደረጉም ነው። የሃበሻው ፓለቲካ አዙሪት ነው የምለውም ለዛ ነው። በዚሁ የግል ሽኩቻና ቀዳዳ ሱዳንና ግብጽ ሌሎችም የፓለቲካ ወሬ አናፋሾች እሳት ጭረው እየቆሰቆሱ መከራችን ያራዝሙታል። እኛም አውቀን ሳንታለል በዘርና በቋንቋ ተሰልፈን እያገዝናቸው ነው። ኦ በዚህ የስርግብ ትግል ግን አትራፊ አይኖርም። ትላንት ሻቢያንና ወያኔን በማስታጠቅና መጠለያ በመስጠት ሃገሪቱ እንድትፍረከረክ ያደረጉት እነዚያ ሃይሎች ከሞላ ጎደል የኢትዮጵያን ግባዕተ መሬት አሁን ይሻሉ። የውጭ ሃይልን መክቶ የውስጥን ለማረጋጋት አንድ መሆን አስፈላጊ ነበር። ግን በወያኔ የ 45 ዓመት ሴራ ዛሬ አንድነት የለም። በቋንቋዬ ካልተናገርክ እቃ አልሸጥም የሚል ደንቆሮ ያለበት ሃገር ላይ ተቀምጦ ሰለ ህብረ ብሄራዊነት ማውራት አይቻልም። ብቻ ሃበሻ ለራሱም ለሃገርም በውጭ ያለውም ሆነ በሃገር ያለው አይጠቅምም። ምቀኛ ነው። እሳቱ አናቱ ላይ ካልወጣ በስተቀር የሌላው ጉዳት ጉዳቱ አይደለም። አዎን 100 ሚሊዪን ህዝብ በላይ አላት የምትባለው ይህች ምድር ላይ የሚርመሰመሰው ሁሉ አንድ ነው እያልኩ አይደለም። ግን ዝምታም ከክፋት ጋር እንደመተባበር ይቆጠራል። የዘር፤ የጎሳ፤ የቋንቋ ፓለቲካ እስካልሞተ ድረስ ሃገሪቱ በውጭ ሃይሎችና በውስጥ አጥፊዎች በእሳት መለብለቧ አያቋርጥም። የፓለቲካው ጡዘት መልክና ስሙን እየቀየረ ይነጉዳል፤ በመንገድ ላይ ያለውንም ይጠርጋል። ሰው በሰውነቱ መሰላቱ ቀርቶ በዘረፈው ሃብትና በዘሩ ይተመናል። ጥቂቶች ፈንጭተው እልፎች እያለቀሱባት ያለች ሃገር ላይ ሰላምና መረጋጋትን እናስከብራለን ማለት ከጅምሩ ዋሾ መሆን ነው። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule