በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሕገ-ወጥ የወርቅ ምርትና ግብይት ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ 29 የውጭ ሀገራት ዜጎች እና ሁለት ኢትዮጵያውያን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢዜአ በላከው መግለጫ መንግሥት በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ የሰላም መደፍረስ እና የጸጥታ ሥጋቶችን ለመቀልበስ ትኩረት እያደረገ በነበረበት ወቅት በሕገ-ወጥ የማዕድን ምርትና ዝውውር የተሰማሩ አካላት በሀገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎችና አሸባሪ ቡድኖች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር በኢኮኖሚው መስክ አስተዋፅዖ ባላቸው የማዕድን ምርቶች በተለይም በወርቅ ላይ ያተኮረ ዝርፊያ ሲፈጽሙ መቆየታቸውን አስታውቋል፡፡ የማዕድን ዘርፉ በሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የነበረው ድርሻ እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ … [Read more...] about በወርቅ ዝርፊያ የተሰማሩ 28 ቻይናውያን፣ 2 ኢትዮጵያውያንና 1 ሱዳናዊ ተያዙ
ethiopian terrorists
የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ካወጣው ዘገባ በተቃራኒ በወልቃይት ጠገዴ ትግራዮች በሰላም እየኖሩ ነው
በወልቃይት ጠገዴ ንፁሃን የትግራይ ተወላጆች በሰላምና በፍቅር እየኖሩ መሆናቸውን ምስክርነታቸው ሲሰጡ ቆይተዋል። እኚህ እናት ወሮ ፀጋ ካህሳይ ይባላሉ። ከትግራይ ወደ ወልቃይት ጠገዴ ማይካድራ ከተማ ከመጡ 50 ዓመት እንዳስቆጠሩ ይናገራሉ። እሳቸው ሲናገሩም "በእነዚህ ረዥም ዓመታት ውስጥ ሃብትና ንብረት አፍርተን ልጆችን ወልደን ከብደንና ከብረን ከወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጋር ኖረናል። ነገር ግን ጥቅምት 24/02/2013 ዓ.ም ሳምሪ የተባሉ ሰዎች በዕድሚያችን በሙሉ አይተነው ሰምተነው በማናውቀው ዘግናኝ ግፍና ጭፍጨፋ በማይካድራ የአማራ ተወላጆች መፈፀማቸውን በአይናችን አይተን ምስክርነታችንን ሰጥተናል” ብለዋል። እኚህ እናት እውነትን በመናገራቸው ክብር ይገባቸዋል! በነገራችን ላይ ወ/ሮ ፀጋ ካህሳይ የተባሉት እኒህ እናት የመለስ ብስራት ወላጅ እናት ናቸው። መለስ … [Read more...] about የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ካወጣው ዘገባ በተቃራኒ በወልቃይት ጠገዴ ትግራዮች በሰላም እየኖሩ ነው
ጌታቸው ረዳ ባለፈው ሳምንት በትግራይ ካድሬና ነዋሪዎችን ሰብስቦ ከተናገረው በጥቂቱ
አትሸወዱ! የትግራይ ደህንነት(Security) ከእጃችን አልወጣም። ያ ሲባል ግን መቼም ቢሆን ጦርነትን ምርጫ አናደርግም። በሆነ አጋጣሚ ጦርነት የግድ ከሆነና appetite ካለን ግን ማን ያግደናል? ሰራዊታችን እንደሆነ ከኛ ጋር ነው ያለው። ትጥቅ በመፍታትና መሳሪያ በማስረከቡ ዙሪያ ላይ ምንም መደናገር አያስፈልግም። እነሱ የፈለጉት ሌላ ነበር። የሆነው ሌላ ነው። በዚህ ዙሪያ ብዙ መናገር አልፈልግም -sensitive material ነው። እርግጥ በትጥቅ ማስፈታት ዙሪያ የሚሰሩ የቴሌቪዢን ፕሮግራሞችን ሲመለከቱ ስጋት የሚገባቸው አንዳንድ የኛ ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ። አሁን ለምሳሌ መንግስት ደብዳቤ ሲፅፍልን "የትግራይ አካታች ጊዜያዊ መንግስት" እያለ ነው የሚፅፍልን። ይሄ ለምን ሆነ? የትግራይ ጊዜያዊ መንግስት ለምን አልተባለም? ስንላቸው "አይ ካቢኔው ከበፊቱ … [Read more...] about ጌታቸው ረዳ ባለፈው ሳምንት በትግራይ ካድሬና ነዋሪዎችን ሰብስቦ ከተናገረው በጥቂቱ
ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ
በመንግሥትና በኦነግ ሸኔ ወይም ኦነግ መካከል ሲካሄድ የከረመው የመጀመሪያ ምዕራፍ የተባለ ንግግር መጠናቀቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሑሴን ቅድሚያ ወስደው ይፋ አድርገዋል። የጎልጉል ታማኝ የመረጃ አቀባዮች እንደሰሙት መንግሥት “አልቀበልም” ያለውና ያላስማማው ጉዳይ ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ ያቀረበው ጥያቄ ዋናው ነው። ከመንግሥት ተደራዳሪዎች በኩል ቃል በቃል ምን ምላሽ እንደተሰጠ ባይገልጹም ዜናውን ያቀበሉን እንዳሉት ከሆነ መንግሥትም ሆነ አቀራራቢዎቹ አካላት በዚህ ጉዳይ ላይ የያዙት አቋም ተመሳሳይ ሆኗል። ጥያቄው ሚዛን የሚደፋና አሁን ላይ ሊነሳ የማይችል እንደሆነ ቀደም ሲል የኦነግ ከፍተኛ አመራር የነበሩ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው። የኦፌኮው ሊቀመንበር መረራ ጉዲና ገና ከጅምሩ ኦነግን በሚቃወሙት አፍላ ጊዜያቸው “ኦሮሞ … [Read more...] about ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ
በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው
ጦርነት ባሕላችን ነው፣ ተራራ ያንቀጠቀጠ ትውልድ፣ ወዘተ በሚሉ ባዶ ዲስኩሮችና ከንቱ ልፈፋዎች ትውልድን በስሁት ትርክት ሲነዳ የኖረው ትህነግ የሚፈራው ጥያቄ እየቀረበለት ነው። "ልጆቻችን የት ናቸው?" "ልጆቻችንን መልሰን ማግኘት እንፈልጋለን" ወዘተ የሚሉ የወላጆች ጥያቄ በትግራይ እየተሰማ ነው። አቶ ገብረመስቀል አበበ የተባሉት ሌላኛው ነዋሪም የአንድ ወንድ ልጅ አባት ሲሆኑ “ከአንድ ቤት አንድ ሰው ወደ ጦርነት መግባት አለበት፣ ካልሆነ እርዳታ አይሰጠውሙ” በተባለ ጊዜ አንዱ ልጃቸው በግዳጅ ወደ ውጊያ ማምራቱን በሀዘን ድባብ ውስጥ ሆነው ነግረውናል። አሁን በተደረሰው ስምምነት መሰረት “ልጄ ከዛሬ ነገ ይመጣል እያልኩ በሀዘንና በተስፋ እገኛለሁ” የሚሉት አቶ ገብረመስቀል ልብ በሚሰብር ሁኔታ እያለቀሱ ልጄ ካለ መንግስት ምላሽ ይስጠኝ ሲሉ … [Read more...] about በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው
በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ
የውጪና የውስጥ ደጋፊዎቹንና አይዞህ ባዮቹን፣ ለዘመናት ከኢትዮጵያ የዘረፈውን ገንዘብና የጦር መሣሪያ የተማመነው ት ህነግ በእብሪት ጦርነት ውስጥ በገባበት ወቅት የአክሱምን አየር ማረፊያ በግሬደር ማረሱ የቅርብ ጊዜ ፅታ ነው። ማሰብ የተሳነው ትህነግ ይህንን ያደረገው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና እና አየር ኃይል የአክሱምን ኤርፖርት ለጦርነቱ እንዳይጠቀሙበት በሚል የጨነገፈና ኋላቀር አስተሳሰብ ነበር። ጦርነቱ የተካሄደው ት ህነግ ፈጽሞ ባልጠበቀው፣ እነ ስዬ አብርሃ ባለቀሱበት የአየር የበላይነትና በድሮን ነበር። የአክሱም ኤርፖርት ግን ምንም ላይፈይድ ፈርሶ ቀረ፤ ሕዝቡ አሁን በውጤቱ እያማረረ ይገኛል። በከፍተኛ ደረጃ የከተማው የንግድ እንቅስቃሴ በቱሪዝም መስህቦች ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው በአጼ ዮሃንስ 4ኛ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የደረሰው ጉዳት የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ላይ … [Read more...] about በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ
አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ
በአዲስ አበባ፣ በባህርዳር፣ በአዳማና በድሬዳዋ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችን ኢላማ ያደረገ ጥቃቶች በመፈጸም ሀገራዊ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረሐይል አስታወቀ፡፡ የጋራ ግብረ ሐይሉ ለመገናኛ ብዙኅን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በአማራና በሌሎች ክልሎች ውስጥ መቀመጫቸውን ያደረጉ እንዲሁም አዲስ አበባ ጭምር የሚገኙ ምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶችን ያካተተ ህቡዕ መዋቅር በምስጢር ሲንቀሳቀስ እንደነበር ተደርሶበታል። ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው፣ ፕሮፌሰር ማዕረጉ ቢያበይን፣ ዶ/ር መሰረት፣ ወርቁ ተስፋዬ ወ/ማርያም፣ ተስፋዬ የኋላሸት ፋሲል፣ ሰለሞን ልመንህ ከተማና መንበረ የተባሉ ግለሠቦችም በህቡዕ አደረጃጀቱ ሲሳተፉና ሲያስተባብሩ በቁጥጥር ስር … [Read more...] about አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ
ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት!
በትግራይ፥ "ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ" የሚለው በግነት የተሞላ ትርክት ከራሱ ከትርክቱ መነሻ ጋር ሦስት ትውልድ በልቷል። አያት፣ አባትና ልጅን የሕይወት ዘመን የአካል ጉዳተኛ አድርጓቸዋል። በትጥቅ ትግሉ፣ በባድመ ጦርነት እና በአሁኑ ጦርነት አያት፣ አባትና ልጅ አካለ ጎደሎ የሆኑበት የትግራይ ፖለቲካ ሙሉ ትራጀዲ ለኢትዮጵያም የተረፈ መሆኑ ይሰመርበት። ዛሬ በትግራይ ያለ አካለ ጎደሎ 'የጉዳት መቼት' ለማወቅ 'የደርጉ ነው ወይስ የብልጽግናው?' እንዲህ ያደረገህ ብሎ መጠየቅ ግድ የሚልበት ሁኔታ ተፈጥሯል። አያት፣ አባትና ልጅ አካለ ጎደሎ ለመሆን ያበቃቸውን፤ ከአማራ፣ አፋርና ኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም አፋሳሽ ቅራኔ ውስጥ የከተታቸውን የእብደት ፖለቲካቸውን መርምሮ ለመከለስ/ለማረም ከመነሳሳት ይልቅ ዛሬም ለአራተኛ ዙር ጦርነት ምልመላ፣ ልምምድና ስልጠና ላይ ናቸው። … [Read more...] about ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት!
“ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን
የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በዛሬው የምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ወቅት ፤ "የሰላም ስምምነቱ ቀሪ ጉዳዮች ቢኖሩም ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል" ሲሉ መናገራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል። ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት በአብላጫ ድምፅ ተሰርዟል። ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ / ህወሓት / ከሽብርተኛ ድርጅትነት በተሰረዘበት የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ ላይ 280 የፓርላማ አባላት ተገኝተው ነበር። 61 የፓርላማ አባላት ተቃውመው ድምፅ ሰጥተዋል ከተገኙት የፓርላማ አባላት መካከል 61 የፓርላማ አባላት ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት መሰረዙን ተቃውመው ድምፅ ሰጥተዋል። 5 የፓርላማ አባላት ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል። በዚህም በአብላጫ_ድምፅ ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት ይነሳ የሚለው … [Read more...] about “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን
ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ
የህ.ወ.ሓ.ት ከሽብርተኝነት መሰረዝ ዘላቂ ሰላምን፣ እፎይታንና ቅቡልነትን የሚያመጣ አይደለም! ኢዜማ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው «ልዩ ጉባኤ» ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት)ን ከአሸባሪነት እንደሰረዘው ማወቅ ችለናል፡፡ ኢዜማ የትኛውም አይነት በሀገራችን ላይ የሚፈጠሩ ልዩነቶች በውይይት መፈታት እንዳለባቸው በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። በህ.ወ.ሓ.ት ጸብ አጫሪነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተነሳውም ጦርነት ላይ ከዚህ የተለየ አቋም አልነበረውም፡፡ በኢዜማ እምነት ውይይት ተደርጎ ችግሮችን መፍታት የሚቻለው የሃሳብ ልዩነት ያላቸው አካላት በሙሉ ልብ ፈቃደኛ እስከሆኑ እና የመንግሥት ስልጣን በኃይል እንደማይያዝ መተማመን ሲኖር ብቻ ነው፤ ሕ.ወ.ሓ.ት እነዚህን ሃቆች ለመቀብል ሳይፈልግ ቀርቶ ጦርነትን ሲያውጅ … [Read more...] about ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ










