ትግራይ አሁን ያለችበት ሁኔታ እንዴት እንደደረሰችና በትህነግ የተፈጸመውን ከአእምሮ ያለፈ ግፍ ምን እንደ ሆነ በጥቂቱ ለማወቅ ይህንን ፕሮፌሰር ሐረገወይን አሰፋ የሰጡትን ቃለምልልስ መስማት የግድ ይላል።
ባለ ማህተምነታቸው አንገታቸው ላይ የሚታይና ሃይማኖተኛ ነን ለማለት ቀዳሚ ተሰላፊ የሚሆኑት ትህነግ የላካቸው የትግራይ ወራሪዎች በአማራና በአፋር ክልል መነኩሴ እስከመድፈር የደረሱት ለምን ይሆን ለሚለው ጥያቄ በቂ ፍንጭ የሚሰጥ ነው ቃለ ምልልሱ።
እውነተኛው የትግራይ ባሕል ሌላ ሳይሆን ይኽ ወረርሽኝ ነው። ሌላው ሥር የሰደደ ነውረኝነትን ለመሸፈን የሚሰጥ ማባበያ ነው።
ትግራይ በዚህ ልክ ከሞራል ልዕልና የወረደች ሆና ትጥቅ መፍታትም ሆነ ለውጥ ማምጣት የማይታሰብ ነው። ሐረገወይን እንደሚሉት በትግራይ በተለይ በእናቶችና ሴቶች ላይ ሥርነቀል የባሕል አቢዮት ማካሄድ የግድ ይላል። በእርሳቸው አነጋገር የጉዳዩ ሰለባ ብቻ ሳይሆን የጉዳቱም ምንጭ ናቸው።
ይህንን ምስክርነት እያንዳንዱ መስማት ብቻ ሳይሆን ሌሎችም እንዲሰሙ የማድረግ የሞራል ኃላፊነትና ግዴታ አለው።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Tesfa says
በእድሜ ዘመኔ ካነበብኳቸው አያሌ መጽሃፍቶች ውስጥ ጥቂቶቹ ፈገግ ሲያሰኙኝ የቀሩት ደግሞ ራሴን እንድፈትሽ አስገድደውኛል። የቀሩት ደግሞ የሰውን አውሬነት አጉልተው በማሳየት እግዚኦ ይኸም አለ አስብለውኛል። ግን በአለማችን ላይ ምን ያለሆነ ነገር አለ? የዚህች ዓለም ችግር ሰው ራሱ ነው። አሁን ደግሞ ይባስ ተብሎ ቁጥራችን ያለ ልክ እየተራባ ይኸው እንሆ በዚህም በዚያም አዲስ ሰበብ እየፈለግን እንራኮታለን፤ የመግደያውን መሳሪያም ዘመናዊ ከማድረጋችን የተነሳ በክብ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ ቡናውን ወይም ሌላውን ነገር እየተጋተና እያኘከ ሰውን በጅምላ ገድሎ የቅምጥ የሚፎክርበት ጊዜ ላይ ቆመናል። የምችለው ስጠኝ የሚሉት አባቶች የማይታመን ገመና ሲያዪ ነው።
ፕ/ር ሃረገወይን የምትለው ለእኔ ይገባኛል። ችግሩ በትግራይ የከፋ ይሁን እንጂ በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች ግፍ ያለ ገዳቢ የሚፈስበት ምድር ቢኖር የሃበሻ ምድር ብቻ ናት። በሃገሪቱ አንጡራ ሃብት ተምረው ዛሬ ዙረው የሚወጓት የዘር ፓለቲከኞች እልፍ ናቸው። እንኳን ሃገር ቦይ የማያሻግር ቋንቋን ተገን አርገው በእኔ ቋንቋ ካልተናገርክ የሚሉ የቁም ሙታኖች የሚራወጡባት ምድር ናት። እህቱን፤ ወንድሙን፤ አባትና እናቱን ገድሎ ለነጻነት ነው የሚሉ ድርቡሾች የተፈለፈሉባት መሬት ናት። የአሁኑ ከያኔው ይሻላል ስንል እንኳንስ ሊሻለው ጭራሽ የከፋና የከረፋ ሆኖ ይኸው የትግራይን ልጆች አባሮ አሁን ደግሞ በወረፋ የኦሮሞ ስብስብ ሃገሪቱን በማመስ ላይ ይገኛል። የድላ ቅብብሎች ይሉሃል እንዲህ ነው። አንድ የጣለውን አንስቶ አቅጣጫ አልባ መንጎድ።
ሲጀመር በኢትዮጵያ ውስጥ ሴቶችን መጨቆን፤ ማሰቃየት፤ የበታችንነት ስሜት እንዲሰማቸው ማድረግ፤ ከትምህርት ማስቀረት፤ ከወንድ እኩል አይሆኑም ብሎ ማሰብ እንደ ባህል የሚታይበት ጊዜ ነበር አሁንም አለ። በተለይ ጾታዊ ትንኮሳ ከልክ ከማለፉ የተነሳ ሁሌ ሴቷ እንዳጠፋች እየተቆጠረ ለፍትህ በር ተዘግቶባቸው ኖሯል። አስተማሪው፤ ተማሪው፤ ሰራተኛው በሥራ ቦታ፤ በመንገድ ለካፊውና ቦዘኔው መብታቸውን ይረግጣል። በሴት ፊት ላይ አሲድ ደፍቶና ገድሎ፤ ደፍሮ በነጻነት የሚኖሩበት ሃገር ቢኖር የሃበሻዋ ሃገር ቀዳሚ ናት።
ይህንና ሌላም ነገር ደምረን ስንመለከት አሁን ፕ/ር ሃረገወይን በትግራይ ሆነ የምትለው ነገር በጭልፋ የቀረበ እንጂ ጉድ ብዙ ነው። ወያኔ ሜዳ ላይ እያለ የደፈራቸው ታጋይ ሴቶች ሲያረግዙ ይገድሏቸው እንደነበር ያውቃሉ? ከደርግ ጋር ሲፋለሙ ከሞቱት የትግራይ ልጆች ቁጥር ወያኔ ራሱ የገደላቸው የትግራይ ልጆች ቁጥር እንደሚበዛ ይረዳሉ? ግን በዘሩና በቋንቋው በክልሉ ፓለቲካ ለሰከረ ሰው እውነት መች ይታየውና። በድርጅት ሚስጢር ካባ ስንት ግፍ ነው ለህዝብ ጀሮ ሳይደርስ አፈር የተመለሰበት? የሰውን ስጋ እንደ ቄራ ስጋ የሚከትፉ የፓለቲካ እብዶች እንዴት ባለ የሰው መመዘኛ ይመዘናሉ? ሌላው ዓለም ጽንፈ ዓለምን ዳሶ በማርስ የመኖሪያ ሥፍራ እያመቻቸ ምላስ ለምታክል መሬት እልፍ አዕላፍ ሰዎችን ማስጨረስ ምን የሚሉት የነጻነት ተጋድሎ ነው? ግን ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ስለሆነ የዛሬን እንጂ የነገን የማያየው የሃበሻ ፓለቲካ በአስረሽ ምቸውና በእንደስትና ተደሰች ጊዜአዊ ተስፋ ብቻ የሚመራ ነው። የትግራይ ህዝብ በወያኔ የመከራ ዝናብ ሳይሆን ዶፍና ውሽንፍር ነው የወረደበት። ያ ኩሩና ፈጣሪውን አክባሪ ህዝብ ዛሬ አንዴ አማራ መጣብህ፤ ሌላ ጊዜ ኤርትራ ወረረችህ፤ ሲመቸው ደግሞ አዲስ አበባ ልንመለስ ነው እያለ ስንቱን ወጣት ነው ያስጨረሰው? በእውነት ኤርትራዊያን የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ናቸው? በጭራሽ? አሁን ማን ይሙት ለትግራይ ከአማራ ህዝብ የበለጠ የሚቀርበው አለ? የለም። የወያኔ ፓለቲካ ግን ከፋፍለህ ግዛው ስለሆነ በትግራይ የሚፈጸመው ግፍና በደልም የዚሁ አንድ ገጽታ ነው።
እውቁ psychiatrist – Viktor Frankl – Man’s search for meaning በተሰኘው መጽሃፉ ላይ የሰው ልጅን ጭካኔና የሰውን የመኖር ተስፋ አበጥሮ ያሳየናል። ግን የእኛው ሃገር ፓለቲካ በእንቅልፍ ላይ ላለ ሰው የእንቅልፍ ኪኒን የሚያዝ ነው። አሁን ጠ/ሚሩ ዋሽንግተን ላይ አሉ በመባሉ ኦሮሞው፤ አማራው፤ ትግራዪ በየዘሩ ተሰልፎ አንገትህን ለገመድ ሲሉት ምን ይሰማው ይሆን? ምነው ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች በተናጠል ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉና Guinness world record በመስበር ሃገራችንን ባስመዘገቧት። ባጭሩ ፕ/ሯ የሚሉት የሚታመን፤ ቢፈለግ የሚገኝ በመሆኑ እንዴት ብናደርግ ነው ይኽን ድርቡሻዊ የሰው ባህሪ መቀየር የሚቻለው የሚለውን መላ ብንመታ ይሻላል ባይ ነኝ። በቃኝ!