የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ጦር መሳሪያዎችን የመሰብሰብ ዘመቻ እንደሚጀመር አስታወቁ! ትላንት (እሁድ) ከሶማሌ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋር ቆይታ ያደረጉት፣ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ረ/ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ በሁሉም የሶማሌ ክልል አከባቢዎች ጦር መሳሪያዎችን የመሰብሰብ ዘመቻ እንደሚጀመር እና ከአሁን በኋላ ለአንድም የሲቪል ማህበረሰብ ትጥቅ እንደማይፈቀድላቸው አስታወቀዋል። በተጨማሪ ከመንግሥት ጦር መሳሪያ ውጭ፣ ለሲቪል ግለሰቦች ታጥቆ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑንም ዋና አዛዥ መሀመድ አህመድ ገልፀዋል ። አክለውም ይህ የጦር መሳሪያ የመሰብሰብ ውሳኔው ለዜጎች ሰላም እና ደህንነት ተብሎ የታወጀ ውሳኔ እንደሆነ ኃላፊው አብራርተዋል። የክልሉ ፀጥታ አካላት በክልሉ ውስጥ ያለው የጦር መሳሪያ የመሰብሰብ ዘመቻ በቂ አቅምና ዝግጅትም አላቸው ያሉት … [Read more...] about ሶማሌ ክልል የጦር መሣሪያ መሰብሰብ ሊጀምር ነው
Middle Column
ይቅርታና ምህረት አድራጊው ይወገዳል! የተደረገለትም ይሞታል!
መሃል ሰፋሪ አሊያም ገለልተኛ ይመስል የነበረው የኦሮሞ አክቲቪስቶች በሙሉ የጃዋር ግልገል መሆናቸው የምታውቀው፤ ልክ እንደ አይን-አፋር ሴት እየተቅለሰለሱ፣ እንደ ሽምግሌ ምሳሌ እያበዙ ከሄዱ በኋላ በማጠቃለያው ላይ “ጃዋር መሃመድ በይቅርታ ከእስር ቢፈታ ለሀገርና ህዝብ ይጠቅማል!” ሲሉ ነው። በእርግጥ በእስር ላይ ያለ ሰው እንዲፈታ ማሰብ፣ አማላጅ መላክ ወይም Lobby ማድረግ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሀገር ውስጥ የተለመደ ነው። በዚህ ረገድ በሰኔ15ቱ ግድያ ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎች መፈታታቸው በተደጋጋሚ እንደ ማሳያ ተጠቅሷል። ነገር ግን በሰኔ 15ቱ ግድያ የተሳተፉ አካላት በስልጣን ሽኩቻና አለመግባባት ምክንያት የተፈጠረ ነው። በዚህ ምክንያት የተጎዱ ሰዎች መኖራቸው እርግጥ ነው። ነገር ግን በአማራ ክልል የሚገኙ አማራዎችን ወይም ሙስሊሞችን ለማጥፋት ታቅዶ የተፈፀመ … [Read more...] about ይቅርታና ምህረት አድራጊው ይወገዳል! የተደረገለትም ይሞታል!
ኦነግ በኦነግ ላይ ዕርምጃ ሊወስድ ነው
የትኛው ኦነግ ስለየትኛው ኦነግ መግለጫም ይሁን ተቃውሞ እንደሚሰጥ ግራ እስኪያጋባ የደረሰው ዕድሜ ጠገቡ ኦነግ ተከፋፍሎ አላልቅ ብሎ አሁን ደግሞ አንዱ በአንዱ ላይ ዕርምጃ እወስዳለሁ እያለ ነው። ኢትዮ ኤፍ ኤም ያጠናከረው ዘገባ እንዲህ ይነበባል። ኦነግ ከፖርቲው ህግና ስርአት ባፈነገጠ መልኩ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን አሳሳች መግለጫዎችን ሲሰጡ በነበሩ አመራሮቹ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ። የኦነግ ቃላ አቀባይ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የተወሰኑ ሰዎች በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን በመቅረብ አላስፈላጊ መግለጫዎችንና መልዕክት በማስተላለፋቸው ምክንያት በተፈጠረ ውዝግብ ላይ ብሔራዊ ምክር ቤቱ በጠቅላላ ጉባኤ በዲሲፕሊን እንዲጠየቁ የሚያስችል ውይይት ማድረጉን ተናግረዋል። በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን በአመራሮች መካከል የርዕዮተ አለም ልዩነት እንዳለ … [Read more...] about ኦነግ በኦነግ ላይ ዕርምጃ ሊወስድ ነው
“ፍትኅ ለአዲስ አበባ” በሚል መሪ ቃል የማኅበራዊ መገናኛዎች ዘመቻ ተጀመረ
ስለ አዲስ አበባ ፍትኅ የሚጠይቅ የማኅበራዊ መገኛ ዘዴዎች ዘመቻ ዛሬ በዋናነት በትዊተር ላይ ተጀመረ። ዘመቻው ዛሬም እንደሚቀጥል አዘጋጆቹ የገለጡ ሲኾን፦ “በአዲስ አበባ የታየውን የመሬትና የኮንዶምንየም ምዝበራ በመቃወም” ፍትኅ ለመጠየቅ የተጀመረ መኾኑንም አክለዋል። በዘመቻዉ ላይ “#ፍትህለአዲስአበባ”፤ “#አዲስአበባ” እንዲሁም “#ኢትዮጵያ” የሚሉ አሰባሳቢ ቃላት (ሐሽታጎች) ጥቅም ላይ ውለዋል። የዘመቻው ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ “ተፈጸመ” ያሉትን አድሏዊ አሠራር እና በደል በመዘርዘር ተቃውሟቸውን እና ቅሬታቸውን ሲያስተጋቡ ተስተውለዋል። የዘመቻው አስተባባሪዎች ባሰራጩት ጽሑፍ፦ “በኢ/ር ታከለ ኡማ አስተዳደር ዘመን በአዲስ አበባ የታለያዩ አድሎአዊ አሠራሮች፤ ጥቅመኝነት፤ የህዝብን ሃብት ማባከን የመሳሰሰሉ ጥፋቶች ተስተውለዋል” ብለዋል። ግድፈቶች … [Read more...] about “ፍትኅ ለአዲስ አበባ” በሚል መሪ ቃል የማኅበራዊ መገናኛዎች ዘመቻ ተጀመረ
ወደ ዛምቢያ ከተሰደዱ 50 ኢትዮጵያውያን አንዱ ግድያ ተፈጸመበት
ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ዛምቢያ ካቴቴ አውራጃ ውስጥ በበሀገሬው ቺቦላያ ነዋሪዎች በተፈጸመ ጥቃት መገደሉን ዛምቢያ ሪፖርትስ ትናንት በድረ-ገጹ ዘግቧል። አምሳዎቹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ዛምቢያ የገቡት ምዋሚ በተሰኘው ድንበር በኩል ሲኾን፤ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ከማቅናታቸው አስቀድሞ ካቴቴ ውስጥ በሕገወጥ ቆይተዋል ሲል የአካባቢው ፖሊስ ተናግሯል። የአካባቢው ነዋሪዎች ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ባረፉበት ቦታ በሌሊት በድንገት ባደረሱት ጥቃት ከግድያው ባሻገር ዘጠኝ ኢትዮጵያውያን መጠነኛ የመቊሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የአካባቢው ፖሊስ ኮሚሽነር ሉክሰን ሳካላ ገልጠዋል። ከኢትዮጵያውያን ስደተኞቹ መካከል 38ቱ በፖሊስ ሲያዙ ማንነታቸው ያልተገለጡ ኹለት ስደተኞች ግን ማምለጣቸውን የፖሊስ ኃላፊው አክለው ተናግረዋል። የፖሊስ አዛዡ፦ የአካባቢው ነዋሪ በሰፈራቸው ስለመጡ ሰዎች ጥርጣሬ … [Read more...] about ወደ ዛምቢያ ከተሰደዱ 50 ኢትዮጵያውያን አንዱ ግድያ ተፈጸመበት
በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላን አስመልክቶ የተደረገ ጥናት ውጤት
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚፈፀም የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ ጋር በተያያዘ ያደረገውን ጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል። የጥናቱ ውጤት ዋነኛ ይዘት ከዚህ በታች ተቀምጧል። በአዲስ አበበ ከተማ መሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ ጥናት አንኳር፥ • የከተማው አስተዳደር እያየና እየሰማ በሕገ ወጥ እና በተደራጀ መልኩ በወረራ የተያዙ ቦታዎች በፍጥነት ካርታና ፕላን ተሰርቶላቸው ለ3ተኛ ወገን በሽያጭ ተላልፈዋል። በማኅበር እና በግል ለማምረቻና ለንግድ አገልግሎት እንዲውሉ ተደርገዋል፤ በምንም መስፈርት የቤት ተጠቃሚ ሊሆኑ የማይገባቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ቤት እና የነዋሪነት መታወቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ • በዋናነት በመሬት ወረራው ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ የነበሩት ሰዎች የአርሶ አደር ልጆች … [Read more...] about በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላን አስመልክቶ የተደረገ ጥናት ውጤት
እነ ጃዋር መሐመድና ተቋማቱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ “ፈጽመናል አልፈጸሙም” በሚል ተካካዱ
“በግል ሐኪሜ ካልሆነ አልታከምም ማለታቸው እንድንጠራጠር አድርጎናል” ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ “አዕምሮዬን ብስት እንኳን በማላውቀው ሐኪም መነካት አልፈልግም” ተጠርጣሪ አቶ ጃዋር መሐመድ “ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ የሚሰጠው ትዕዛዝ እየተከበረ አይደለም” ተጠርጣሪዎች “መርህ አክብረን ሁሉንም ነገር በአግባቡ እየፈጸምን ነው” የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በተጠረጠሩበት የአመፅ ጥሪ ማድረግ፣ የሰው ሕይወት ማጥፋት፣ የእርስ በርስ ግጭት መፍጠር፣ የንብረት ውድመትና ሌሎችም የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኘው እነ አቶ ጃዋር መሐመድና ሁለቱ የመንግሥት ተቋማት (ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና ፌዴራል ፖሊስ) የፍርድ ቤት ትዕዛዝ “ፈጽመናልና አልፈጸሙም” በሚል ተካካዱ። ሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች “ፈጽሜያለሁና አልፈጸሙም” በሚል … [Read more...] about እነ ጃዋር መሐመድና ተቋማቱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ “ፈጽመናል አልፈጸሙም” በሚል ተካካዱ
የፍርድ ቤት የችሎት ውሎ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት እንዲተላለፍ ምክረ ሐሳብ ቀረበ
በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ምክንያት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ጨምሮ በርካታ ተጠርጣሪዎች የፍርድ ቤት ውሎ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት ለሕዝብ ተደራሽ እንዲደረግ ምክር ሐሳብ ቀረበ። የፍርድ ቤት ውሎ በቀጥታ ሥርጭት ለሕዝብ ተደራሽ እንዲሆንና ሌሎች አማራጮችን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው፣ የኢፌዴሪ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ነው። በተቋሙ ዋና እንባ ጠባቂ እንዳለ ኃይሌ (ዶ/ር) ተፈርሞ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ለዳኞችና ዓቃቢያነ ሕግ፣ ለተጠርጣሪዎችና ለችሎት ታዳሚዎች ደኅንነትና ጥበቃ አመቺ በሆነ ሰፊ አዳራሽ ችሎት ማስቻልን የመጀመርያ አማራጭ አድርጓል። የፍርድ ቤቱን ውሎ ሁሉም የመንግሥትና የግል፣ የሕትመትና የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ አካላት ብቻ እንዲዘግቡት ማድረግና በዘገባዎቻቸው የችሎቱን … [Read more...] about የፍርድ ቤት የችሎት ውሎ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት እንዲተላለፍ ምክረ ሐሳብ ቀረበ
የእነ ለማ ጉዳይ ወደ ሕግ ሊያመራ ይችላል ተባለ
ሰሞኑን ከኃላፊነታቸው መታገዳቸው የተሰማው የኦሮሚያ ከፍተኛ አመራሮች አቶ ለማ መገርሣ፥ ወ/ሮ ጠይባና ሜልኬሣ ሚደጋ ከፌዴሬሽን ምክርቤት አባልነታቸውም ተነስተዋል ተብሎ በሥፋት ሲናፈስ ነበር። ሆኖም ዜናው ሐሰት ነው ተብሎ ማስተባበያም ተሰጥቶበታል። ጎልጉል ከወደ አዲስ አበባ ያሰባሰበው መረጃ እንደሚጠቁመው በቀጣይ ግለሰቦቹ ጉዳያቸው ወደ ሕግ የሚሄድበት መንገድ እየተመቻቸ ያለ ይመስላል። በተለይ ወ/ሮ ጠይባ ሻሸመኔ ከንቲባ በነበሩበት ጊዜ በከተማዋ ለተፈጸሙ ዘግናኝ ግፎች ተጠያቂ የሚሆኑበት ሁኔታ አለ የሚለው ገዝፎ እየወጣ ነው። እንደሚታወቀው ወ/ሮ ጠይባ ከንቲባ በነበሩበት ጊዜ በሻሸመኔ ከተማ እጅግ ዘግናኝ የሆነው ግድያ ያውም ገድሎ ዘቅዝቆ የመስቀልና የማቃጠል አሰቃቂ ወንጀል ተፈጽሟል። የብልጽግና ኦሮሚያ ቅርንጫፍ አመራሮችም ጉዳዩን በግልጽ ባይናገሩትም የጠይባን በሕግ … [Read more...] about የእነ ለማ ጉዳይ ወደ ሕግ ሊያመራ ይችላል ተባለ
የዎላይታ አመራሮች “ከህወሃትና ኦነግ ሸኔ አካላት ጋር በድብቅ ስብሰባ ያረጉ ነበር”
የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኮምቤን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ከትላንት በስቲያ በመከላከያ ሠራዊት መያዛቸው ተሰምቷል። እሁድ አመሻሹን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊዎች ለደቡብ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ የዎላይታ ዞን አመራሮች በዞኑ ኮማንድ ፖስት ዛሬ ከሰዓት መያዛቸውን ተናግረዋል። በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አለማየሁ ባውዲ እንዳሉት የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ ህገወጥ አደረጃጀቶችን ፈጥረው ግጭት የመቀስቀስ ፍላጎታቸውን እንዲያስፈጽሙ እያደረጉ ነበር ብለዋል። አመራሮቹ በፓርቲ ደረጃ እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ ሀገር ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር ተቀናጅተው በመስራት ላይ ይገኛሉም ሲሉ ገልጸዋል። አቶ አለማየሁ ሀገር ለማፍረስ የሚሰሩ በማለት … [Read more...] about የዎላይታ አመራሮች “ከህወሃትና ኦነግ ሸኔ አካላት ጋር በድብቅ ስብሰባ ያረጉ ነበር”