አቶ ፍፁም አባዲ በኢትዮጵያ አየርመንገድ የካርጎ ክፍል ሃላፊ፣ ምክትሉ አቶ ናትናኤል ጎበና እና የጌታቸው አሰፋ የቅርብ ዘመድ የሆነው አቶ ዮሃንስ አረጋይ በአየርመንገዱ የካርጎ ክፍል የሚሰሩ “የጌታቸው አሰፋ ትሬዲግ” ሰራተኞች ናቸው። በዱባይና ቻይና የሚገኙ የኢትዮጵያ አየርመንገድ የጭነት ወኪሎች፣ የቦሌ ጉሙሩክ ሃላፊ ከነበረው ከአቶ ገብረማርያም እስከ ጥበቃ ክፍል ሰራተኞች የሚደርሰው ሰንሰለት የጌታቸው አሰፋ የኮንትሮባንድ ንግድ ሰንሰለት ነው። እነ ጌታቸው አሰፋ ከስልጣን የተወገዱበትን ሚስጥር፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በህወሓቶች ስለሚፈፀመው ዘረፋና የኮንትሮባንድ ንግድ በተጨባጭ ማስረጃ የተደገፈ መረጃ ይፋ ወጥቷል። “የጌታቸው አሰፋ ትሬዲንግ” ከሶስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የ800 ሚሊዮን ብር ኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በአየርመንገድ በኩል ግብር ሆነ ታሪፍ … [Read more...] about “ጌታቸው አሰፋ ትሬዲንግ” በቢሊዮን የሚቆጠር የኮንትሮባንድ ዕቃዎች አስመጪና አከፋፋይ!
Middle Column
ከአገር ሊወጣ የነበረ ከ132 ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር 9.2 ኪሎ ኮኬይን በቁጥጥር ሥር ዋለ
በህገ-ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጣ የነበረ 132 ሺህ 860 የአሜሪካን ዶላር እና 9.2 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተሰኘ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል። በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቴክኖሎጂ ተደገፎ በተደረገ ጥብቅ ፍተሻና ክትትል ከአዲስ አበባ ወደ ናይጄሪያ ሊጓጓዝ የነበረ 9.2 ኪሎ ግራም ኮኬይን እንዲሁም መዳረሻውን ዝምባብዌ ያደረገ 132 ሺህ 860 የአሜሪካን ዶላር በቁጥጥር ስር መዋሉ ነው የተገለፀው። የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለኢቲቪ በላከው መረጃ እንደገለጸው፤ በህገወጥ ድርጊቱ ተጠርጥረው የተያዙት ግለሰቦች በኢትዮጵያ ለቀናት ባደረጉት ቆይታ ከግብረአበሮቻቸው ጋር ግንኙነት በመፍጠር በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ነበር። ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ክትትል … [Read more...] about ከአገር ሊወጣ የነበረ ከ132 ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር 9.2 ኪሎ ኮኬይን በቁጥጥር ሥር ዋለ
ወደ ንግድ ባንክ በየቀኑ በአማካኝ ከ351 ሚሊዮን ብር በላይ ይገባል
ከብር ኖት ለውጡ ጋር በተያያዘ በአማካኝ በቀን ከ16 ሺ 700 በላይ ሰዎች አዲስ የሒሳብ ደብተር እንደሚከፍቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ። በየእለቱ በአማካኝ ከ351 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ንግድ ባንኩ ገቢ እንደሚሆን ገለጸ። የባንኩ የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ የአብስራ ከበደ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ የብር ኖቱ መቀየሩ በባንኮች የሚቆጠበውንም ሆነ የሚቀመጠውን ብር ሆነ የደንበኞችን ቁጥር ያሳድጋል። ባንኩ ከ5ሺ ብር በላይ ለቅያሬ ይዘው የሚመጡ ሰዎች የቁጠባ ደብተር እንዲከፍቱ እያደረገ መሆኑን አመልክተው ፣ የቁጠባ ሒሳብ ደብተር የሚከፍቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን አስታውቀዋል። በቀን በአማካኝ ከ16ሺህ 700 በላይ ሰዎች የቁጠባ ሒሳብ እንዲከፈቱ ጠቁመው ፣ የቁጠባ ሂሳቡ በየእለቱ ከ351 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ … [Read more...] about ወደ ንግድ ባንክ በየቀኑ በአማካኝ ከ351 ሚሊዮን ብር በላይ ይገባል
“አልሲሲ የፈጣሪ ጠላት ነው፤ አገራችንን ለቅቀህ ውጣ” የተቃውሞ ሰልፈኞች
በግብጹ ፕሬዘዳንት አልሲሲ ላይ የተነሳው ቁጣ በመላው ግብፅ ተቀጣጥሏል፤ የአልሲሲን አገዛዝ ተቃውመው የሚደረጉ ሰልፎች በመላው ግብፅ መደረጋቸውን ቀጥለዋል። የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲ በግብፅ አለመረጋጋትና ትርምስ ለመፍጠር ጥረት የሚያደርጉ ሁሉ ከድርጊታቸው ቢታቀቡ ይሻላቸዋል ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። ተቃዋሚዎች አልሲሲ ስልጣን እንዲለቁ ይፈልጋሉ፤ እንደ ዋና ምክያት የሚያነሱት ደግሞ ሙሰኝነታቸውን ነው። ሲሲ ለአመታት ከጦር ኃይሉ ጋር በመሆን ለፕሬዝዳንቱ ቤተሰብ እና ጓደኞች ይሆኑ ዘንድ ከተገነቡ ቅንጡ ቤቶችና ከሌሎች በርካታ የግንባታ ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል እያሉ ነው። ተቃውሞው ቁጣቸው እየጨመረ በሚመጣ አመፀኞች ተቀጣጥሏል። በተለይ በገጠርና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አካባቢዎች በርትቷል። ህገ ወጥ ግንባታዎች ይቁሙ … [Read more...] about “አልሲሲ የፈጣሪ ጠላት ነው፤ አገራችንን ለቅቀህ ውጣ” የተቃውሞ ሰልፈኞች
ለኮፍያና ለባጅ ከ415 ሺህ ዶላር በላይ ከባንክ መውሰዱን ዋልታ አመነ
“ከ69 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከመመሪያ ውጪ ከኢትዮጵያ ባንክ መባከኑ በሰነድ ተረጋገጠ” በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቀድሞ ፕሬዝደንት አቶ ባጫ ጊና የተፈረመበትን ሰነድ ዋቢ አድርጎ ባሰናዳው ወሬ በ2010 ከብሔራዊ ባንክ መመሪያ ውጪ በትንሹ ከ69 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ መሰጠቱን ሸገር 102.1 በመጥቀስ ዘግበን ነበር፡፡ በዚሁ ዓመት በግንቦት ወር መመሪያው የውጭ ምንዛሬ እንዲያገኙ ከተፈቀደላቸው የሥራ ዘርፎች ውጪ ላሉ ወይም መመሪያው ለማይመለከታቸው 5 ድርጅቶች በድምሩ 11 ሚሊዮን 841,583 የአሜሪካ ዶላር እንደተሰጠ ከተገኘው ሰነድ በመጥቀስ በዘገባው ተመልክቷል፡፡ በዚሁ ሰነድ ላይ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል 500,000 የአሜሪካ ዶላር እንደተፈቀደለት ተጽፏል፡፡ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ለሸገር በላከው ማስተባበያ የውጭ ምንዛሬው የተሰጠኝ ሕጋዊ … [Read more...] about ለኮፍያና ለባጅ ከ415 ሺህ ዶላር በላይ ከባንክ መውሰዱን ዋልታ አመነ
የፀጥታና ደህንነት ተቋማት በዓላት ያለ ችግር እንዲከበሩ በዘመናዊ መልኩ ተዘጋጅተዋል
መጪዎቹን የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበሩ ለማድረግ የፀጥታና የደህንነት ተቋማት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅቶች ማድረጋቸው ተገለፀ። ይህን የገለጸው ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለፀጥታና ደህንነት አካላት በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ ተግባራዊ የፀረ-ሽብር ሥልጠና ሰጥቷል። ሥልጠናው ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከፌዴራልና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች፣ ከሪፐብሊካን ጋርድና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ልዩ ኃይል ለተውጣጡ ከ330 በላይ አመራሮችና አባላት ነው የተሰጠው። የንድፈ ሃሳብና የተግባር ሥልጠናው ሽብርተኝነትን መከላከልና ማክሸፍ፤ የሽብር ተልዕኮዎችንም አስቀድሞ ማወቅ የሚቻልበትን የመረጃ ሥራ ያካተተ ነው። በዚሁ መሰረት ሰልጣኞቹ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊ /ቪ.አይ.ፒ/ እገታን በተቀናጀና … [Read more...] about የፀጥታና ደህንነት ተቋማት በዓላት ያለ ችግር እንዲከበሩ በዘመናዊ መልኩ ተዘጋጅተዋል
ተከሳሾቹ እነ ጃዋር ወደ እስር ቤት እንዲዛወሩ ታዘዘ
ባለፈው ሰኞ በዋለው ችሎት እነ ጃዋር ሲራጅ መሐመድ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት የክስ ፋይላቸው መቀየሩ ተዘግቦ ነበር። የዚያን ዕለት የቀረበባቸውም ክስ ሃይማኖትና ብሔርን መሠረት በማድረግ፣ በተለይም በአማራ ብሔር ተወላጆችና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም የተለያዩ መገናኛ ብዙኃንና የትስስር ድረ ገጾችን በመጠቀምና በአካል በመገኘት፣ በተገለጸው አግባብ ባስነሱት የእርስ በርስ ግጭት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የ13 ሰው ሕይወት እንዲያልፍና 48,026,526 ብር የሚገመት ንብረት እንዲወድም አድርገዋል፣ በኦሮሚያ በተለያዩ ዞኖችና ከተሞች የ167 ሰዎች ሕይወት እንዲያልፍ፣ 360 ሰዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸውና 4,673,031,142 ብር ግምት ያለው ንብረት እንዲወድም ማድረጋቸውን በመጥቀስ ነበር ዐቃቤ ሕግ ክሱን … [Read more...] about ተከሳሾቹ እነ ጃዋር ወደ እስር ቤት እንዲዛወሩ ታዘዘ
በቦሌ በኩል አሮጌው ብር እየገባ ነው፤ በበረራ ሠራተኞችና መንገደኞች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ተጠየቀ
“ህወሓት ወደ አገር በሚገቡ መንገደኞች ገንዘብ ለማስገባት እየጣረ ነው” በሚል ርዕስ አንድ ዘገባ ካወጣን በኋላ ዛጎል “በአሜሪካ “ገንዘብ – ውሰዱልን” የቅርብ ወዳጆችን ግንኙነት በጠሰ” በሚል ርዕስ የሚከተለውን ዘገባ ለንባብ አብቅቷል። አሁንም የኢትዮጵያን መንግሥት ለማሳሰብ የምንፈልገው ይህንን የተቀናጀ ሥራ እያከናወኑ ያሉት ህወሓቶች መሆናቸውን ነው። ከዚህ ሌላ በተለያዩ የኢትዮጵያ ድንበር ኬላዎች ከጎረቤት አገር ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ ይገባል ከሚለው እሳቤ በተጨማሪ በቦሌ በኩልም እየገባ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባዋል። ስለዚህ በቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮጵላን ማረፊያ በተጓዦች በተለይም በበረራ ሠራተኞች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግ ይገባል እንላለን። በአሜሪካ “ገንዘብ – ውሰዱልን” የቅርብ ወዳጆችን ግንኙነት በጠሰ “እንዴት ብትንቁን ነው” ሲል ባለቤት ቁጣ የተሞላ ምላሽ … [Read more...] about በቦሌ በኩል አሮጌው ብር እየገባ ነው፤ በበረራ ሠራተኞችና መንገደኞች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ተጠየቀ
የእነ እስክንድር ክስ እንዲሻሻል ተጠየቀ
ዓቃቤ ሕግ በመሠረተባቸው ክስ የሕዝብ ሰላምንና የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል፣ ሥልጣንን በኃይል ለመያዝና የሽብር ተግባር ለመፈጸም ተዘጋጅተዋል በማለት የዋስትና መብታቸው እንዳይፈቀድላቸው መከራከሩን በመቃወም ለፍርድ ቤቱ ምላሽ የሰጡት እነ አቶ እስክንድር ነጋ፣ መንግሥት ወይም ዓቃቤ ሕግ ለሕዝብ ሰላምና ለአገር ደኅንነት የሚያስብ ከሆነ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆላቸው፣ በመጪው አገራዊ ምርጫ እንዲሳተፉ መደረግ እንዳለበት ለፍርድ ቤት ተናገሩ። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ዋስትና እንዲከበርላቸው የጠየቁት፣ የተመሠረተባቸውን ክስ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሽብር ተግባራትና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች አንደኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም. ካነበበላቸው በኋላ፣ ስለመብት … [Read more...] about የእነ እስክንድር ክስ እንዲሻሻል ተጠየቀ
ኤርሚያስ ለገሰ፤ “ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል”
የኢህአዴግ ካድሬና እያለቀሰ ስለኢህአዴግ ይሰብክ የነበረው የበረከት ስምዖን የጡት ልጅ ኤርሚያስ ለገሠን በተመለከተ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” እና “የኤርምያስ ለገሰ ቪዲዮዎች ፉከራ ሲጋለጥ” በሚል ሁለት የአስተያየት ጽሁፎችን አቅርቦ ነበር። በወቅቱ እነዚህን ጽሁፎች በማተማችን ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶብናል። የተሰጡትንም አስተያየቶች አሁንም በጽሁፎቹ ግርጌ ማግኘት ይቻላል። ኤርምያስ ለረጅም ጊዜ እንደ ትልቅ ነገር አድርጎ ሲያወራው የነበረው ቪዲዮ የኔታ ቲዩብ ይፋ አድርጎታል። አበበ ገላው ደብቆ ያስቀመጠውና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚናገር ትልቅ ምሥጢር የያዘ የድምጽ ቅጂ አለ በማለት ኤርምያስ ቅጂው አንዲወጣ አበበን ባደባባይ ይገዳደር ነበር። አሁን በወጣውና ኤርምያስ ምሥጢር ሲለው በነበረው ድምጽ ቅጂ ውስጥ ግለሰቡ … [Read more...] about ኤርሚያስ ለገሰ፤ “ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል”