“ሃጫሉን የገደሉት ነፍጠኞች ናቸው፤ መላው የኦሮሞ ህዝብ የምኒሊክን ሃውልት አፍርሰህ ወደ ቤተመንግሥት ገስግስ!” ይህንን የዘር ዕልቂት የተናገረው የዶ/ር ዐቢይ የለውጥ ቡድን እነ ጃዋር መሃመድን በቁጥጥር ሥር ከማዋሉ በፊት በሕወሃት የደም ገንዘብ የሚቀለበው ሕዝቅኤል ጋቢሣ አሜሪካ ቁጭ ብሎ ሕወሃት ባደራጀው ዲጂታል ሚድያ በመጠቀም ሲያውጅ ነበር። “በደረሰን መረጃ መሠረት፤ የሃጫሉ ሁንዴሳ ገዳዮች ነፍጠኞ ሳይሆኑ ሥልጠናና ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የመጡ ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራውያን ናቸው፤ እኔ በደንብ አውቃለሁ እነማን እንደገደሉት፤ ምን ዓይነት ሚሊተሪ ፐርሶኔል እንደተሳተፈም አውቃለሁ፤ ኢትዮጵያውያን እንኳን አይደሉም፤ ኤርትራውያን ናቸው" ይህን የተናገረው ደግሞ በጎጥ አስተሳሰብ እጅግ የጠበበው መርዘኛው ፀጋዬ አራርሳ ነው። ፀጋዬ አራርሣ፤ ሃገር መምራት የማይችል ደካማ ነው፤ … [Read more...] about ህወሓት ይፍረስ፤ ዕልቂት ሰባኪዎች ለፍርድ ይቅረቡ!
Middle Column
የስብሃት ነጋ ወንድም በሌብነት ተያዘ
አቤሴሎም ነጋ የተባለውና ነዋሪነቱ በአውስትራሊያ የሆነው ስብሃት ነጋ ወንድም 4 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር (2.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር) በማጭበርበርና በመስረቅ መከሰሱን Herald Sun ዘገበ። እኤአ ከ2008 – 2019 ባሉት ዓመታት የ54 ዓመቱ አቤሴሎም ነጋ የተለያዩ የፋይናንስ ወንጀሎችን በመፈጸም ነው 4.2 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ወደ ግል የባንክ ሒሳቡና iEmpower በሚል ለሚመራው የግል ድርጅቱ ሒሳብ እንዲገባ ያደረገው። ወንጀሉ ስርቆት ብቻ ሳይሆን በኑሯቸው ዝቅተኛ ለሆኑ የሚሰጠውን (የዌልፌር) ገንዘብን አጭበርብሮ መውሰድም የሚጨምር ነው። አቤሴሎም ከዘረፈው ገንዘብ ውስጥ $25,300 የሚሆነውን ያጭበረበረው ከሕግ ጋር ችግር ያለባቸውን የአፍሪካ ወጣቶችን ለመርዳት ከተቋቋመ ድርጅት በመስረቅ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አቤሴሎም የቪክቶሪያ … [Read more...] about የስብሃት ነጋ ወንድም በሌብነት ተያዘ
ሕግን በሕግ እናስከብራለን!!
ጃዋር በአዲሱ “ዓለም” ሆኖ ከፍርድ ሒደት ይልቅ ሽምግልናን ጠየቀ
ሐሙስ ዕለት በተለያዩ ወንጀሎች ተከስሶ ፍርድ ቤት የቀረበው ጃዋር የባህላዊ ሽምግልና እና ዕርቅ ከመደበኛው ፍርድ ቤት በፊት እንዲሞከር ጥያቄ አቀረበ። እጅግ መረን ከለቀቀና ከተደንደላቀቀ የቅምጥል ኑሮው ወጥቶ ወደ አዲስ “ዓለም” የገባው ጃዋር መሐመድ ያቀረበውን ጥያቄና ተማጽንዖ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ አድርጎ ክሱ እንዲቀጥል ቀጠሮ ሰጥቶ አሰናብቶታል። ጃዋር በሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የሚያስጠረጥረውን በርካታ መረጃዎች ተከትሎ፤ በኔትወርክ ሊያደርግ ያሰበው የመንግሥት ለውጥ በመክሸፉ፤ በተለይም በአስከሬን ባለቤትነት የተፈጠረው ግብግብ ከፍተኛ ተቃውሞ ስላስነሳበት የሽምግልና አካሄድ እንደሚያዋጣው በመረዳት ጥያቄውን ሐሙስ ለዋለው ችሎት ማቅረቡን በቅርብ ሂደቱን የሚከታተሉ ለጎልጉል ተናግረዋል። ጎልጉል ቀደም ሲል የሽምግልና ሃሳብ እንዳይጨናገፍ በማለት ያላተመውን … [Read more...] about ጃዋር በአዲሱ “ዓለም” ሆኖ ከፍርድ ሒደት ይልቅ ሽምግልናን ጠየቀ
ሃጫሉ አምቦ እንዲቀበር የቤተሰብ ፍላጎት ነው – ሃብታሙ ሁንዴሳ
ዛሬ [ረቡዕ] በአምቦ ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ እና የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ከሚፈጸምበት ቦታ ጋር ተያይዞ በተከሰቱ ግጭቶች የሟቹን ድምጻዊ አጎትን ጨምሮ 5 ሰዎች መገደላቸውን ከቤተሰብ፣ ከከተማው ነዋሪዎች እና ከሆስፒታል ምንጮች ቢቢሲ አረጋግጧል። ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም ከ10 በላይ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውም ተነግሯል። የሃጫሉ ታናሽ ወንድም የሆነው ሃብታሙ ሁንዴሳ ለቢቢሲ ሲናገር “አጎታችን ተገድሏል። በእድሜ ትልቅ ሰው ነው። ያሳደገን ነው። የአባታችን ወንድም ነበር” ብሏል። ከሟቾቹ መካከል የአንዱ የሃጫሉ አጎት መሆናቸውን የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ከሃጫሉ አጎት በተጨማሪ ሶስት የቤተሰብ አባላት በጥይት ተመተው የተለያየ ጉዳት እንደደረሰባቸው ሃብታሙ ሁንዴሳ ለቢቢሲ ተናግሯል። “የአጎታችን ሚስት እግሯን ተመታለች፣ … [Read more...] about ሃጫሉ አምቦ እንዲቀበር የቤተሰብ ፍላጎት ነው – ሃብታሙ ሁንዴሳ
ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት
(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን) ዛሬ ላይ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች በስፋት አየተዘገበ ስላለው የኮሮና መድሀኒት ተገኘ የተባለው ዴክሳሜታሶን መድሀኒት አዲስ የተገኘ ሳይሆን ከዚህ በፊት እኛም ሀገር ላይ በስፋት ስንጠቀምበት የነበረ መድሀኒት ነዉ። ዴክሳሜታሶን (Dexamethasone) የሚባለው ስቴሮይድስ (Steroids) ከሚባለው ቤተሰብ የሚመደብ የመድኃኒት ዓይነት እ.ኤ.አ ከ1960 ጀምሮ ለተለያዩ በሽታዎች ጥቅም ላይ ሲዉል የቆየ ነው። ዛሬ ቢቢሲ ላይ የተዘገበዉ መድሀኒት የመተንፈስ ችግር እና በጽኑ የኮሮና ቫይረስ ሕመም ላይ ያሉ ሰዎችን እንጂ መጠነኛ (Mild Symptoms) ምልክት ላላቸው እንደማይጠቅም በጥናቱ ላይ አስፍረዋል። በተጨማሪ ስቴሮይድስ (Steroids) ' በከፍተኛ ጥንቃቄ' የሚሰጡ መድኃኒቶች ሲሆኑ በርካታ 'የጎንዮሽ ጉዳት' እንዳላቸው … [Read more...] about ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት
የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል
የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ደግም ለተጀመረው ድርድር እንቅፋት መሆኑን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገለፁ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አምስተኛ ቀኑን በያዘው የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የሶስትዮሽ ድርድር የእስካሁን ውጤት ላይ እየሰጡት ባለው መግለጫ የግብፅ የእኔ ጥቅም ብቻ ይጠበቅ አቋም ድርድሩን እየተፈታተነ ነው ብለዋል። ሚኒስትሩ እንደተናገሩት፥ ግብፅ በድርድሩ በተለመደው ሁለት አካሄዷ ቀጥላበታለች ነው ያሉት። ግብፅ አንድ እግሯን ድርድሩ ላይ አንድ እግራን የፀጥታው ምክር ቤት አስቀምጣ መደራደርን መምረጧን በማንሳት። በድርድሩ ግብፃውያኑ የፈለጉት እና የጠየቁት ሁሉ እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ የሚሰጡት ግን የላቸውም ነው ያሉት። ግብፅ የጋራ ስምምነት ላይ ሳይደረስ ኢትዮጵያ ውሃ መሙላት አትችልም የሚል ተቀባይነት የሌለው … [Read more...] about የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል
ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል
የሚዲያው ዝምታ ለምን ይሆን? የኮሮና ቫይረስ በቻይና ከመከሰቱ በፊት በአሜሪካ በቫይረሱ ተጠቅተው የሞቱ መኖራቸው ተረጋገጠ። ይህንን ያረጋገጡት የአሜሪካ የበሽታ ቁጥጥር ማዕከል (CDC) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሮበርት ሬድፊልድ ናቸው። ዳይሬክተሩ እንዳሉት ይህ የታወቀው በኢንፍሉዌንዛ በሞቱ ሰዎች ላይ በድጋሚ በተደረገ ምርመራ ነው። በተለያዩ የሚዲያ ዘገባዎች በተደጋጋሚ ሲነገር እንደቆየው የኮሮና ቫይረስ የተጀመረው በቻይና ዉሃን ከተማ እንደሆነ ነበር። ለበሽታው መነሻም የተለያዩ መላምቶች ሲሰጡ ቆይተዋል። አንዱ መላምት ከእንስሳት ወደ ሰው ነው የተላለፈው የሚል ነው። ለዚህም እንደ ማስረጃነት የሚቀርበው ቻይናውያኑ የሚበሉት፣ “እርጥብ ገበያ” (wet market) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ከባህር የሚገኙ ማንኛውም የአሣ ዝርያ እስከ የሌሊት ወፍ፣ እባብ፣ ውሻ፣ ሸለምጥማጥ፣ … [Read more...] about ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል
የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው?
በቡራዩ ብር የማይሰጥ አገልግሎት አያገኝም በአዲስ አበባ ዙሪያና ውስጥ የባዶ መሬትና የኮንዶሚኒየም ቤቶች ገበያ ደርቷል። በርካቶች እንደሚሉት ይህ የደራ ገበያ ምሥጢር ባለመሆኑ ከከንቲባ ታከለ ኡማ አስተዳደር የተሰወረ አይደለም። ምን አልባትም የአዲስ አበባ መሬትና የኮንዶሚኒየም ቤቶች የጠራራ ጸሃይ ገበያና የባለቀንነት ሽሚያ፣ በማኅበራዊ ጉዳዮች ባላቸው ተሳትፎ ሰፊ ተቀባይነት ላላቸው ታከለ ኡማ ጉዞ ጋሬጣ እንዳይሆንባቸው የሚፈሩም አሉ። በተመሳሳይ በቡራዩ ነዋሪዎች ከመሬት ጋር በተያያዘ ሰፊ ቅሬታ ያሰማሉ። በቡራዩ ብር የማይጠበቅበት አገልግሎት እንደሌለም አመልክተዋል። የአየር ጤና ነዋሪ መሆናቸውን የገለጹ ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንዳስታወቁት ለውጡን ተከትሎ በርካታ ቦታዎች ታጥረውና ሳይታጠሩ ባለቤት አልባ ሆነዋል። እንደ እነሱ ገለጻ ባለቤቶቻቸው ጠፍተዋል፣ … [Read more...] about የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው?
ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ
በአሜሪካ የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክትል ሊቀ መንበር ተደርጎ የተሾመው የቀድሞው የህወሃት ካድሬና የበረከት ስምዖን ታማኝ ኤርሚያስ ለገሰ መሰናበቱ ተሰማ። እስክንድር ነጋን የጠቀሱ የጎልጉል እማኞች እንዳሉት ኤርሚያስ መባረሩን አያውቅም። በዚህ ሳቢያ 360 እንደ ስሙ ዘመቻውን ያዞራል ተብሎ ይጠበቃል። የእስክንድር ነጋን የአሜሪካ ጉዞ ተከትሎ በሰርግና ምላሽ የባለ አደራው ምክትል ሰብሳቢ የሆነው ኤርሚያስ ሹመቱን አስመልክቶ ስለ ቀጣዩ የትግል አቅጣጫ፣ የትግሉ ግብና አደረጃጀት እንዲሁም ኔትዎርክ ማብራሪያ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል። ተያዘውም ወደ ተፈለገው ዓላማ እንደሚደርሱ ምሎ ነበር። ለድርጅቱ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ ቅርብ የሆኑና ይህ ውይይት ሲደረግ የነበሩ ኤርሚያስ ለገሰ በቅርቡ ከሃላፊነት መነሳቱ ይነገረዋል "የእሱ መሰናበት ያለቀ ነው። መጀመሪያም ትክክል አልነበረም" … [Read more...] about ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ