ትህነግ ወደ ከርሰ መቃብር፤ ጃዋር ወደ ከርሱ፤ ልደቱ ወደ ዕረፍቱ
በስተመጨረሻ “መንግስት የለም” የሚለውን ትግል ተቀላቅለው የነበሩትና፣ ትህነግ ባስቀመጠው የትግል ስልት የማስተባበር ስራ ሲሰሩ እንደነበር በመግለጽ ክስና ወቀሳ ሲሰነዘርባቸው የነበሩት አቶ ልደቱ አያሌው በድንገት ከፖለቲካ በበቃኝ መገለላቸው ተሰማ። ውሳኔያቸው ከትህነግ ህልውና መክሰማና ከነ ጃዋር ምግብ መብላት መጀመር ጋር መያያዙ ውሳኔያቸውን የተስፋ መቁረጥ አስመስሎባቸዋል።
ልደቱ አያሌው በቅርቡ ተከሰው በነበሩበት ወቅት የተገኘባቸውን ሽጉጥ ከደህንነት መስሪያ ቤት የተሰጣቸው መሆኑንን መግለጻቸው፣ በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ በሂሳብ መዝገብ ወጪ እየተደረገ ደሞወዝ ይከፈላቸው እንደነበር ይፋ መሆኑ “ቀድሞም ትህነግ ነበሩ” የሚለውን ወቀሳ አጠናክሮባቸው ነበር።
ቀደም ሲል ህግ ተጥሶም ቢሆን ምርጫ መደረግ እንደሌለበት ሲሞግቱ የነበሩት አቶ ልደቱ፤ ትህነግ መቀሌ ሆኖ “ከመስከረም 30 በኋላ ቅቡል መንግስት የለም” የሚል አዋጅ ካሰማ በኋላ “ የሽግግር መንግስት ይቋቋም” በሚል የመሃል ፖለቲካውን ለመምራት ከነ ጃዋር መሐመድ ጋር ግንባር ገጥመው እንደነበር ይታወሳል። በወራት እድሜ ውስጥ ለተቀያየረው አቋማቸው በወጉ ተጠይቀው ምክንያታቸውን ሲያስረዱ ያልተሰሙት አቶ ልደቱ፣ ባሰራጩት ሰፊ ጽሁፍ ራሳቸውን ከፖለቲካ ማሰናበታቸውን አስታውቀዋል።
“በመጨረሻም ከአቅም በላይ በሆነ የጤና ምክንያት ቢሆንም ሀገራችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ዋጋ የሚከፍልላት ዜጋ በሚያስፈልጋት በአሁኑ ወቅት ለጊዜውም ቢሆን ከትግል ተሳትፎዬ ለመታቀብ በመገደዴ፥ የትግል አጋሮቼንና የዐላማ ደጋፊዎቼን ሁሉ ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ” ያሉት አቶ ልደቱ፣ ስንብቱን የመረጡት በጤና እክል የተነሳ ነው ብለዋል።
ሆኖም በእስር በነበሩ ጊዜ የልብ በሽታ እንዳልባቸውና ውድ አሜሪካ ለመሄድ እያሉ መታሰራቸው አገባብ አይደለም በማለት የፓርቲ ሰዎቻቸው መንግሥትን ሲሞገቱ ነበር። በእስር እያሉ የጤና ዕክል ቢገጥማቸው መንግሥትን ተጠያቂ እንደሚያደርጉ ሲናገሩ ነበር። ሆኖም አቶ ልደቱ ከእስር ከተለቀቁ ወራት የተቆጠሩ ቢሆንም ለልብ ሕክምና ወደ ውጭ እስካሁን እንዳልሄዱ ይታወቃል። ከዚያ ይልቅ የሚለውን መጽሃፋቸውን በማሳተም ተጠምደው እንደ ነበር ይታወቃል።
“… ከእኔ ብዙ እንደምትጠብቁና ለእኔ ለራሴ እንደሆነብኝ ሁሉ ለእናንተም ይህ ክስተት ድንገተኛ መርዶ እንደሚሆንባችሁ ስለምገነዘብ ነው። ወደፊት የጤና ሁኔታዬ ተሻሽሎ እስከመጨረሻው በፖለቲካ ሒደቱ ለመቀጠል ለራሴ የገባሁትን ቃል ለመፈጸም ፈጣሪ ዕድል እንደሚሰጠኝ ተስፋ እያደረግኹ ሀገራችን ኢትዮጵያ መልካሙ ሁሉ እንዲገጥማት ያለኝን ልባዊ ምኞት በዚህ አጋጣሚ እገልጻለሁ” ሲሉ ደብዳቤያቸውን የቋጩት አቶ ልደቱ፣ እሳቸው በሚሉት ደረጃ ለኢትዮጵያ ወሳኝና ለዘመኑ ቀውስ መድሃኒት የሆኑ ዜጋ ስለመሆናቸው የሚያሳይ ታሪካቸው ለማሳያነት አልጠቀሱም።
በጽሁፋቸው ኢትዮጵያ በኤርትራና በሱዳን መወረሯን አንስተው “ይህ የመበታተን ምልክት ነው” ብለዋል። የኢትዮጵያ ጦር ላይ ክህደት ተፈጽሞ በተኛበት መጨፍጨፉን አጉልተው ሲነቅፉ ያልተሰሙት አቶ ልደቱ ዛሬም ኤርትራን ወራሪ አድረገው መሳላቸው አግራሞትን ፈጥሯል።
“ከሞት የተረፈው የኢትዮጵያ ጦር እርቃኑንን በርሃብና በውሃ ጥም ተሰቃይቶ ኤርትራ ሲገባ ነብስ እንዲዘራና ሃፍረተ ሰውነቱን እንዲሸፍን ያደረጉት የኤርትራ ሰራዊትና መንግስት ናቸው” በሚል የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የደረሰባቸውን ግፍ በተናገሩት መጠንና ህዝብ ቁጣውን በገለጸበት ልክም ባይሆን አቶ ልደቱ ለትህነግ ወግነው መቆማቸው ደጋፊ አልባ አድርጓቸዋል እየተባለ ነው። በተለይ ከእስር ሲፈቱ ከእስርቤት ደጅ ጀምሮ ይሆናል ብለው የጠበቁትን የሕዝብ ድጋፍ ባለማግኘታቸው ፖለቲካቸው ድጋፍ እያጣ ለመሆኑ የማነቂያ ደወል እንደሰጣቸው በቅርብ ያሉ ሰዎች ይናገራሉ።
ተወለድኩበት የሚሉት አካባቢ ሳይቀር በዚሁ ከትህነግ ጋር ያላቸው ትሥሥር ያስከተለባቸው ጥላቻ ድጋፍ እየነሳቸው መሆኑንን በመረዳታቸው ከጤና ችግራቸው ጋር አዳምረው ከፖለቲካው ዓለም ለመሰናበት መወሰናቸውን ከጽሁፋቸው ግርጌ አስተያየት የሰጡ አስታውቀዋል። “ሲሻለኝ እንደምመለስ ተስፋ አደርጋለሁ” ያሉትን አስመክልቶ “አቶ ልደቱ አሁን የደበዘዘውና የሰከነው የውስጡ ፖለቲካ ሲጋጋል እንደሚሻላቸው አመላካች ነው” የሚል ሽሙጥ ቢጤ አስተያየት ተሰጥቶበታል። በመረጋጋት ላይ ያለው ፖለቲካ ባንድ ጊዜ መጦዝ ቢጀምርና ትርምስ ቢከሰት ልደቱ በፊትአውራሪነት ብቅ እንደሚሉ በርግጠኝነት አስተያየት የሰጡም አሉ።
አቶ ልደቱ “የትግራይ ህዝብና ትህነግ አንድ ናቸው” በሚል ድምዳሜያቸው ይታወቃሉ። በዛሬ የመለያያ ጽሁፋቸው መንግስትን ለአንዴና ለመጨረሻ በሚመስል መልኩ ደብድበዋል። ህገ መንግስቱ እንዲቀየር ጥሪ አቅርበዋል። የህገመንግስት ረቂቅና አፈጻጸም መጽሃፍ እያዘጋጁ ስለሆነ ተቃዋሚዎች እንደ ሰነድ ተጠቅመውበት የመታገያ አጀንዳቸው እንዲያደርጉት ታቦት ሳይጠሩ ተማጽነዋል። በተዘዋዋሪ ቀጣዩ መጽሃፌን ግዙ ብለዋል።
የትህነግ መክሰም በኢትዮጵያ በርካታ ችግሮችን አብሮ እንደሚያከስም በፖለቲካው ዙሪያ ያሉ አስተያየት ሰጥተዋል። በርካታ ደጋፊዎቻቸውም ተስፋ እንደሚቆርጡ አመልክተዋል።
ሌላው የተነሳው ጉዳይ አቶ ልደቱ ከፖለቲካ መሰናበታቸውና የእነ ጃዋር መሐመድ ምግብ መጀመር ግጥምጥሞሽ ነው። አቶ ልደቱ “ከመስከረም ሰላሳ በኋላ መንግስት የለም” የሚለውን ዘመቻ ሲቀላቀሉ ከነ ጃዋር ጋር ገጥመው የነበረ መሆኑንን፣ በኦሮሞ ሚዲያዎች ላይ ከጃዋር ጎን በመሆን በህብረት ዘመቻውን ማራመዳቸውን ያታወሱ፣ ሁሉም ነገር ማክተሙና እነ ጃዋርም ምግብ ለመብላት መወሰናቸው አቶ ልደቱን አዲስ የሚጠበቅ ተስፋ አሳጥቷቸዋል። በዚህም የተነሳ ስንበቱን ለጊዜውም ቢሆን መርጠዋል የሚሉ አስተያየቶች ተሰምተዋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጃዋር “የአንድነት ሃይሎች ከዱኝ” መናገሩን አስመልክቶ ከዚህ በፊት የዘገበው እዚህ ላይ ይገኛል። (ethio12.com)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ነፃ ሕዝብ says
ሠላም ጎልጎሎች ፦ ዝንጀሮ የቂጧ መላጣ አይታያትም ይባላል ፥ እናንተም የፋሽስታዊና አፓርታይዳዊ ኦሮሙማው አገዛዝ ቁንጮ ከሆነው ግራኝ አህመድ አሊ ጀምሮ የነፍሰ_ገዳዩ ህወሃት ሎሌዎችና ተላላኪዎች እንዳልነበራችሁ ልደቱን እንደ ሰይጣን አድርጋችሁ ትቆጥሩታላችሁ ፥ ለፋሽስቱና ነፍሰ_ገዳዩ ህወሃት ከልደቱ በበለጠ እናንተ አልነበራችሁም እንዴ የምትቀርቡትና አገልጋይ የነበራችሁት ? ጎልጉሎች ኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥት አለ ብላችሁ ተቃዋሚውን ስታብጠለጥሉ በእጅጉ ትገርማላችሁ ፥ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፋሽስቱና አፓርታይዳዊ አገዛዝ ብሎም ነፍሰ_ገዳዩ ኦሮሙማ መሆኑን የዓለም ሕዝብ የሚያውቀው ሃቅ ነው ፥ ጎልጎሎች በምሥራቅ ወለጋ በየቀኑ የሚገደለውን አማራ ይታያችሁዋልን ? እናንተ የነፍሰ_ገዳዩና ዘረኛው የአብይ አህመድ አሊ አለቅላቂዎች ናችሁ ፥ ባለፈው ጊዜ ለአብይ ወግናችሁ እውቁ የፖለቲካ ተንታኝ የሆነውን ኤርምያስ ለገሰን ስታብጠለጥሉት ነበር ፥ በፍጹም ሃፍረት የማይሰማችሁ ጉደኞች ናችሁ ፥ በኢትዮጵያ ውስጥ ማንም ፖለቲከኛ ነኝ የሚል ሁሉ ቢጨፈለቁ አንድ ልደቱ አያሌውን የሚያህል አይኖርም ፥ ልደቱ ያነበበ እና ወቅቱን ያገናዘበ እውቅ ፖለቲካኛ ነው ፥ ለህክምና ወደ አሜሪካ እንዳይሄድ የከለከለው የእናንተው ነፍሰ_ገዳዩ አብይ መሆኑን እያወቃችሁ በመጽሐፍ ሽያጭ ላይ ተጠምዶዋል ትሉታላችሁ ፥ መጽሐፍ የሚፅፍ ጭንቅላት ያለውና እውቀት ያለው እንጂ እንደ እናንተ ያለው ዲጂታል የኦሮሙማው ተቀላቢ አይደለም ፡፡
Sule says
ትክክል!!
አሌክስ says
ልደቱ ከሞተ ሰንብቶል. ዛሪ ሰለሞተ ግለሰብ መፃፍ ወይም ግዜ ማባከን ተገቢ አይደለም. አሁን ሐገራችንን ለመከፋፈል የሚፈልጉ ጠላቶቻ ችንን በመዋጋት ግዜአችንን እንጠቀም.
We ana Anaa says
Selabi bet buda geba!! Lidetu ( aselchi achberbary polotikegna)
Please lidetu don’t try to go to dedebit it should be enough to you here!
Shewa rega says
ትክክል ብልሀል አሌክስ እንዴት የሞተ ሬሳ ለማንቀሳቀስ ይሄ ሁሉ ሽርጉድ ??!!!
Tesfa says
የሃበሻው ፓለቲካ ሸፋፋና ገዳዳ ነው፡፡ አንድም ቀን ሞልቶለት አያውቅም፡፡ ወፌ ቆመች ሲባል ተመልሶ በአፍ ጢሙ የሚደፋ፤ የቀደመው ያቆመውን የቀኑ አለቃ የሚንድበት በዙር የመገዳደል ፓለቲካ ነው፡፡ አቶ ልደቱ ወያኔና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው ማለቱ ወደውም ሆነ ተገደው የትግራይ ህዝብ 45 ኣመት ሙሉ ወያኔን ተሸክሞት ኖሯል፡፡ አሁንም የወያኔን ሞት ቀድመው ያወጅ ሁሉ ቢላሾች እንደሆኑነ ቀን ያሳየናል፡፡ ወያኔ በተንኮልና በማፍረስ ሥራ የተካነ ድርጅት ነው፡፡ ያው ዛሬም ጠበንጃ ይዞ ዘጥ ዘጥ ማለቱ አይቀሬ ነው፡፡ በመሰረቱ ወያኔ ማለት ከጀርመኑ ናዚ፤ ከጣሊያኑ ሞሶሎኒና ግራዚያኒ የሚስተካከል የጨካኞች ስብስብ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሰሩትና የሚሰሩት መሰሪ ሥራ የሚመሰክረው በዘራቸውና በቋንቋቸው የሰከሩ ታላቋን ትግራይ ለመመስረት ታስቦ ለ 27 ኣመታት በሰፋ ዳቦ ተታለው ምድሪቱን ሲመዘብሩ ኑሮው መቀሌ ከተሰባሰቡ በህዋላ ለውጊያ ሲዘጋጅ እንደ ነበር በሰሜን እዝ ላይ ያደረሱት “መብረቃዊ ጥቃት” ዛሬ ላለንበት ቀን አድርሶናል፡፡
አሁን በሱዳን በገዳሪፍ ግዛት ከሱዳንና ከግብጽ ሃይሎች ጎን ተሰልፈው እንደገና ለመፋለም ወደ 80 ሺህ ጦር እንዳዘጋጅ ይነገራል። የኢትዮጵያን አንድ መሆን ከሚጠሉ ነጮችና የአረብ ሃገሮች ጋር ዳግመኛ በመቆራኘት የሌለ ነገር ሆነ እያሉ ከፍለው በማሳመንና አልፎ ተርፎም የዘር ማጥፋት ተፈጸመብን በማለት መጮሃቸው ምን ያህል የዲፕሎማሲ ስራቸው ሥር የሰደደ መሆኑን ያሳያል። እነ ስዬ አብርሃ በእርጅና ሱዳን ጠረፍ የወሰዳቸው ያ በፊትም ከከተማ ወደ ጫካ የወሰዳቸው የዘር ፓለቲካ እንጂ ለሰው ልጆች ሰላምና ልዕልና ወያኔዎች አንድም ቀን አስበው አያውቁም። ያልገባቸው ነገር ግን መለስ ብሎ የሃበሻውን ፓለቲካ ላየ በዙር መገዳደል እንጂ የብሄር ነጻነት ፈላጊዎች ባርነትን እንጂ ነጻነትን አመንጭተው አያውቁም። ዛሬም ውጊያ፤ ነገም ተነሱ፤ ሞትና ለቅሶ ለጥቂቶች ተድላና ደስታ እልፎች የሚሞቱባት ሃገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት። ጃዋር፤ ልደቱ እና ወያኔ በሃሳብ ተስማሙ ከተባልን ለማፍረስ እንጂ ሃገር ለማቆም እንዳልሆነ የታወቀ ነገር ነው። ዛሬ በኦሮሚያ ክልልና በሌሎችም የሃገሪቱ ምድር ሰው የሚሸራከተው በክልል ዙሪያ በሚነሳ የብሄር ግጭት ምንጩ አዲስ አበባ ላይ ቁጭ ብለው ሰው እንዲገዳደል አይዞአችሁ የሚሉ ሁሉ ናቸው። ገዳዪ ተከፋይ፤ ከሞት የተረፈው ተፈናቃይ ከሆነ ዘመን አልፎ እያለ አውሮፓና አሜሪካ በትግራይ የአዞ እንባ ሲያፈሱ ማየት ለጤና እንዳልሆነ የሰነበተ ያየዋል። የአለም ፓለቲካ ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ በሃያላን መንግስታትና በተለጣፊ ሃገሮች መካከል ያለው ግብግብ በረድ ያለ ቢመስልም የሚናቆሩበት ጉዳይ አጥተው አያውቁም። ሊቢያ፤ የመን፤ ኢራቅ፤ ሶሪያና ሌሎችም ሃገሮች በእነዚህ ሃይሎች ተፈረካክሰው በመንገዳገድ ላይ ይገኛሉ። አሜሪካ ማለት ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ያለውን የሰው ልጆች ጭቆናና ግፍ በነዳጅ ዶላር ሸፍኖ የመን ከምድርና ከሰማይ እንድትደበደብ ስንቅና ትጥቅ የሚያቀብል መንግሥት ነው። ዞሮ ተመልሶ ደግሞ ለተራበ ስንዴ ያቀብላል። ይህን እንዴት ቆሞ የሚሄድ ሰው መረዳት ይሳነዋል? ለኢትዪጵያም የታለመላት ማፈራረስ ነው። ጣሊያን በመርዝ ጋዝ ህዝባችን ሲያጠቃው ቆመው ያዪ ሃገራት ናቸው ዛሬም ከወያኔ ጎን ቆመው ኡኡታ የሚያሰሙት። ይህ ግን ለትግራይ ህዝብ አዝነው ሳይሆን የቆመው ሁሉ ዶጋ አመድ ሆኖ እነርሱ ነፍስ አትራፊ ሆነው ለመታየት ነው።
የዶ/ር አብይ መንግስትና አረማመድም ከቀን ወደ ቀን እየተወላገደ ሄዷል። ወንጀል የሰሩ ሰዎችን እየለቀቁ ያለ ምንም መረጃ ሌሎችን ጨለማ ውስጥ ማጎሩ ወያኔያዊ ነው። ለነገሩ ጠ/ሚሩ ቢሆን ከወያኔ የክፋት ጆኒያ አፈትልኮ የወጣ አይደል። ሰው ደንዝዟል። ሰው ሞተ ሲባል ተዳረ የሚሉት ይመስለዋል። ለነገሩ ዘሩ ተጠይቆ ለቅሶ በሚደረስበት ምድር የሰው ሰውነቱ ከሞተ ቆይቶ የለ። ብቻ የዓረብና የነጭ ተላላኪዎች፤ ወገናችን ተጸያፊዎች ሆነን የት ነው የምንደርሰው? አሁን ማን ይሙት ኢትዮጵያ ያለ ትግራይ ኖሯ ታውቃለች? ትግራይ ያለ ኢትዮጵያስ የሚተርፋት ምንድን ነው? የጅል ፓለቲካ ያዘው ጥለፈው ነው። ሁሌ መኮነን፤ ሁሌ ያልተረጋገጠ ነገር መለጣጠፍ በሰው ደምና ህይወት መነገድ የቀኑን በይ ሌላ በላተኛ ሲበላው ያ ኡደቱ ይቀጥላል። ማነህ ባለሳምንት? ተነሳና ቁም! ቆይተን እንይ። በቃኝ!
ነፃ ሕዝብ says
አንዳንድ ጊዜ ሆድ ሲሞላ ህሊና ይታወራል ይባላል ፥ የብልፅግና ካድሬዎች የፋሽስቱ ህወሃት ግልባጭ የሆነው አፓርታይዳዊ አገዛዝ ኦሮሙማው ሲነካባቸው የማይዘላብዱት መዓት የለም ፥ ምክንያቱም መሬት ሻጭ ካድሬ ሳይሰራ ምላሱን እየቆላ በገፍ የሕዝብ ገንዘብ ስለሚከፈለው ለሥርዓቱ ዐይንና ጆሮ ሆኖ ያገለግላል ፥ ካድሬ የሕዝብን ቆዳ ገፎ የሚያስቀር ከሃዲ ነው ፥ ካድሬ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሲቃይና የመጀመሪያ ተጠያቂ መሆኑ ይታወቃል ፥ በየሥርዓቱ ካድሬ የሚሆኑ እውቀት የሌላቸውና ፍጹም ሆዳሞች ሲሆኑ የሕዝብ እልቂትና እንግልት የማይሰማቸው ከርሳሞችና ውሸታሞች ናቸው ፥ ትናንት የገዳዩና ፋሽስቱ ህወሃት ካድሬዎች የነበሩ ዛሬ ተገልብጠው ለተረኛው ዘረኛና ነፍሰ_ገዳይ ብሎም ፋሽስት ኦሮሙማው አፓርታይዳዊ አገዛዝ ህሊናቸውን ሸጠው ይህንንም ገዳይና አስገዳይ ሥርዓት ለማስቀጠል ፋሽስቱ ኦሮሙማው የሚጠላውን ሁሉ እየተከተሉ ሲያብጠለጥሉና ሲያራክሱ ይታያሉ ፥ ያም ሆነ ይህ የአብይ ሥርዓት በአፍጢሙ ሲደፋ እናንተም አብራችሁ ትደፏታላችሁ @