• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሓት ተሠረዘ!!!

January 18, 2021 01:32 pm by Editor 1 Comment

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህግ ከተቋቋመባቸው ዋና ዋና ተግባራት አንዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ፥ ቁጥጥር እና ክትትል ነው። በመሆኑም በምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት ፓርቲዎች የተለያዩ መስፈርቶችን ማሟላታቸውን ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።

በዚህም መሰረት ቀደም ብሎ መስፈርት አሟልተው ምዝገባቸው የተጠናቀቀ እና በሂደት ላይ ያሉ ፓርቲዎች ዝርዝርን ማሳወቁ ይታወሳል። ቦርዱ ከዚህ ቀደም ውሳኔ ያልሰጠባቸው እንዲሁም የተጠየቁትን ማብራሪያዎች ያቀረቡ ፓርቲዎችን አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል።

1. ቦርዱ ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ሕወሃት) የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል ወይ የሚለውን ሁኔታ ለማጣራት በፓርቲው የተሰጡ መግለጫዎችን እና በይፋ የሚታወቁ ጥሬ ሃቆችን በማቅረብ ፓርቲው ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ መሣተፉን አረጋግጧል። በተጨማሪም ፓርቲው መልስ የመስጠት እድል እንዲኖረው በማሰብ በፓርቲው እና በቦርዱ መካከል አገናኝ በመሆን ይሰሩ የነበሩትን የፓርቲውን የአዲስ አበባ ቢሮ የቀድሞ ተወካይ ለማነጋገር ጥረት ያደረገ ሲሆን ተወካዮም ፓርቲውን መወከል እንደማይችሉ ገልጸዋል። በመሆኑም፦

ሀ. በአዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 98/1//4/ መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲውን ህጋዊ ሰውነት ሰርዞታል። በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 99 መሠረት የፓርቲው ኃላፊዎች በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንደማይችሉም ውሳኔ አስተላልፏል።

ለ. የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በፓርቲው እና በፓርቲው አመራሮች ላይ በሚያደርገው ምርመራ የሚገኙ በህወሐት ሥም የተመዘገቡ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ንብረቶችን በተመለከተ ያገኘውን ዝርዝር መረጃ እንዲልክ ቦርዱ ጥያቄ አቅርቧል።

ሐ. የፓርቲው ንብረት በአዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 99/2/ መሠረት ንብረቱ ተጣርቶ ዕዳ ካለበት ለዕዳው መሸፈኛ እንዲውል፤ ይሁንና እዳውን ሸፍኖ የሚተርፍ ንብረት ከተገኘ ቀሪው ገንዘብና ንብረት በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 99/3/ መሠረት ለሥነ ዜጋና መራጮች ትምህርት እንዲውል ቦርዱ ወስኗል። (ምንጭ የምርጫ ቦርድ ፌስቡክ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: meles zenawi, operation dismantle tplf, sibhat, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    January 20, 2021 09:16 am at 9:16 am

    በቅርቡ ከአንድ የትግራይ ተወላጅ ጓደኛዬ ጋር (አባቱን ወያኔ የገደለበት) ሰፋ ያለ ጫወታ ስንጫወት የትግራይ ህዝብና ወያኔ አንድ አይደሉም አለኝ። አይ ናቸው አልኩት። በጋለ የሃሳብ ንትርክ መካከል እንዲህ ብየ ጠየኩት። 45 ዓመት ሲቀልድበት የኖረን አንድ ድርጅት ያልተቃወመ ህዝብ እንዴት ነው ወያኔ አፍቃሪ አይደለም የምትለው ስለው። ኦ አሁን ራሴን አሳመምከኝ። ሰሞኑን ሃገር ቤት ደውዬ ነበርና ስንጫወት አንድ ወያኔ ይሻለናል አሁን ከሚደረገው ነገር ቢለኝ እንዴ እንዴት እንዲህ ትላለህ ስለው “ያው የዘረፉትን ዘርፈው የቀረውን በልተን እንድናደር ይበቃ ነበር አሁን ጭራዙን ጾም አዳሪዎች ሆንን” በማለት መለሰልኝና የለሆሳስ ወሬውን ጉልበቱ እንደራደው ሰው ጨርሶ አወራኝና አትሰማኝም ጮክ ብለህ ተናገር እያልኩ በዚያው ተቋረጠ። ሌላ ጥሪ መቶበት ይሆናል። አይ ጊዜ! ጊዜ ወልጋዳ ነው። እስቲ የሰሜኑን ጦር ወያኔ በሸር ከውስጥና ከውጭ ካጠቃው በህዋላ ያለውን ጉዳይ ከዓይን እማኞች እኔ ራሴ ያሰባሰብኩትን ላጫውታችሁ እና መንግስትን ወረፍ አርጌ ሃሳቤን አጠቃልላለሁ።
    የአይን ምስክር – በብዙ መቶ የምንቆጠር የበታችንና የበላይ መኮንኖች በእግር ጉዞ እንደ ቀንድ ከብት እየተገፋን እንጓዛለን። በዚህ መካከል ተቀመጡ ተባለና በረድፍ በረድፍ ሆነን ተቀመጥን። ድንገት ሳናስበው አንድ የወያኔ ታጣቂ ከተቀመጥነው መካከል አንተ ውጣ። አንቺ ውጪ እያለ እያስወጣ ከተቀመጥነው ፊት ለፊት አስቆማቸው። እነዚህ አማራ ይመስላሉ በማለት በሩምታ ተኩስ ሁሉንም ገደሏቸው። ይህን ያጫወተኝ አንድ ሻለቃ ነው፡፤ አሁን ስራው ላይ ተመልሶአል። ከዚያ እኛም ይህ አይቀርልንም በማለት 15 የምንሆን አመለጥን ይላል ሻለቃው። ገበሬዎች አይተውን ኑረው ሄደው ይናገሩ እና በዚህም በዚያም ከበው ተከፋፍለን ስንሄድ ስለነበር ከፊታችን የቀደሙትን በመያዝ 7 ቱን ረሸኗቸው፡ ገበሬው የእኛን ቡድን ስላላዪ ያመላከቷቸው እነርሱን ብቻ በመሆኑ እኛ ተፍጨርጭረን ለመትረፍ በቃን በማለት በሲቃ አጫውቶኛል። በእኔ እምነት የትግራይ ህዝብና ወያኔ አንድ ናቸው። ዝም ብሎ ለፓለቲካ ፍጆታ አይደሉም የሚባለው። ይህ አባባል በተግባር ያልተመሰከረ የቀበሌ ጡርንባ ነው። ይህ ሲባል ቅን አስተዋይ፤ ሃገራቸውን የሚወድ፤ ለእምነታቸው የሚያድሩ፤ የትግራይ ተወላጆች የሉም ማለት አይደለም። በ 45 ዓመቱ የገደልና የከተማ ትግል ውስጥ ከሞት የተረፉትንና ከወያኔ ቁራሽ ተካፍይ የሆኑትን ጨምሮ ይህ ድርጅት ከተፈጠረ በህዋላ የተወለድት ሁሉ ጭራሽ ብሄራዊ ወይም አለም አቀፋዊ እይታ የላቸውም። ለዚህ ነው ዛሬ በትግራይ በሴራ የተደበደበውን ጦር እንደ ጠላት የሚቆጥሩት። ወያኔ ያጠፋውና የሚያበላሸው ሁሉ ለአፍቃሪ ወያኔዎችና ስለ ትግራይ ብቻ ለሚያስቡ ጠባቦች ጥፋት አይደለም። አጭዶ፤ ት/ቤት ሰርቶ/አንበጣ አባሮ፤ ተጋብቶና ተዛምዶ ለዘመናት የኖረውን የሰሜን ጦር ከውስጥና ከውጭ ወያኔ ሲያጠቃው፤ ሰዎች በዘራቸው እየተለዪ ሲረሸኑ ለምን ብሎ የጠየቀ የለም። ባጭሩ ምድሪቱ በወያኔ የክፋት ፓለቲካ የተበከለች ናት። 45 ዓመት ስለ ትግራይና ለትግራይ እያለ ከበሮ ይዞ ይዘል የነበረ ድርጅት ከሥሩ ሲመነገል እንዴት ነው የትግራይ ህዝብ በወር ብቻ ረሃብተኛ የሚሆነው? የታለ የምግብ ዋስትናው እቅድና ፕላን? አሁን በመቀሌና በዙሪያዋ የወታደሩን እንቅስቃሴ ለወያኔ ትራፊ ታጣቂዎች እየጠቆሙ የሚያስገድሏቸው እነማን ናቸው? መንግሥትስ እከሌን ከገደል አወጣን እያሉ ወሬ ከመንዛት ሞቱ፤ ተደመሰሱ ያልናቸው ሳናስበው ተኩስ ከፍተው ይህን ያህል ወታደሮች ገደሉብን ለማለት እንዴት ይሳነዋል? የዚህ ሁሉ ሴራና ገመና ዋንኛ ተዋናዪች መሳሪያ አስረክበናል ያሉ፤ የሚሊሻ፤ የፌዴራልና የክልል የጸጥታ ሃይል መለዪ የለበሱ የወያኔ ተባባሪዎች ለመሆናቸው ምስክር አያሻም። በመቀሌ ከተማና በዙሪያዋ በመሳሪያ የታገዘ ግድያ፤ ዝርፊያ፤ ሴት መድፈር፤ ማፈን የሚያካሄድት የወታደር ልብስ ለብሰው ድምጽ በማያሰማ መሳሪያ እየታገዙ ነው። ይህ ደግሞ ለወያኔ ይኸው እኛ ከሌለን ህግና ሰላም ፈረሰ ለማለት አማራውን በሌሎቹ ክልል እንዲጨፈጨፍ በማቀድ ከሚያካሂድት እቅድ ጋር ይያያዛል። በወገኑ ደም የሚነግደው ወያኔ በዶ/ር አብይ መንግስት ሁሌ መቆላመጡ ግራ ያጋባኛል። የገደለ፤ ሃገር ያፈረሰ፤ በዘርና በጎሳ ሃገር ቆራርጦ እኔን ብቻ እዩኝ ያለ ድርጅት መደምሰስ አለበት። እጅ ስጡ፤ በሰላም ኑሩ የሚለው ጥሪ ሁሉ ለወያኔ የፍርሃት ምልክት እንጂ ሌላ መስሎ አይታየውም። በየጊዜው ይህን ገደልን፤ ያን ያዝን እዚህ ጋ ተደመሰሱ የሚባለው ነገር ሁሉ ለይደር ቢቆይ መልካም ነው። የተያዘም፤ የሞተም፤ የፈረጠጠም፤ በውጭ ሃገር ሆነው አይዞህ የሚሉትም፤ ከሱዳን ጎን ተሰልፈው ወረራ የሚያደርጉትን ሁሉ ለይቶ በመያዝና በማወቅ በመረጃ ሁሉንም አፈር ካለበሱ በህዋላ ነው ኦሮማይ ማለት እንጂ እንዲህ የነጠብጣብ ወሬ ማናፈስ ወያኔ የራሱን የስለላ መረብ ለመቀጠል ይረዳዋል እንጂ ግፍ ለደረሰበት የወገን ጦር የሚጠቅም ፋይዳ የለውም። ሙያ በልብ ነው ይሉ የለ አበው።
    በመጨረሻም ምንም ይሁን ምንም አንድ ህዝብ ሰላምን የሚሻው ራሱ ሲሻና ሲፈልግ እንጂ በሌላ ሃይል ተገዶ ወይም ተገፍቶ እንዳልሆነ ታሪክ ያስተምረናል። ጠበንጃ ማንገትን እንደ ቁም ነገር የሚቆጥር ትውልድ፤ ወንድምና እህቱን በዘርና በቋንቋ መዝኖ አንገት የሚቀላ ፍጡር ስለ ሰላም ያስባል ብሎ ማመን ጅልነት ነው። የመጽሃፉ አር ዕስት ተረሳኝ እንጂ አንድ የቀድሞ ሰው የጻፉት ያ መጽሃፍ ስለ ሃበሻው የፓለቲካ ፍትጊያ ይተነትናል። በመዝጊያው እንዲህ የሚለው ቃል ትዝ ይለኛል “ሲገድሉም ሲገዳደሉም ኖሩ” ይላል። ለዛ ነው ውጭ ሃገር ላይ ቁጭ ብለው በስማ በለው ፓለቲካ በዘሩና በቋንቋው ሰክሮ ሰው እንዲጫረስ የውሸት ፕሮፓጋንዳ ሲነዙ የሚውሉት። ያሰለቻል። ሰው እንዴት እድሜ ልኩን ያዘው ጥለፈው ሲል ይኖራል? አባካችሁ እናንተ መንግስት ነን የምትሉ ከማይክሮፎንና ከሚዲያ መስኮቶች ራቁ፤ ሞቱ፤ ተያዙ፤ ተገደሉ፤ ተደመሰሱ አትበሉን። ስራችሁን ስሩና ከእናንተም የሞተውን፤ ወያኔ በዚያች ሰአት ያደረሰውን የንበረት ውድመትና የሰው ህይወት ጥፋት ከተረፉት ሰዎች በመረዳት፤ ሌሎች መረጃዎችንም በማከል በመጽሃፍ መልክ ብታወጡት የተሻለ ይሆናል። ሌላው ሁሉ ነገር በማሰሮ ውስጥ አስገቡትና እዚያው ይብላላ። የፈጠራም ሆነ እውነት ነክ ወሬ ስልችቶናል። የህዝባችንን እንባ አስቁሙ። ያ ነው ጀግንነት። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ February 15, 2021 11:46 pm
  • የትግራይ ገበሬና የከተማ ነዋሪ በሠራዊታችን ላይ አንድ ጥይት አልተኮሰም – ሪር አድሚራል ክንዱ February 4, 2021 01:51 pm
  • ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው February 4, 2021 11:10 am
  • ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ February 4, 2021 08:48 am
  • በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት የሚያጣራ ግብረ ኃይል መቀሌ ገባ February 3, 2021 12:06 pm
  • ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ February 3, 2021 10:29 am
  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule