በጁንታው መሪ ደብረጺዮን ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተደረገ ፍተሻ በኮንክሪት የተገነባ ዋሻ ተገኘ። የጁንታው መሪ ህዝቡን አለንልህ እያሉ ለማምለጫቸው ያዘጋጁት ይህ የኮንክሪት ዋሻ ውስጥ ለውስጥ እስከ 300 መቶ ሜትር እንደሚረዝም ነው የተገለጸው። በትግራይ ክልል እየተከናወነ ባለው የህግ ማስከበር ዘመቻ በጽ/ቤቱ በተደረገ ፍተሸ ይህ የኮንክሪት ዋሻ ተገኝቷል። ሻለቃ አምባቻው እንደገለጹት፣ ከመንግስት የህግ ማስከበር ዘመቻ ከተጠናቀቀ በኃላ የሕውሃት ጁንታ መሪ ጽ /ቤትና እኖርበታለሁ ፣ አመልጥበታለሁ ያሉት ዋሻ በቁጥጥር ስር ውሎ የአደባባይ ሚስጥር ሆናል። ምናልባት ቢሮው ቢመታ ወይም ሊይዙን ቢመጡ በዚህ በኩል ለማማለጥ ያስችለናል ብለው የሰሩት ነው። https://www.youtube.com/watch?v=KV1rVcsTEsA የጁንታው መሪ በዋናው በር … [Read more...] about የደብረጽዮን ዋሻ
Middle Column
ባለ ከዘራው ኮሎኔል
ፊታቸው ላይ የአልበገርም ባይነት ስሜት ጎልቶ ይነበባል፤ እያነከሱም ቢሆን ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሳሉ። መገናኛ ራዲዮናቸውን እና የምርኩዝ ከዘራቸውን ይዘው የጁንታው ቡድን አመራር ያለበት ቆላ ተንቤን አቅራቢያ በምትገኝ ሰዋራማ ስፍራ ላይ ጦሩን እየመሩ ይገኛል። ኮሎኔል ሻምበል በየነ ይባላሉ። በቆሙበት የውጊያ ትዕዛዝ እየሰጡ ኮስታራ ፊታቸውን ወደእኛ ዘወር አደረጉ። ቆስለው አልታከምም በማለት በወኔ እየመሩ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አመራር መሆናቸውን ሰማንና ታሪካቸውን እንዲያካፍሉን ጠየቅናቸው። ድንገተኛ ፈገግታ እያሳዩ ቀድሞም የጁንታው አባላት ውጊያ ሰራዊቱ ላይ ሊከፍቱ እንደሆነ ጥርጣሬ ነበረኝ በማለት በተረጋጋ ስሜት ትውስታቸውን ማጋራት ጀመሩ። እኔ የ31ኛ ክፍለጦር ምክትል የኦፕሬሽን አዛዥ ነበርኩ ዋና አዛዡ ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ቀደም ብሎ የተወሰኑ … [Read more...] about ባለ ከዘራው ኮሎኔል
ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው
በሀገር መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር በምትገኘው ማይጨው ከተማ ህዝቦቿ ወደሙሉ የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ተመልሰዋል። (መረጃውን ለtikvahethiopia ያደረሰው አበበ ሰማኝ ከማይጨው ነው)። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው
ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው
በአገር ክህደት እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በነበሩ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው፦ ኮማንደር ሰለሞን አብርሃ ብስራት 2. ኮማንደር ሀይለማርያም ብርሃኔ ገ/ማርያም 3. ም/ኢ/ር ክብሮም ገብሩ ገ/እግዚአብሄር 4. ም/ኢ/ር አረጋዊ ገ/ሂወት አስፋዉ 5. ረ/ኢንስፔክተር ገዛኢ ገ/ሂወት ገ/ስላሴ 6. ረ/ኢንስፔክተር ተስፋ ኪሮስ ግደይ 7. ረ/ኢንስፔክተር አርአያ ገ/አናንያ ኪዳኑ 8. ረ/ኢንስፔክተር ሰለሞን ወላይ ወ/አብዝጊ 9. ዋ/ሳጅን ሀይላይ ወልዱ ገ/ማርያም 10. ዋ/ሳጅን ሀፍቱ ካህሳይ አብርሃ ናቸው። በመሆኑም መላው የሃገራችን ህዝቦች በተለይም ደግሞ ሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ፤ እንዲሁም የሀገር መከላከያ … [Read more...] about ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው
“የማይካድራ ጭፍጨፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብዓዊ፣ ስነልቦናዊ ቀውስና ጥልቅ ሀዘን ያስከተለ ነው” – ዶ/ር ዳንኤል
በህወሓት ጁንታ ቡድን ላይ ህግ የማስከበር ዘመቻ መጀመርን ተከትሎ በማይካድራ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው እልቂት በነዋሪዎች እና በተመልካች ላይ አስከፊ የስነ ልቦና ቀወስ ሊያስከትል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር (ኢሰመኮ) ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አስታወቀዋል። ዶክተር ዳንኤል የማይካድራ ጭፍጨፋ አስመልክቶ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፣ በማይካድራ የተፈጸሙ ግፍ በቁጥር ከሚገለጸው ሪፖርት ባሻገር በነዋሪዎች ላይ ሰብዓዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ እንዲሁም ጥልቅ ሀዘን አስከትሏል። በማይካድራ አማራ እና በወልቃይት ተወላጆች ላይ ያነጣጠረውን ጥቃት ተከትሎ ቤተሰቦች መበታተናቸውንና ሕፃናት ለስነልቦና ቀውስ መዳረጋቸውን የተናገሩት ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል፤ የጭፍጨፋው ሰለባ ቤተሰቦች ህይወታቸውን እንደቀድሞ ለማስቀጠል አዳጋች እንደሚሆንባቸው … [Read more...] about “የማይካድራ ጭፍጨፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብዓዊ፣ ስነልቦናዊ ቀውስና ጥልቅ ሀዘን ያስከተለ ነው” – ዶ/ር ዳንኤል
ለደቡብ ሱዳን ሰላም ማጣት የስዩም መስፍን ሤራ
5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባውን ባካሄደበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሰጡት ማብራሪያ፤ ከሀዲው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን በክልልና በዘር ከመከፋፈል አልፎ ጎረቤት ሀገራትን ጭምር በጎሳና በዘር ሲያባላ እንደነበር ተናግረዋል። “ሶማሊያ ስንሄድ እኛ እኮ እናንተን አናምናችሁም፤ በክልልና በጎሳ ከፋፍላችሁ የምታባሉን እናንተ ናችሁ፤ የእናንተ መንግስት ነው ይህን የሚያደርገን፤ በጣም ነው የምንጠላችሁ” በማለት ሳይደብቁ ኢትዮጵያን ይወቅሱ ነበር ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። “በተመሳሳይ ደቡብ ሱዳን ስንሄድም አሁን ላይ በሀገራችን እየተባላንበት ያለው ጉዳይ የእናንተው ውጤት ነው” በማለት ኢትዮጵያን እንደሚወቅሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ አብራርተዋል። “በኢጋድ ውስጥ ስዩም መስፍን የሚባለውን ሰውዬ መድባችሁ ከፋፍሎን አባልቶን … [Read more...] about ለደቡብ ሱዳን ሰላም ማጣት የስዩም መስፍን ሤራ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፓርላማ ፊት ቀርበው ከተናገሩት
በለውጡ ዋዜማ የገጠመን መፈናቀል በሚሊዮን የሚቆጠር እንደነበርና በአንድ ጉድጓድ በርካቶችን የመቅበር ሂደት ይታይ ነበር፤ከለውጡ በፊት የአገርን ደህንነት ለማስጠበቅ የተቋቋመ ተቋም የኦነግን ባንዲራ በገፍ በማሳተምና እሱን የያዙ ሰዎችን ኢሬቻ በዓል የሚከበርበት ቦታ ውስጥ በማስገባት ሰዎችን ለማፈን ይጠቀምበት ነበር፤ ሎጎ የሌላው ባንዲራም በተመለከተ ተመሳሳይ ነው፤ይህም በስልጣን ላይ የነበረው ቡድን ዜጎችን ለማሳዘንና የተፈራው ለውጥ እንዳይመጣ ለማድረግ ነው፤ከለውጡ ጋር በተያያዘ ለውጡን በቅርበት በሚመሩት አካላት ላይ የደህንነት አስጨናቂ ክትትልና ዛቻ እንዲሁም የእስር ማዘዣ እስከማውጣት ተደርሶ ነበር - በጁንታው ስብስብ፤ከኢህአዴግ ሊቀመንበር ምርጫ ጋር በተያያዘ የፈለጉት ሰው ለማስመረጥ የጁንታው አባላት ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም - ግን አልተሳካላቸውም፤ፍላጎቱ እኛን … [Read more...] about ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፓርላማ ፊት ቀርበው ከተናገሩት
ህወሓት በማይካድራ በፈፀመው ወንጀል በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ ተጠየቀ
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ሕወሓት ዘርን መሠረት አድርጎ በማይካድራ በፈፀመው የንጹሐን ዜጎች የግድያ ወንጀል መንስዔ በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ ጠየቁ። አባላቱ ይህንን እና ሌሎች መሰል ወቅታዊ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቅርበዋል። የተደረገው ፍጹም ጭካኔያዊ እና አረመኔያዊ ድርጊት እጅግ እንዳሳዘናቸውም አያይዘው ገልጸዋል። ተግባሩም የጦር ወንጀለኝነት መሆኑንም አበክረው ተናግረዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አክለውም፤ የሀገርን እና የህዝብን አደራ ተቀብለው ግዳጃቸውን እየተወጡ በነበሩት የሰሜን ዕዝ የሠራዊት አባላት ላይ የሕወሓት ጽንፈኛ ቡድን የወሰደው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊትም እጅግ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል። በየትኛውም የህግ መመዘኛ ተቀባይነት እንደሌለውም አስረድተዋል። የፓርላማ አባላቱ በተጨማሪም፤ የኢፌዴሪ የሀገር … [Read more...] about ህወሓት በማይካድራ በፈፀመው ወንጀል በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ ተጠየቀ
ነቀርሳው ህወሓት ተነቀለ!
በትግራይ ክልል ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ ለ25 ቀናት በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ቡድንና በመከላከያ ሠራዊቱ መካከል ሲደረግ የሰነበተው ውጊያ፣ ቅዳሜ ኅዳር 19 ቀን ከሰዓት በኋላ የመከላከያ ሠራዊቱ የክልሉ ዋና ከተማ መቀሌን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ(ዶ/ር) እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ አረጋግጠዋል። መከላከያ ሠራዊቱ ባካሄደው ዘመቻ ንጹኃን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑና ቅርሶች ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አስታውቀዋል። ሠራዊቱ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንዴት ከተማዋን መቆጣጠር ይቻላል በሚለው ላይ ኅዳር 18 ቀን ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን በመግለጫቸው ያስታወሱት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ፣ … [Read more...] about ነቀርሳው ህወሓት ተነቀለ!
ህወሃት እንደአጀማመሩ እየተጠናቀቀ ነው
ድልድይ በማፍረስ፤ መሠረተ ልማቶችን በማውደም ከየቦታው በተለቃቀሙ ወንበዴዎች መሪነት ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም በግፍ ሲገዛ የነበረው ህወሃት/ትህነግ እንደ አጀማመሩ አፈጻጸሙም እየሆነ እንዳለ ተጠቆመ። ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው። ከዚህ በታች የሚገኘው መረጃ በዓለምአቀፉ የአሸባሪዎች ቋት ተመዝግቦ የሚገኝ የህወሃት ወንጀል ዝርዝር ነው። በበረሃ ዘመኑ ህወሃት ካወደማቸው በጥቂቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ትላንት … [Read more...] about ህወሃት እንደአጀማመሩ እየተጠናቀቀ ነው