ኢትዮጵያ ጀግና ከመውለድ ፀሀይም በምስራቅ ከመውጣት ቦዝነው አያውቁም ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዛሬው እለት በኢፌዴሪ መከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በሶስተኛ ዙር በመሰረታዊ ውትድርና የሰለጠኑ ምልምል ወታደሮች ምረቃ ላይ ተገኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ምረቃ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ አገሬን አትንኳት ብለው ከመላ ኢትዮጵያ የዘመቱ ጀግኖች በግንባር አኩሪ ድል እያስመዘገቡ መሆኑን ገልፀው፤ የዛሬ ተመራቂዎችም ለአገር አንድነትና ክብር ለመዋደቅ የሰራዊቱ አባል ለመሆን መወሰናቸው የሚደነቅና የሚያኮራ ነው ብለዋል።
አሸባሪው የህወሓት ቡድን የኢትዮጵያ እንቅርት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህን እንቅርት በኢትዮጵያዊያን አኩሪ ገድል እናጠፋዋለን ብለዋል።
የኢፌዴሪ የአገር መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ በበኩላቸው ጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት በአሸባሪው ሀይል ላይ አስደናቂ ድል እየተጎናፀፈ መሆኑን ገልፀዋል።
“ከሀዲውን አሸባሪ ሀይል ለመደምሰስ በበጎ ፈቃዳችሁ ወደ ሰራዊቱ ለመቀላቀል መወሰናችሁ የሚያኮራ ተግባር ነው” ብለዋል ጄኔራል ብርሀኑ።
በኢፌዴሪ መከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በሶስተኛ ዙር በመሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች ዛሬ በድምቀት አስመርቋል።
ትርምህት ቤቱ በ1979 ዓም ተመስርቶ እስካሁን ድረስ የአገር ሉላዊነት የሚያስከብሩ ጀግና የሰራዊት አባላትን አያፈራ ይገኛል። (ኢ.ፕ.ድ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply