በመግለጫው ትህነግ የሚያዋጣው የብልጽግና መንገድ ነው አለ ለትግራይ ህጻናት ዕልቂት ተጠያቂው ማን ነው? ብልጽግናን እንደማይቀላቀል አስታውቆ ወደ ትግራይ ያፈገፈገው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግ) “በአዲሱ ዓመት ግጭቱን አቁመን ለሰላም ዕድል በመስጠት የሰላም እና ብልጽግና መንገድ እንጀምር” ሲል በይፋ የተናጠል ተኩስ አቁም ማወጁን አስታወቀ። መግለጫውን ተከትሎ “ላለቁት የትግራይ ህጻናት ተጠያቂ ማን ሊሆን ነው? ለዚህ ለዚህ ለምን ውጊያ ውስጥ ገባን?” በሚል ደጋፊዎቹ ንዴት አዘል ጥያቄ እያነሱ ነው። ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት “አፍንጫቸውን ይዘን ቅድመ ሁኔታችንን ተቀብለው ወደ ድርድር እናመጣቸዋለን። ካልሆነም እንወጋቸዋለን” በማለት የወንበዴው ቡድን መሪ ደብረጽዮን መግለጫ ሰጥቶ ነበር። መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ቦታ ለመደራደር ፈቃደኛ … [Read more...] about ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እደራደራለሁ ያለው ትህነግ ውጊያ ከፍቷል
Archives for September 2022
የአዲስ አበባዎቹ አሸባሪ የትህነግ ወንበዴዎች (“ሰላማዊ ነዋሪዎች”) በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ባለፈው ሳምንት ባወጣነው ዘገባ ከአዲስ አበባ ሆነው የትህነግን ሥራ የሚያስፈጽሙ ወንበዴዎች መኖራቸውንና መንግሥት በጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጥ ጠቁመን ነበር። በወጣው ዘገባ መሠረት ከአዲስ አበባ ሆነው የት ህነግን ሥራ የሚያስፈጽሙ በተለይም በትዊተር በተለቀቀው መልዕክት 88% የተላከው ከአዲስ አበባ መሆኑን በማስረጃ የተደገፈ መረጃ ነበር የቀረበው። የአዲስ አበባ “ሰላማዊ” ነዋሪዎች – አፍቃሪ ትህነጎች ማንነት በማስረጃ የኢትዮጵያ የጋራ የጸጥታ ግብረኃይል ሲከታተላቸው የነበሩና እጅግ ውስብስብ በሆነና ሕዝብን በሚያሸብር ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩ 19 የሽብር ቡድን አባላትና የትህነግ አስፈጽሚ ወንበዴዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ከፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ያወጣው መግለጫ እንዲህ ይነበባል፤ ጠላቶቻችን አዲስ አበባን የሽብር ማዕከል እናደርጋለን ብለው … [Read more...] about የአዲስ አበባዎቹ አሸባሪ የትህነግ ወንበዴዎች (“ሰላማዊ ነዋሪዎች”) በቁጥጥር ሥር ዋሉ
የህወሓት የሽብር ሰነድ ሲገለጥ…
አሸባሪው ህወሓት ሀገርን የሚያፈርስበትና የኢትዮጵያን ህዝብ በመበቀል ለመከራ የሚዳርግበት አዲስ ሰነድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር ገብቷል። አሁን እያካሄደ ያለው ውጊያም የዚሁ አካል ነው። ፅሁፉ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ በማሳጠርና መታየት ያለባቸው ነጥቦች ብቻ ቀርቧል። ከሰነዱ የተወሰዱ ዋና ወና ሃሳቦች: ስለ ሰላም አማራጮች ያላቸው አቋም:- • የሰላም አማራጭ በሚል ስትራቴጂው፣ በአንድ በኩል ጊዜ ወስዶ ለአጠቃላይ ዘመቻ ለመዘጋጀት በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት ሰላም ፈላጊ አይደለም ብሎ ለዓለም ማህበረሰብ ጥላቻ ለማሰተጋባት እንዲያግዘው በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የጀመረው አካሄድ በፍፁም የማያዋጣና የትግራይ ህዝብን ጥቅም የማያስከብር መሆኑን ያስቀምጣል። • የውስጥ ትግላችን በማገዝ የሚንቀሳቀሱ እንደ ኦነግ የመሳሰሉ አጋሮቻችን እንዲሁም በተለያዬ የዓለም … [Read more...] about የህወሓት የሽብር ሰነድ ሲገለጥ…
ኢትዮጵያን “በእኛ ትውልድ ማንም ተነስቶ እንዲፈነጭባት አልፈልግም” ምክትል ፲ አለቃ በዝናሽ ወዳጆ
ኢትዮጵያ ታፍራ እና ተከብራ እንድትኖር የተሠጠኝን ግዳጅ በጀግንነት እወጣለሁ ትላለች ምክትል ፲ አለቃ በዝናሽ ወዳጆ። በሰቆጣ ግንባር የአሸባሪውን የህወሓት ታጣቂ ዶግ አመድ ካደረጉት ጀግኖች መካከል አንዷ ናት ምክትል አስር አለቃ በዝናሽ ወዳጆ። ምክትል አስር አለቃ በዝናሽ ወዳጆ እንደተናገረችው ኢትዮጵያን ተላላኪ የሽብር ቡድን ሰላሟን እንዳያደፈረስ ላፍታም ቢሆን ሳልዘናጋ የተሠጠኝን ግዳጅ በጀግንነት እወጣለሁ። አባቶች በመስዋትነታቸው ያስረከቡንን ሀገር በእኛ ትውልድ ማንም ተነስቶ እንዲፈነጭባት አልፈልግም። በተሰለፍኩበት ግንባር የሀገሬን ጠላት እስከ መስዋዕትነት ከፍዬ ግዳጄን በቁርጠኝነት እወጣለሁ ብላለች። (መከላከያ ሠራዊት) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ኢትዮጵያን “በእኛ ትውልድ ማንም ተነስቶ እንዲፈነጭባት አልፈልግም” ምክትል ፲ አለቃ በዝናሽ ወዳጆ
ደስታ ጌታሁን – የደጀንነት ጀብዱ
ወይዘሮ ደስታ ጌታሁን ነው የምትባለው፡፡ ይህች እህታችን በሰቆጣ ከተማ በትንሽዬ የዳስ ውስጥ ቡና እና ሻይ በመስራት ሁለት ልጆችዋን ታስተዳድራለች፡፡ ወይዘሮ ደስታ ለእናት ሃገሩ ኢትዮጵያ ለሚፋለመው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን የምታደርገው ነገር ግራ ቢገባትም ከልጆችዋ እና ከራስዋ የእለት ጉርስ ቀንሳ በግዳጅ ቀጠናው ለሚፋለሙ የሰራዊት አባላት ቡና እና ሻይ ይዛ ተገኝታለች፡፡ ወይዘሮ ደስታ ጌታሁን ሰራዊቱ በግዳጅ ላይ ፋታ ሲያገኝ ቡና እና ሻይ በማቅረብ ደጀንነቷን በጀግንነት አስመስክራለች፡፡ (ዘግባና ፎቶግራፍ፤ ልመነህ ሻወል የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ደስታ ጌታሁን – የደጀንነት ጀብዱ
“ልጆቼ ከሀገሬ አይበልጡም”
"ለዐማራነቴ፤ ለኢትዮጵያዊያነቴ ህይወቴን እሰጣለሁ" እንዳልህ ይኼው ደማህ፤ ልክ እንደ አድዋው ጀግና ፊታውራሪ ገበየሁ "ህወሓትን ፈርቼ ስሸሽ ከኋላዬ ከተመታሁ አሞራ ይብላኝ፤ ከፊት ለፊት ስፋለም ከወደቅሁ ግን ልጆቼን አደራ" እንዳልህ ክንድህ ላይ በፈሰሰው የደም ጠብታ ቃልኪዳንህን አፀናህ። ባለፈ ጊዜ ለእረፍት መጥቶ ሚስቱ "እባክህ በልጆችህ ልለምንህ አትሂድ" ስትለው "ልጆቼ ከሀገሬ አይበልጡም" ነበር ያላት። በርግጥ ይህ የአባቶቻችን ውርስ ነው። ዐፄ ቴዎድሮስ መቅደላ አፋፉ ላይ ሽጉጣቸውን ከወገባቸው ላይ መዘው ሊጨልጡት ባሉበት ቅፅበት ልጃቸው ልዑል አለማየሁን የወለዱላቸው እቴጌ ጥሩ ወርቅ "እባክዎትን ለአንድ ልጅዎት ለልዑል ዓለማየሁ ሲሉ እንኳን ይህን ሀሳብዎን ትተው ይቆዩለት" ቢሏቸው "ልጅ አለማየሁ ከሀገሬ ከኢትዮጵያ አይበልጥም። አንዲት ኢትዮጵያ በዐይኑ እንደዞረች ሞተ … [Read more...] about “ልጆቼ ከሀገሬ አይበልጡም”
“ውረሩ፣ ያገኛችሁትን ግደሉ እየተባልን ነው የምንመጣው” እጃቸውን የሠጡ የትህነግ ታጣቂዎች
በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ላይ የተነሳው የሽብር ቡድን በሕዝብ ላይ አያሌ በደሎችን አድርሷል። ከእኩይ ቡድን አቅራቢያ የሚገኙ የአማራና የአፋር ክልል ነዋሪዎች ደግሞ የሽብር ቡድኑ ግፍና ወረራ ገፈት ቀማሾች ናቸው። ለሦስተኛ ጊዜ ጦርነት ያነሳው የትህነግ የሽብር ቡድን የትግራይ ተወላጆችን ከሕፃናት እስከ አዛውንት ድረስ እየመለመለ ለጦርነት እየላካቸው ነው። የሽብር ቡድኑ በአማራና አፋር ክልል በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች ንፁሐንን በጅምላ ረሽኗል፣ ሃብትና ንብፈታቸውን ዘረፏል አውድሟል። የሽብር ቡድኑ የሚልካቸው ታጣቂዎች ሀገሩን እየተከላከለ በሚገኘው ጥምር ጦር እየተመቱ ብዙዎች ይረግፋሉ። እድል የቀናቸው እጃቸውን ሰጥተው ሕይወታቸውን ያተርፋሉ። የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች በወልቃት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ለሚገኘው ጀግናው የሀገር መከላከያ በርካቶች እጃቸውን እየሰጡ … [Read more...] about “ውረሩ፣ ያገኛችሁትን ግደሉ እየተባልን ነው የምንመጣው” እጃቸውን የሠጡ የትህነግ ታጣቂዎች
“ህወሃት የበሰበሰች ናት፤ አትጠቅምም” የህወሃት ምርኮኛ
አሸባሪው ህወሓት የቀረበለትን የሰላም አማራጭ ረግጦ ዳግም ጦርነት መክፈቱ በትግራይ ህዝብ ጫንቃ ላይ ቆሞ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ነው ሲሉ በተለያዩ ግንባሮች እጃቸውን ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰጡ ምርኮኞች አጋለጡ። ምርኮኞቹ እንደተናገሩትም የትግራይን ህጻናት ሳይቀር ወደ ጦር ግንባር እየማገደ የሚገኘው አሸባሪው ህወሃት በሃሰተኛ ትርክት የትግራይን ወጣት ራሱ ወደለኮሰው ጦርነት እየማገደ ክልሉን ትውልድ አልባ የማድረግ እኩይ አላማውን ገፍቶበታል። ይህም ተግባሩ የሽብር ቡድኑን የባንዳነት ትክክለኛ ባህሪ በተጨባጭ እያረጋገጠ መሆኑንም ነው ምርኮኞቹ የተናገሩት። https://www.youtube.com/watch?v=z_adOLMwufQ ምርኮኞቹ አሸባሪው የህወሃት ቡድን በትግራይ ህዝብና ህፃናት ላይ እየፈፀመ ያለውን ስቃይና እንግልት በመቃወም … [Read more...] about “ህወሃት የበሰበሰች ናት፤ አትጠቅምም” የህወሃት ምርኮኛ
WhatAboutism በመረጃ ‘ጦርነት’ ውስጥ
WhatAboutism ስትራቴጂው በሰዎች ባህሪ ውስጥ ብቻ ሳይወሰን በፖለቲካ እሰጣገባዎች ውስጥም የሚተገበር ሆኗል፤ ወቀሳ እና ትችት ሲሰነዘር የወቃሽ መሰል ወንጀል በአፃፋነት ማቅረብ…። Whataboutism እንደ ፖሮፓጋንዳ ስትራቴጂ ቆየት ቢልም በኮቪድ 19 ሰሞን ጡዘት ላይ የደረሰበት ነበር። የኮቪድ መነሻ ቻይና ነች የሚለው የምዕራባዊያን የሚዲያ ዘመቻ ከቻይና በተጨማሪ ሩሲያን ያካተተ ቅንጅታዊ የመልስ ምቶይ እንዲያይሉ ያደረገ ነበር። የቻይና እና ሩሲያ ባለስልጣናት አሜሪካ በቤተ ሙከራ ፈጥራ አሰራጨቻቸው የሚባሉትን የበሽታ ዝርዝሮች ቆየት ያሉ ፋይሎች እየፈለፈሉ ይጠቅሱ ነበር። የራሳቸው የምዕራባዊያን ተቋማት ቀደም ሲል ያወጧቸውን ጥናታዊ ማጋለጫዎች እንደማጠናከሪያ መጠቀማቸው ሞስኮ እና ሩሲያን በ whataboutism ፕሮፖጋንዳው በለስ ሆኖላቸዋል። “Whataboutism” … [Read more...] about WhatAboutism በመረጃ ‘ጦርነት’ ውስጥ
ምኒልክ የድል መንፈስ!
የዛሬዋ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ስበት ማዕከል የሆነው አፄ ምኒልክ ዘመን ተሻጋሪ ውርሶች ለዘመናዊት ኢትዮጵያ ጥሎ አልፏል። ዘመናዊት ኢትዮጵያ ስንል ከጨረቃ የመጣች እያልን ሳይሆን ግዛታዊ ቅርጿ ሲጠብና ሲሰፋ የነበረችው ኢትዮጵያ በአንጻራዊ ዝማኔ መመራት የጀመረችበት አስተዳደራዊ ዘመን መገለጫ ማለታችን ነው። የዛሬዋ ኢትዮጵያ መልከዓ ምድራዊ ቅርጽ ከሞላ ጎደል የአፄው የንግሥና ዘመን ውጤት ናት። ከምንም በላይ የጥቁር ዘር የነጻነት ምልክት የሆነው የአድዋ ድል በምኒልክ መሪነት የመጣ ነው። በርግጥ ድሉ የአባቶቻችን የመደማመጥና የመተባበር ውጤት ነው። ምኒልክን አልባ የአድዋን ድል ማስመዝገብ ይቻል (ይሆን) ነበር ብሎ ማመን ይቻላል። ይሁንና በታሪክ የምናውቀውን የአድዋን ድል ያለ ምኒልክ ማሰብ ክርስትናን ያለክርስቶስ፣ እስልምናን ያለነብዩ መሐመድ እንደማሰብ ያለ ቅዥት ነው። ይህ … [Read more...] about ምኒልክ የድል መንፈስ!