አሸባሪው ህወሓት ሀገርን የሚያፈርስበትና የኢትዮጵያን ህዝብ በመበቀል ለመከራ የሚዳርግበት አዲስ ሰነድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር ገብቷል። አሁን እያካሄደ ያለው ውጊያም የዚሁ አካል ነው።
ፅሁፉ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ በማሳጠርና መታየት ያለባቸው ነጥቦች ብቻ ቀርቧል።
ከሰነዱ የተወሰዱ ዋና ወና ሃሳቦች:
ስለ ሰላም አማራጮች ያላቸው አቋም:-
• የሰላም አማራጭ በሚል ስትራቴጂው፣ በአንድ በኩል ጊዜ ወስዶ ለአጠቃላይ ዘመቻ ለመዘጋጀት በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት ሰላም ፈላጊ አይደለም ብሎ ለዓለም ማህበረሰብ ጥላቻ ለማሰተጋባት እንዲያግዘው በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የጀመረው አካሄድ በፍፁም የማያዋጣና የትግራይ ህዝብን ጥቅም የማያስከብር መሆኑን ያስቀምጣል።
• የውስጥ ትግላችን በማገዝ የሚንቀሳቀሱ እንደ ኦነግ የመሳሰሉ አጋሮቻችን እንዲሁም በተለያዬ የዓለም መአዘናት የሚገኙ የትግራይ ዲያስፖራና ዓለም አቀፍ አጋዦቻችንና አጋሮቻችን በዚህ ጊዜ የተሳካ ጥምረት በማድረግ ወደ አዲስ አበባ በምናደርገው እንቅስቃሴና ዘመቻ ከጎናችን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑን የትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ጋር በዝግ ባደረገው ውይይት አረጋግጧል።
የአማራ ሃይል የተመለከተ
• ይሄ ፅንፈኛ የአማራ ተስፋፊ ሃይል በትግራይ ላይ ካሳየው ጫፍ የወጣ ጥላቻ በላይ፣ በክልሉ ያገኘውን ሕዝባዊ ተቀባይነት ሽፋን በማድረግ እና ጠንካራ ቅንጅት በመፍጠር ከአማራ ክልል መንግሥት የሚስተካከል አቅም መፍጠር በመጀመሩ የዐቢይ አስተዳድር በወሰደው ርምጃ በተወሰነ መልኩ መዳከም ታይቶበታል።
* አሁንም ግን የዚህ ሃይል አመራሮች በህዝብ ጉያ ተደብቀው ስለሚገኙ ምቹ ሁኔታ ካገኙ ዳግም ሃይል አግኝተው መነሳታቸው አይቀርም። ይህ ሁኔታ የትግራይ ሰራዊት እንደ ጥሩ አጋጣሚ ሊጠቀምበት የሚገባ ሲሆን፣ ይሄ ሃይል ራሱን “ፋኖ” ብሎ በመጥራቱ የተወሰደበት ርምጃ በርከት ያሉ የአማራ ታጋይ ሃይሎች ከዐቢይ ጎን ተሰልፈው ለመንቀሳቀስ ያላቸውን እንዲቀንስ አድርጎታል። ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ስራ በመስራት የተፈጠረውን መሻከርና ክፍተት የበለጠ እንዲከር ማድረግ ይገባል።
አፋር ክልልን በተመለከተ
• የዓፋር መንግሥት የእርዳታ ተደራሽነት በመቆጣጠር በየጊዜው ምክንያት የሌለው ግጭቶች በመፍጠር በአዋሳኝ አከባቢዎች በዘላቂነት ሰላም እንዳይሰፍን በማድረግ በአከባቢው የሚኖሩ ተጋሩ በስጋት ውስጥ እንዲሆኑ አድርጓል። በአወል አርባ የሚመራ ግጭት ቀስቃሽ ቡድን ከዐቢይ አስተዳድር በሚሰጠው አድናቆትና ቁጥር የሌለው የትጥቅ እገዛ አይኑ የታወረ፣ ጆሮው የተደፈነ በመሆኑ፣ ትግላችን በሚያግዙ የዓፋር የነፃነት ታጋዮችና ቤተሰቦቻቸው አፈናና ግድያ እየፈፀመባቸው ይገኛል።
ኤርትራን በተመለከተ
• ይሄ ፍፁም አምባገነን የሆነ የኤርትራ መንግሥት፣ አሁንም እንደ ትላንት ዋነኛ የሰላምና የትግራይ ህዝብ ነፃነት ጠላት መሆኑ ዳግም እያሳየ ይገኛል። ይሄ ጨቋኝ መንግሥት ባጭር ጊዜ መፍትሄ ካላገኘ ሕዝባችንን ወደ ማያቋርጥ ጦርነትና መከራ ዳግም ለማስገባት የሚችል ስጋት በውስጡ የያዘ ነው። ከዚህ በተጨማሪ፣ በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ የዐቢይ ታማኝ አመራሮችና ደጋፊዎች በክልላቸው ውስጥ በምናደርገው እንቅስቃሴ የሚያግዙንን የውስጥ አካላት እያደኑ ማጥቃት ቀጥለዋል።
ከኦነግ ጋር ያለን ግንኙነት
• ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አመራር ጃል ሚልኬሳ ጋር በሚስጢር ባደረግነው ውይይት፣ ባጭር ጊዜ አመራራቸው ወደሚመች አከባቢ ወይም ወደ አጎራባች ሃገሮች ስልታዊ ማፈግፈግ የሚያደርጉበት ሁኔታ እንዲመቻች፣ እንዲሁም የመከላከል አቅምና ዝግጁነት የሌላቸው የሰራዊቱ አባላት ከተቻለ ዩኒፎርማቸውን ጥለው ወደ ሕዝባቸው እንዲቀላቀሉና እንዲደበቁ ካልተቻለም ለመንግሥት ሃይሎች እጃቸውን መስጠት የተሻለ አማራጭ እንደሆነ አንስቶ ነበር።
• በወለጋ ያለው ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አመራር መካከል ጃል ራሣና ጃል ቃንቄ በፋሺስት ዐቢይ ከተከፈተባቸው ከበባ ለመውጣት አስቸኳይ ዘዴ ዘይደው መመርያ በመስጠት ወደሚመች ምስጢራዊ ቦታዎች እንዲንቀሳቀሱ የተደረገው ሙከራ የተሳካ ነው። በዚህ አግባብ በአንዳንድ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አመራሮች መካከል የትግል ስልት ልዩነት ቢኖርም በአስቸጋሪ ሁኔታ ሁነንም የመረጃ ልውውጣችን እና መተጋገዛችን የሚቀጥል ይሆናል። የዚህ ግንኙነት ዋነኛ መሰረት፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ለአዲስ አበባ ካላቸው ቅርበትና ለሚታሰበው ዘመቻ ከፍተኛ ትግል በማድረግ ድል ሊያስመዘግቡ የሚችሉ በመሆናቸው ላይ ካለን መተማመን የሚመነጭ ነው።
• ይሁን እንጂ አሁንም የፋሺስት ዐቢይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳን አገዛዝ ሽባ በማድረግ ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው የመጨረሻ የትግል ምዕራፍ ላይ የቅርብ አጋዦች እነዚህ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በመሆናቸው ሊስተካከሉ የሚገባቸው እና ባለፈው ግምገማ የታዩ ክፍተቶች ታርመው ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እንዲዘጋጁ ማድረግ አስፈላጊ ነው።
ሶማሌ ክልልን በተመለከተ
•በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል በሱማሌ ክልል ከሚንቀሳቀሱ እና የጋራ ጠላታችንን ከሚታገሉ የአልሸባብ ሴሎችና ከኦጋዴን ታጋዮች ጋር የመረጃ ልውውጥ እገዛ እና ስትራቴጂ ሥራዎቻችን ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
የውጭ ሃይሎችን ድጋፍ
• በውጭ ያሉ አጋዦቻችንና አጋሮቻችን በአስቸጋሪ እና አጣብቂኝ ጊዜ ውስጥ ቢንሆንም ችግሩን አልፈው ዘመናዊ ትጥቆች እንድንታጠቅ አድርገውናል። ይህም ሆኖ የዚህ ዘመቻ ምዕራፍ መራርና በርካታ መስዋእትነት የሚጠይቅ በመሆኑ አሁንም ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ዘመናዊ ትጥቅ ለመከላከያ ሃይላችን እንዲያቀርቡልን የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ከውስጥና ከውጪ ተባባሪዎቻችን ጋር ያለንን ስራ አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል።
• በትግራይ የሚገኙ የዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ሰብአዊ ድጋፍ ማከማቻ መጋዘኖች ፋሽስቱን ለማስወገድ በምናደርገው ትግል የስንቅ አቅርቦት እንዳይጓደል በቁጥጥራችን ስር ልናደርጋቸው ይገባል።
የስነልቦና ጦርነትና ስጋትን መፍጠር
• በጠላት ላይ ሽብር፣ ፍርሃትና የስነ ልቦና ጫና መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፣ ሽብር የሚያስፋፉ እና በመሀል ሃገር ያለው ሕዝብ ሳይቀር በመንግሥት አቅም ላይ ያለው እምነት እንዲሸረሸር የሚያደርጉ መረጃዎች በሀገር ውስጥና በውጪ ሚዲያዎች በሙሉ ማዳረስ ያስፈልጋል። ለዚህም ባለቤቶቻቸው አዲስ አበባ የሚገኙ ሚዲያዎችና ዩቲዩብ ቻናሎች ከፍተኛ ድጋፍ ስለሚኖራቸው የመረጃና ፋይናንስ ድጋፋችን ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
ልማትን የማደናቀፍ እቅድ
• ዐቢይ ያገኘው ጊዚያዊ አንፃራዊ መረጋጋት፣ ሕዝብ በማንቀሳቀስ የጀመረው የእርሻ ልማት፣ የበጋ ስንዴና ሌሎች የኢኮኖሚ ስራዎች ማደናቀፍ ላይ ትኩረት እናደርጋለን። የእርሻ ዘርፉ እንዲደናቀፍ በየአከባቢው ግጭት በመቀስቀስ እና ግጭት ለመቀስቀስ የሚያስችሉንን ሃይሎች በማገዝ እረፍት በመንሳት፣ የልማት ስራዎችን ትቶ እሳት ማጥፋት ላይ እንዲጠመድ ማድረግ በረዥም ጊዜ የዐቢይ መንግሥትን ለማዳከም የሚያግዝ ሲሆን፤ ባጭር ጊዜም ደግሞ ለሚካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ የጠላት አቅም እንዲዳከም ትልቅ ጥቅም አለው። በአማራ ክልል በተወሰነ መልኩም ቢሆን ፊቱን ወደ ልማት ያዞረ ገበሬ እየታየ ነው። ይህ ወደ ልማት ፊቱን ያዞረ ሃይል ትላንት እና ከትላንት ወዲያ የትግራይን መሬት በሃይል የወረረ፣ ሰብል ያቃጠለ፣ ንብረት ያለምንም ይሉኝታ የዘረፈ፣ ሴቶችን የደፈረ ሃይል ነው።
ይህ ወደ ልማት ፊቱን ያዞረ ሃይል ትላንት እና ከትላንት ወዲያ የትግራይን መሬት በሃይል የወረረ፣ ሰብል ያቃጠለ፣ ንብረት ያለምንም ይሉኝታ የዘረፈ፣ ሴቶችን የደፈረ ሃይል ነው። ስለሆነም በሕዝባችን ላይ ባደረሰው ግፍ የማያዳግም እርምጃ ሊወሰድበት ሲገባ የተፈጠረውን ጊዜያዊ ክፍተት በመጠቀም ፊቱን ወደ እርሻው መልሷል፤ ይህ ሃይል የእርሻ ውጤቱን ወደ ቤቱ እንዲያስገባ ልንፈቅድለት አይገባም።
የትግራይ መሬቶችን የማስመለስ እቅዶች
• ለጦርነት ባልተዘጋጁበትና በዐቢይ የሰላም ጥሪ በተዘናጋበት ጊዜ አስፈላጊ የሚባል ርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪ በጦርነት ጊዜ ከእጃችን የወጡ የትግራይ ሕዝብ ታሪካዊና ህገመንግሥታዊ ርስቶች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ታሪካዊ ሃላፊነት አለብን።
የቅማንት የወሰንና ማንነት ጉዳዮችን በሚመለከት
የቅማንት ማህበረሰብ የምኖርበት አካባቢ ከፍተኛ ሕዝባዊ ጥያቄ እንዲነሳና አካባቢውን ወደማያባራ ፖለቲካዊ ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ እንዲገባና ያለውን ሁኔታ ሊለውጥ የሚያስችሉ ስራዎች መስራት አስፈላጊ ነው።
የህዝብ ጥያቄዎች እንዲባባሱ ማድረግ: ለጥፋት የመጠቀም እቅድ
• ማንኛውንም አይነት ማህበራዊና ፖለቲካዊ አጀንዳዎችን ሳንንቅ ወደ አደባባይ እንዲመጡ በማድረግ፣ ጥያቄዎቹ ሕዝባዊ ቁመና እንዲላበሱ ማድረግ አስፈላጊ ነው። እነዚህ ጉዳዮች ተገቢ ትኩረት እንዲያገኙ ሚዲያዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች አጀንዳውን የማቀጣጠል ሚናቸውን በሚገባ እንዲወጡ በማገዝ የፋሺስት ዐቢይን ውድቀት ሊያፋጥኑ ይገባል።
በትግራይ ያለው የተሻለ ሁኔታ
• በትግራይ ያለው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ፋሺስቱ ዐቢይ የትግራይ ሕዝብ በችግር እንዲያልቅ ባለው ፍላጎት እየተቀጣጠለ ቢሆንም፣ ከሌሎች ጦርነት ካላገኛቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከሚታየው ችግር አንጻር ሲታይ እንደሚባለው ሰፊ ችግር እንደሌለ ሊታወቅ ይገባል።
የኢኮኖሚ አሻጥርን በስፋት መስራት
• ኢትዮጵያዊያን በተለይም የከተማ ነዋሪዎች፣ መንግሥትን የሚቃወሙት በተለያዬ የፓለቲካ አጀንዳዎች አይደለም፣ ከፓለቲካ አጀንዳዎች ይልቅ በቀጥታ ከዕለት ኑሯቸው ጋር የተያያዘው የኑሮ ውድነት ዋና መንግሥትን የሚቃወሙበት አጀንዳ መሆኑ ግልፅ ነው። ስለሆነም የኑሮ ውድነቱን የሚያባብሱ ኢኮኖሚያዊ አሻጥሮችን በተቀናጀ መንገድ መፈጸም አስፈላጊ ነው።
ከላይ በአጭር በአጭሩ የተቀመጠው የሰነዱ ዋና ዋና ይዘት ሆኖ አሸባሪው ህወሓት ለዕቅዱ ተግባራዊነት የትግራይ ህዝብ የትኛውንም ያክል የሕይወት መስዋእት ለመክፈል መዘጋጀት እንዳለበት አሰቀምጧል። (የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት)
Leave a Reply