
ወይዘሮ ደስታ ጌታሁን ነው የምትባለው፡፡ ይህች እህታችን በሰቆጣ ከተማ በትንሽዬ የዳስ ውስጥ ቡና እና ሻይ በመስራት ሁለት ልጆችዋን ታስተዳድራለች፡፡ ወይዘሮ ደስታ ለእናት ሃገሩ ኢትዮጵያ ለሚፋለመው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን የምታደርገው ነገር ግራ ቢገባትም ከልጆችዋ እና ከራስዋ የእለት ጉርስ ቀንሳ በግዳጅ ቀጠናው ለሚፋለሙ የሰራዊት አባላት ቡና እና ሻይ ይዛ ተገኝታለች፡፡
ወይዘሮ ደስታ ጌታሁን ሰራዊቱ በግዳጅ ላይ ፋታ ሲያገኝ ቡና እና ሻይ በማቅረብ ደጀንነቷን በጀግንነት አስመስክራለች፡፡ (ዘግባና ፎቶግራፍ፤ ልመነህ ሻወል የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply