ባለፈው ሳምንት ባወጣነው ዘገባ ከአዲስ አበባ ሆነው የትህነግን ሥራ የሚያስፈጽሙ ወንበዴዎች መኖራቸውንና መንግሥት በጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጥ ጠቁመን ነበር። በወጣው ዘገባ መሠረት ከአዲስ አበባ ሆነው የት ህነግን ሥራ የሚያስፈጽሙ በተለይም በትዊተር በተለቀቀው መልዕክት 88% የተላከው ከአዲስ አበባ መሆኑን በማስረጃ የተደገፈ መረጃ ነበር የቀረበው።
የአዲስ አበባ “ሰላማዊ” ነዋሪዎች – አፍቃሪ ትህነጎች ማንነት በማስረጃ
የኢትዮጵያ የጋራ የጸጥታ ግብረኃይል ሲከታተላቸው የነበሩና እጅግ ውስብስብ በሆነና ሕዝብን በሚያሸብር ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩ 19 የሽብር ቡድን አባላትና የትህነግ አስፈጽሚ ወንበዴዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
ከፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ያወጣው መግለጫ እንዲህ ይነበባል፤
ጠላቶቻችን አዲስ አበባን የሽብር ማዕከል እናደርጋለን ብለው በአደባባይ ከፎከሩበት ጊዜ ጀምሮ እኩይ ተግባራቸውን ለመፈፀም ያላደረጉት ሙከራ እንዳልነበረ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡
በውጭና በውስጥ ተላላኪ የሚዲያ አውታሮቻቸው ከሚያናፍሱት የሐሰት ፕሮፓጋንዳና የተዛባ መረጃ ባሻገር በልዩ ልዩ የተሽከርካሪ የውስጥ አካላት ጭምር ድብቅ ቦታዎችን እያዘጋጁ ከነብስ ወከፍ እስከ ቡድን የጦር መሳሪያዎችን ወደ ከተማው ለማስገባት ያደረጉት ሙከራ በህብረተሰቡ ተባባሪነትና በፀጥታ ኃይሉ ብርቱ ጥረት እንደከሸፈ የሚታወስ ነው፡፡
ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ ደግሞ ጠላቶቻችን ስልታቸውን በመቀየር በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ህዝቡ የደህንነት ዋስትና እንዳይሰማው እና ሰላም እንዲያጣ በማቀድ በንፁሃን ላይ ከባድ የዘረፋ እና የውንብድና ወንጀሎችን ጨምሮ አሰቃቂ ግድያን ሲፈፅሙ ቆይተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ ከጀግናው መከላከያ ሠራዊት፣ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር በመሆን ባደረገው የተቀናጀ ኦፕሬሽን እነዚህ የወንጀል ቡድኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ በጉዞ ርቀት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በተለምዶ ራይድ ተብለው የሚጠሩ ተሽከርካሪዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ተሳፋሪ መስለው ከገቡ በኋላ ወደ ሰዋራ ስፍራ ወስደው በአሽከርካሪዎቹ ላይ የግድያ እና የውንብድና ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የቆዩ፡-
1ኛ. ሸዊት ሐዲስ፣
2ኛ. ዳዊት አለሙ፣
3ኛ. በሪሁ ናይዝጊ፣
4ኛ. ሃይለአብ ወርቁ የተባሉት ፖሊስ ባደረገው የሌት ተቀን ክትትል በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆኑ ገዳይ ቡድኑን በማሰማራት፣ ድጋፍ በማድረግ፣ የተዘረፉ ንብረቶችን በመሸጥና በሽያጩ የተገኘውን ገንዘብ መልሶ ለወንጀል ተግባር እንዲውሉ በማድረግ በአጠቃላይ ለገዳይ ቡድኑ የቁሳቁስና የፋይናንስ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ፡-
1ኛ. በረከት መዝገበ፣
2ኛ. ሰናይ ሐይላይ፣
3ኛ. ማዕረጉ በርሔ፣
4ኛ. ይኩኖአምላክ አማረ፣
5ኛ. ፀሀዬ ተስፋዬ እና
6ኛ. ዳንኤል ገ/ማርያም የተባሉት ተጠርጣሪዎችን ጥምር የፀጥታ ሃይሉ ባደረገው ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል በጦር መሳሪያ የተደገፈ ዘረፋ፣ የመግደል ሙከራ እና የውንብድና ወንጀሎችን በየካ፣ በለሚኩራ፣ በቦሌ እና በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞች ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ሲፈፅሙ የቆዩ፡-
1ኛ. ፊሊሞን ህንፃ፣
2ኛ. አቡሽ ገ/እግዚአብሄር፣
3ኛ. መሰለ አባዲ ፣
4ኛ. ቸርነት ውዱ ፣
5ኛ. አቡሽ ግደይ፣
6ኛ. ህሉፍ ፈፀጉ፣
7ኛ. ወልደ ገብርኤል ህይወት፣
8ኛ. ሄኖክ ብርሃኔ እና
9ኛ. ክብሮም ንጉሱ የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ፖሊስ በብርቱ ክትትል በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ሲሆን ግለሰቦቹ ስለፈፀሙት ወንጀል በተጨባጭ ማስረጃ የተረጋገጠባቸው ከመሆኑም ባሻገር ወንጀል መፈፀማቸውን አምነው ቦታውንና አፈፃፀሙን ለፖሊስ መርተው አሳይተዋል፡፡
በተወሳሰበ መንገድ በየጊዜው የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶች አሳሳቢነታቸውን በመገንዘብ እና ፖሊስ ከህብረተሰቡ ያገኛቸውን መረጃ መነሻ በማድረግ የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራና የክትትል አባላት ባደረጉት ብርቱ ክትትል እና ጥምር የፀጥታ ሃይሉ ባካሄደው ሰፊ ኦፕሬሽን በአጠቃላይ 19 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሲሆን የወንጀሉ ፍሬ የሆኑ 12 ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣ ለዕኩይ አላማ ማስፈፀሚያ ይጠቀሙባቸው የነበሩ የተለያዩ ሐሰተኛ ሰነዶች እና ልዩ ልዩ የፀጥታ አካላት የደንብ ልብስም ተይዘዋል፡፡
ከዚህ ባሻገር በፖሊስ ላይ ጥቃት ለመፈፀም በሞከሩ ሁለት የዘረፋ ቡድኑ አባላት ላይ ዕርምጃ የተወሰደባቸው መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ሽብርተኛው የትህነግ ቡድን በግንባር የከፈተብንን ጥቃት እንደማያዋጣው ሲያውቅ የከተማ ላይ ሽብር ለመፍጠር የሽብር ቡድኑን አባላት መልምሎ በድብቅ ወደ አዲስ አበባ ላስገባቸው ተላላኪዎቹ ልዩ ልዩ የጥፋት ተልዕኮ ሰጥቶ ቢያሰማራቸውም በጥምር ፀጥታ ኃይሉ የሚያኮራ ብርቱ ተግባር በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል፡፡
ፖሊስ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግባራትን ለመከላከል በፀጥታ ኃይሉ የሚደረገው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እየገለፀ ሁሌም ለሰላማችን መረጋገጥ ከጎናችን ያልተለየው ህዝባችን ቀና ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Tesfa says
ከገጠር እስከ ከተማ ሰው ከማሸበርና ከዝርፊያ ሌላ ሙያ ያጡ ወያኔዎችና ጄለዎቻቸው ዛሬም የሚያስቡት የዛሬ 30 አመት ገደማ ሲዘርፉና ሲገድሉ በነበሩበት ጭንቅላት ነው። ለጥምሩ ጦሩ እጃቸውን የሰጡ የወያኔ ወታደሮችን ለተመለከተ ልብ ይሰብራል። ገና ውሃ ተራጭተው ያልጠገቡ ህጻናትን ለጦርነት የማገደው ወያኔ የሚደገፍና አይዞህ የሚባል ድርጅት ሳይሆን አይንህ ላፈር መባል ያለበት የማፍያ ስብስብ ነው። አሁን ተጠለፈ ተብሎ በተለቀቀው የድምጽ መረጃ ላይ ከፊት ያሉት አመራሮች ጉዳዪ አልቋል፤ ወታደሩ ተበትኗል ሲሉት አለቃ ተብዬው “በሏቸው በጥይት” የምን መሸሸት ነው ብሎ ሲናገር መስማት ደምን ያፈላል። ግን ይህ አሁን የተጀመረ ሳይሆን ከበረሃ እስከ ከተማ ይጠቀሙበት የነበረ የጭካኔ ጥግ ነው። የትግራይ ወጣት በዚህም እሳት በዚያም እሳት ይለበልበዋል። ይህንና ሌላውን ወያኔ በትግራይ ህዝብ ላይ የሚፈጽመውን በደል እያወቁ በውጭና በሃገር ውስጥ ወያኔን የሚደግፉ ሰዎች ህሊና የጎደላቸው ድርቡሾች ናቸው። ሌላው ቢቀር እውነቱን ለይቶ በማወቅ አቋምን በጊዜ ማስተካከል መልካም በሆነ ነበር። ልብ ላለው የደብረ ጽዪን፤ የጌታቸው ረዳ በየጊዜው መወሻከት በቂ ማስረጃ አይሆንም? ለምንስ ለ3ኛ ጊዜ ጦርነት አስፈለገ? ግን ምንም ቢመከሩ ከራሳቸው ውጭ ሌላን ነገር የማይሰሙት እነዚህ ሃገር ሽያጮች በጄ/ጻድቃን በኩል እኮ “አሁን ጦርነቱ አልቋል” በማለት የደነፉበት ጊዜ የቅርብ ትዝታችን ነው። ወያኔን ማንም አይፈልገውም። እንኳን የኢትዮጵያ ህዝብ ቀርቶ ከአብራኩ የወጣበት የትግራይ ህዝብ አክ እንትፍ ብሎታል። የድሮ አጋሮቹ ሁሉ ተራ በተራ እየሸሹት ሄደዋል። አሁን የቀረው ወዳጅ አሜሪካና ግብጽ ናቸው። እሷም የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች እንዲሉ እንጂ ሃገር መገንባትና ሰላምን ማስፈን አያውቁበትም። ማተራመስ እንጂ! የሚያሳዝንነው አሜሪካኖች ፊታቸው ላይ እንደ ተራራ የተደቀነውን እውነት ረግጠው ሌላ ዝባዝንኬ ነገር ሲሸርቡ ማየት እንዴት ያማል።
በቅርቡ ለወያኔ የጦር መሳሪያ ሊያቀብል ሲል ተመታ ስለተባለው አውሮፕላን ከአንዳንድ በዚሁ ዙሪያ አዋቂ ነን ከሚሉ ሰዎች ጋር ተጫውተንበት ነበር። ተመታ የተባለው አንቶኖቭ 24 ወይም 26 ነው (There are some variants) ሁሉንም ባይሆን አንዳንድ ነገሮችን ከመረመርን በህዋላ በሁለት ሃገሮች ላይ ትኩረት አርገናል። አንድ ያው ሁሉም እንደሚጠራጠረው ግብጽ ናት። ግን የተመታው አውሮፕላን አንቶኖቭ 26 ከሆነ ይህ አውሮፕላን በግብጽ አየር ሃይል ውስጥ የለም። ያለው አንቶኖቭ 24 ነው። ሌላዋ ሃገር ፓኪስታን ናት። ከግብጽ ይልቅ ፓኪስታን በእኛ ጥርጣሪ ጎልታ ወጥታለች። አንቶኖቭ 26 አላት። መሳሪያም በገፍ ትሸጣለች። ባጭሩ የኢትዮጵያ መንግስት መታሁ ላለው ማስረጃ አላቀረበም። ግን ወደ 40 ሰው መጫን የሚችለው ይህ የትራንስፓርት የጦር አውሮፕላን በውስጡ መሳሪያ ከመጫኑ ሌላ እነማን ነበሩ? የወያኔ አመራሮች? ነጮች? አብራሪዎቹስ እነማን ናቸው? ይህ ሁሉ መልስ ያላገኘ ጉዳይ ነው። ግራም ነፈሰ ቀኝ ወያኔ ጦርነቱን ለማፋፋም የማይፈነቅለው ድንጋይ አለመኖሩን ነው።
ይህ በአዲስ አበባ የሚደረገው ዘረፋና ግድያም ከጦር ሜዳው ፍልሚያ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልኩ ጥምረት አለው። የወያኔ ዋናው መሳሪያ “ህዝብን ማሸበር ነው”። የሚገርመው የአብይ መንግስት እንዴት ገና ከጅምሩ የጠበቀ ቁጥጥር በእነዚህ ሰዎች ላይ ማድረግ እንደተሳነው ነው። ጋዜጠኛና ጦማሪዎችን፤ ፋኖዎችን ለማፈንና ለማሰር ጊዜ ያላጣው ይህ መንግስት እንዴት ነው ዘራፊና ገዳይ ለዚያውም ሃገርን ለማፍረስ እስከ ሲኦል እንወርዳለን የሚሉ ሙታኖችን ከስለላ መረቡ ውጭ ሆነው ግድያና ዝርፊያ እስኪፈጽሙ ዝም ማለቱ? አሁን የወያኔ ሰዎች የሚጠቀሙበት ስልት እኛ ኤርትራዊያን ነን በማለት መታወቂያ በማውጣት፤ በሌላ ክልሎች እንደተወለድ አርገው በማስመስከር ራሳቸውን መደበቅና እቡይ ተግባራቸውን በሌትና ቀን መፈጸም። እንዲሁም ሌሎችን የስውርና የግልጽ የፓለቲካና የሃይማኖት ግጭቶችን ለመቀስቀስ መስራት ከዘረፋና ከግድያው ተግባራቸው ጋር አብረው የሚፈጽሙት ጥምር ተግባር ነው። ሰው ሊነቃ ይገባል! ይህ ጉዳይ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በየክልሉ የተደራጅና ሌላውን በገንዘብና በማስፈራራት ጭምር ለእኩይ ተግባራቸው ያሰለፉ ብዙዎች ናቸው። ሊፈተሽ፤ ሊመረመር፤ የእዝ መሰላላቸው ሊሰበር ይገባል። ወያኔና አፍቃሪዎቹ በተንኮል የተጠመቁ የሰውን አንገት ሲቆርጡ ቅር የማይላቸው የእንስሳ ጥርቅሞች ናቸው። ለዚህም ትግራይ ውስጥ የፈጸሙትንና በመፈጸም ላይ ያሉትን ተግባር ፈትሾ ማወቅ ተገቢ ነው። ጦርነት ጫወታችን ነው የሚል ጭንቅላት የጤነኛ ጭንቅላት እንዳልሆነ እንኳን ጤና አለኝ የሚል ሰው ልብሱን ያወለቀ እብድም ያውቀዋል። ግን የወያኔ እብደት ደረጃው ከፍ ያለና ከሰው ስብዕና የወጣ ስለሆነ ለትግራይ ህዝብ እያሉ ሲያላዝኑ የትግራይን ህዝብ ጨለማ ውስጥ እየከተቱት እንደሆነ አይታያቸውም። አሁን ለ 3 ጊዜ የከፈተው ጦርነት ሲፍረከረክ ለተመድ ደብዳቤ በመጻፍ አድኑኝ ገለ መሌ ማለቱ የውስልትናቸውን ከፍታ ያሳያል። ሱዳንም ሆነ አሜሪካ ግብጽም ሆነ ሌሎች አይዞህ ባዪች ለትግራይ ህዝብ አስበው የሚያደርጉት ድጋፍ ነው ብሎ የሚያስብ ሃበሻ ካለ የቁም ሙት ነው። ሁሉም ለራሱ አጀንዳ ነው የሚሰራው። ለዘመናት ሲያጋድሉን የኖሩት እነርሱ ናቸው። ለዚህ ዋናው ማስረጃ ለ 30 ዓመት በሻቢያና በኢትዪጵያ መንግስታት የተደረገው ውጊያ ነው። የእኛ መሞት ለእነርሱ ሰርግ ነው፡፤ የእኛ መራብና መጠማት ለእነርሱ ንግድ ነው። ለአንድ እሳት ለሌላው ጭድ እያቀበሉ የሚያገዳድሉን እነርሱ ናቸው። በትግራይ ውስጥ ያለውን መከራና በአፋርና በአማራ ክልሎች የሚፈጸመውን ወንጀል አሜሪካ ከፈለገች በ 24 ሰአታት ማስቆም ትችላለች። ግን አትፈልግም። አሜሪካ ሌባውን ጳጳስ ነው የምትል ሃገር ናት። ለዚህ ነው የወያኔን ግፍና ኪሳራ እያወቁ ተመድን ከደርዘን በላይ የሰበሰቡት። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴራቸው አንቶኒ ቢሊንከን ልክ እንደ ወያኔ የውሸት ተከራካሪ በመሆን ለወያኔ ወገቡን ታጥቆ የሚሟገተው። ግን መቼ ይሆን ረሃብ፤ ጦርነት፤ መፈናቀልና ተንኮል ከሃበሻ ምድር የሚጠፋው? ባይጠፋም ሰከን የሚለው? ያ ጊዜ ይመጣ ይሆን? አይታየኝም። በቃኝ!