ትግራይ ነጻ አውጪ የተሰኘውን የወንበዴዎች ድርጅት በትግራይ ሕዝብ ስም በሕይወት እንዲቆይ እያደረጉት ያሉት በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ውስጥ በተለይ በአዲስ አበባ “ሰላማዊ” ሆነው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው በማስረጃ ተረጋገጠ።
የማኅበራዊ ሚዲያ መረጃ ላይ ጠቃሚ መረጃዎችን በማስተላለፍ የሚታወቀው እስሌማን አባይ እንዳለው “በመዲናዋ ስውር አፍቃሪ ትህነጎች ያሰራጩት የ 88 በመቶ የትዊተር የሀሰት መረጃ ዘመቻ በሳምንቱ #TPLFisTheCause የሚለው ሀሽታግ በህወሃቱ Tigray Under Attack ሐሽታግ ከ30,000 በላይ ትዊት ብልጫ ተወስዶበት ይታያል” ብሏል።
ትህነግ ጦርነቱን (ነሐሴ 17 ንጋት) ላይ ከመክፈቱ በፊት ጀምሮ ነበር tigray under attack በሚለው ሀሽታግ በመቶ ሺዎች የሀሰት መረጃ ትዊተር ማሰራጨት የጀመረው። በሳምንቱ ሰባት ቀናት ብቻም ከ 475 ሺህ በላይ ትዊቶች ሲያሰራጭ ከዚህ ውስጥ ከኢትዮጵያ በሚገኙ አካውንቶች የተሰራጨውም ሀሰተኛ መረጃም በመቶ ሺዎች ሆኗል።
አዲስ አበባ ትግራይ እና አማራ ክልሎች የህወሃቱ ሀሽታግ ከተሰራጨባቸው አካባቢዎች ሆነዋል።
በሳምንቱ ውስጥ በተጠቀሰው ሀሽታግ ከ129 ሺህ በላይ ትዊቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የትዊተር Users የተሰራጩ ሲሆን ሶስቱ ቦታዎች የነበራቸው ድርሻ የሚከተለው ነው።
አዲስ አበባ 112 ሺ የትዊተር መልእክቶች በሳምንቱ
ትግራይ ክልል ውስጥ 15,800 ሺህ ትዊቶች በሳምንት
አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች (ከመቶ በታች ትዊቶች ቢሆኑም)
በሳምንቱ #TPLFisTheCause የሚለው ሀሽታግ በህወሃቱ Tigray Under Attack ሐሽታግ ከ 30,000 በላይ ትዊቶች ብልጫ ተወስዶበት ይታያል። ይህም በመዲናዋ በሚኖሩ አፍቃረ ትህነጎች ባሰራጩት የ 88 በመቶ የትዊተር ስውር ዘመቻ የተተገበረ መሆኑ ነው ሲል እስሌማን በማኅበራዊ ድረገጹ አስታውቋል።
ከዚሁ ጋር በማያያዝም በጦርነት ወቅት እንዲህ ዓይነቱን ተግባር መፈጸም በሕግ እንደሚያስቀጣ አንቀጽ ጠቅሶ መረጃውን አስተላልፏል።
አንቀፅ 257 – የጦርነት ጊዜ መረጃ
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፣ ኢትዮጵያ በጦርነት ላይ በምትገኝበት ጊዜ የጠላትን ዓላማ ለማሳካት የሕዝብን ሞራል ዝቅ ለማድረግና እምነቱን/የመቋቋም ኃይሉን ለማፍረስ ጥላቻ የተሞላበት መረጃ በንግግር፣ በፅሁፍ/በስዕል የበተነ/ያስታወቀ እንደሆነ 10 አመት(በማይበልጥ) ፅኑ እስራት ይቀጣል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply