• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ህወሃት የበሰበሰች ናት፤ አትጠቅምም” የህወሃት ምርኮኛ

September 5, 2022 05:49 pm by Editor 1 Comment

አሸባሪው ህወሓት የቀረበለትን የሰላም አማራጭ ረግጦ ዳግም ጦርነት መክፈቱ በትግራይ ህዝብ ጫንቃ ላይ ቆሞ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ነው ሲሉ በተለያዩ ግንባሮች እጃቸውን ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰጡ ምርኮኞች አጋለጡ።

ምርኮኞቹ እንደተናገሩትም የትግራይን ህጻናት ሳይቀር ወደ ጦር ግንባር እየማገደ የሚገኘው አሸባሪው ህወሃት በሃሰተኛ ትርክት የትግራይን ወጣት ራሱ ወደለኮሰው ጦርነት እየማገደ ክልሉን ትውልድ አልባ የማድረግ እኩይ አላማውን ገፍቶበታል።

ይህም ተግባሩ የሽብር ቡድኑን የባንዳነት ትክክለኛ ባህሪ በተጨባጭ እያረጋገጠ መሆኑንም ነው ምርኮኞቹ የተናገሩት።

ምርኮኞቹ አሸባሪው የህወሃት ቡድን በትግራይ ህዝብና ህፃናት ላይ እየፈፀመ ያለውን ስቃይና እንግልት በመቃወም በፕሮፖጋንዳ ተታለው ከገቡበት ጦርነት በመውጣት ለጀግናው የሃገር መከላከያ ሰራዊት እጃቸውን መስጠታቸውን ገልፀዋል።

የሰላም አማራጭ በሰፊው ቀርቦለት ጦርነትን መርጦ ህጻናትን ሳይቀር ወደ ጦርነት እየማገደ ያለው የሽብር ቡድኑ ህወሃት የራሱን የስልጣን ላይ ቆይታ ለማራዘም ትግራይ ላይ ምንም አይነት ጥፋት ከመፈጸም ወደኋላ እንደማይመለስ ምርኮኞቹ አረጋግጠዋል።

“የትግራይ ከፍታ የሚረጋገጠው በኢትዮጵያ መቃብር ላይ ነው” በሚል ቀቢፀ ተስፋ በመነሳሳት ኢትዮጵያን ለማፍረስና ህዝቦቿን ለመበተን ዳግም ጦርነት ቢከፍትም ዓላማ ቢስ ለሆነው የሽብር ቡድኑ አላማ መሰለፍ ከንቱ በመሆኑ እጃቸውን ለመስጠት እንዳስገደዳቸው ተናግረዋል።

በቡድኑ የውሸት ወሬና ፕሮፓጋንዳ ተታለው በመሰለፍ ለፈፀሙት ጥፋት በመፀፀት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ፤ ለመከላከያ ሰራዊቱና ለሌሎች የፀጥታ ኃይል ይቅርታ ጠይቀው የህወሓት የሽብር ቡድንን ከንቱ ራስ ወዳድ አላማ ለማስፈፀም የተሰለፉ የትግራይ ወጣቶችም የሚጓዙበት መንገድ ፈጽሞ እንደማያዋጣ ተረድተው ፈጥነው እንዲነቁ ምርኮኞቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ምርኮኞቹ በመከላከያ ሰራዊትና በሌሎች የፀጥታ ሃይሎቻችን ለተደረገላቸው መልካም አቀባበልና እንክብካቤም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ከጦርነት ኪሳራ እንጂ ትርፍ እንዳማይገኝ የገለፁት ምርኮኞቹ፤ አሸባሪ ቡድን ለዳግም እልቂት የከፈተውን ወረራ በማውገዝ ወደ ሰላም እንዲመጣ የትግራይ ህዝብ፤ ወጣቶችና ልዩ ኃይል አባላት ጫና መፍጠር እንደሚገባቸው ጥሪያቸውን አቅርበዋል። (Fana)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    September 7, 2022 08:58 am at 8:58 am

    ወቸው ጉድ እንዲህ ያለ ሃበሳ በምድራችን ላይ ይውረድ? ለዚህ ይሆን ገጣሚው ሙሉጌታ ተስፋዬ ” እውነት ከመንበሩ የለህማ” በማለት ሰቆቃውን ከዘመናት በፊት ያሰማው? እንዴት ህጻናትን ወደ ጦር ሜዳ ሰው ይልካል? ግን ወያኔ ከሰው ልጅ ህልውና ውጭ ስለሆነ ጭካኔ የመለያ ምልክቱ ነው። እነዚህ ተማረኩ ወይም እጃቸውን ሰጡ ተብለው በሰልፍና በተንቀሳቃሽ ምስል የቀረቡልን ወገኖቻችን እንኳን ተረፋችሁ እላለሁ። ጦርነቱ የእብደት ስለሆነ ማንም ሰው መሞት አልነበረበትም። ግን የእብድ ገላጋዪች በሩቅና በቅርብ ሆነው እሳትና ጭድ እያቀበሉ ይነግድብናል።
    የተመድ ጽ/ቤት ወያኔ በሱዳን ባሉ መጠለያ ጣቢያዎች በግድ ስደተኞችን ለጦርነት ስልጠና እንደሚመለምል መረጃው ነበረኝ ለሱዳን መንግስትም ይህን አስታውቄአለሁ ብሎናል። ለምን የዓለም ህዝብ፤ የዓለም መንግስታት እንዲያውቁት አልተረደረገም? ለነገሩ የተመድ ዋና ጸሃፊ ራሳቸው ከወያኔው ደም አፍሳሽ ከደብረጽዪን ጋር የቀጥታ የኢሜልና የሌላም ግንኙነት እንዳደረጉ በቅርቡ ይፋ ሆኗል። ታዲያ በሰው ነፍስ ከዚህ በላይ እንዴት ይቀለዳል? አሁን እንሆ ወያኔ ለትግራይ ህዝብ የተላከውን መድሃኒትና ምግብ እንዲሁም መጠለያ በግድም በውድም ላስታጠቀው ሃይል እንዳከፋፈለው ጥሎ ከፈረጠጠባቸው የጦር ምሽጎች መገኘቱ አስገራሚ አይሆንም። ወያኔ ለትግራይ ህዝብ አንድም ቀን ገዶት አያውቅም። ልክ እንደ ንግድ ማስታወቂያ በትግራይ ህዝብ ስም ሲነግድ እንሆ ዘመናትን ተሻገርን። ወያኔ ጦርነት ከቆመ አንድ ቀን በትግራይ መሬት ላይ ውሎ እንደማያድር ያውቃታል። ስንቱን አስጨርሶና ያን ሁሉ ውሸት ዋሽቶ የትግራይ ህዝብ ዝም አይለውም። ስለዚህ ያለው ምርጫ ተከበናል፤ ሻቢያ መጣ፤ አማራ መጣ ወዘተ እያለ ሰውን ማምታታ ነው። ግን የዚህም የውሸት ቱልቱላ ጊዜው ያበቃ ይመስላል። የትግራይ ህዝብ ወያኔን አክ እንትፍ ብሎታል። በተጣረሰ የሂሳብ ስሌት የሰሜን እዝን በመምታት ወደ አዲስ አበባ እንመለሳለን ብለው ያሰቡት እቅድ ፉርሽ ሆኖ ይኸው እንሆ ሃገርና ወገን ያስጨርሳሉ። የአሜሪካና የአውሮፓ ለወያኔ ድጋፍ በማድረግ ኡኡታ ማሰማታቸው ሊያስገርመን አይገባም። ሲጀመር የእነዚህ ሃገሮች የጥቁር ህዝቦች እይታ ጠንጋራ ነው። በተለይ አሜሪካ ዪጎዝላቪያን አፍርሳ፤ አሁን ደግሞ ከጅብ የማያስጥል ባል ሆኗ በሩቅ ዪክሬንን አይዞአችሁ እያለች ታስጠብሳለች። ፍትህ በጀርባው ተኝቶ የሚፈራገጥበት አንድ ስፍራ ቢኖር በአሜሪካ የውጭ ፓሊሲ አርቃቂዎችና አስፈጻሚዎች ቢሮ ነው።
    ቁርጠኛ የትግራይ ልጆች ይህ ጦርነት እንዲቆምና የትግራይ ህዝብ መሳሪያ ባነገቱ ከማህል ሃገር በመጡ ወይም ከራሱ አብራክ በወጡ ሃይሎች ሳይሆን ራሱ በመረጠውና በወከላቸው እንዲተዳደር ሊታገሉ ይገባል። የጦርነቱ መቀጠል ለማንም አይጠቅምም። እየሞቱ መግደል ድል አይደለም። ከዚህ ውጭ እንደ ዓለም የጤና ጥበቃ ዳሬክተር በተገኘው መድረክ ሁሉ የአዞ እንባ ማንባት ከትዝብት ሌላ ፍሬ አያስገኝም። ዶ/ር ቴዎድሮስ ለሰላም ጥሪ ማድረግ እንጂ በዘሩ ተሰልፎ ማንባቱ ነገሩን ያብሰዋል እንጂ እንዲገታ አይረዳም። የትግራይ ህዝብ ሲበደል የሚሰማው የትግራይ ተወላጅ የሆነ ብቻ አይደለም። ሁሉም ኢትዪጵያዊ እንጂ! ይህ የዘር ፓለቲካ ሰውን አንሻፎ እያስኬደ ሰውን በሰውነቱ እንዳንመዝን አርጎናል። ወያኔንና የዘር ተሰላፊዎችን የሚደግፉ ማንኛውም አይነት ቱልቱላ ነፊዎች ሁሉ ከንቱዎች ናቸው። የሰው መለኪያው ሰውነቱ ብቻ ነው። ቋንቋህን ቀርጥፈህ ብላው፤ ሃይማኖትህን የራስህ አርገው፤ ዘርህን ምን ያህል ወደኋላ ቆጥረህ እንደምትደርስበት አስላው። ከ 10 እጣቶችህ አያልፍም። ባይደንቅህ (Humans and chimps share a 98.8% of their DNA) ዝም ብሎ የጠራ አማራ፤ የጠራ ትግራዋይ፤ የጠራ ኦሮሞ ገለመሌ ማለቱ ራስን ማታለል ነው። ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በትግራይ፤ በአፋር፤ በአማራ የሚፈሰው ደም የሰው ደም እንጂ የዘር ደም አይደለም። የዘርና የቋንቋ የክልልና ከሃገራችን ውጡልን የሚሉን ሁሉ ልበ ቢሶችና የማሰብ ችሎታቸውን የተቀሙ ድርቡሾች ናቸው። መገዳደል ይብቃ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule