• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ውረሩ፣ ያገኛችሁትን ግደሉ እየተባልን ነው የምንመጣው” እጃቸውን የሠጡ የትህነግ ታጣቂዎች

September 8, 2022 02:46 am by Editor 1 Comment

በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ላይ የተነሳው የሽብር ቡድን በሕዝብ ላይ አያሌ በደሎችን አድርሷል። ከእኩይ ቡድን አቅራቢያ የሚገኙ የአማራና የአፋር ክልል ነዋሪዎች ደግሞ የሽብር ቡድኑ ግፍና ወረራ ገፈት ቀማሾች ናቸው። ለሦስተኛ ጊዜ ጦርነት ያነሳው የትህነግ የሽብር ቡድን የትግራይ ተወላጆችን ከሕፃናት እስከ አዛውንት ድረስ እየመለመለ ለጦርነት እየላካቸው ነው።

የሽብር ቡድኑ በአማራና አፋር ክልል በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች ንፁሐንን በጅምላ ረሽኗል፣ ሃብትና ንብፈታቸውን ዘረፏል አውድሟል። የሽብር ቡድኑ የሚልካቸው ታጣቂዎች ሀገሩን እየተከላከለ በሚገኘው ጥምር ጦር እየተመቱ ብዙዎች ይረግፋሉ። እድል የቀናቸው እጃቸውን ሰጥተው ሕይወታቸውን ያተርፋሉ።

የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች በወልቃት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ለሚገኘው ጀግናው የሀገር መከላከያ በርካቶች እጃቸውን እየሰጡ ነው። እጃቸውን ከሰጡት መካከከል የሽሬው ተወላጅ አብርሃም በሪሁ ይገኝበታል። የትህነግን የሽብር ቡድን ከመቀላቀሉ አስቀድሞ የፌዴራል ፖሊስ አባል የነበረው አብርሃም የሰሜን ዕዝ በተካደ ጊዜ በትግራይ ልዩ ኃይል በቁጥጥር ሥር ዋልኩ ይላል። ከዚያ በኋላ የሽብር ቡድኑን እንዲቀላቀል ይጠይቁታል። እርሱም እምቢ እንዳላቸው ይናገራል። ከዚያ በኋላ ግን በግዳጅ የሽብር ቡድኑን ተቀላቅያለሁ ነው የሚለው። አብርሃም አለቆቹ “የብልጽግናን ወታደር እንደመስሰዋለን፣ ደምስሰን እኛ እራሳችን እንመራቸዋለን” እንደሚሏቸው ተናግረዋል።

የብልጽግና ወታደር መከላከያ፣ ልዩ ኃይልና ፋኖ ሊወጋችሁ መጥቷል እንደሚባሉም ገልጿል። የመከላከያን ምት አልችል ሲል እጁን እንደሰጠ የሚናገረው አብርሃም ያን ሁሉ ግፍ ያሳለፈ መከላከያ እንደዚህ ይቀበለናል ብዬ አላሰብኩም ነበር ብሏል። ላደረጉልኝ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል፣ በጣም ተንከባክበውናል ነው ያለው።

ከሰባት ዓመት በላይ ያለ ሰው እንዳይቀመጥ ከመጡ ያርዷችኋል ይሉናል። “ይገድሏችኋል፣ ያርዷችኋል፣ ቤት ውስጥ ቁጭ ብላችሁ ከምትሞቱ ገድላችሁ ብትሞቱ ይሻላችኋል፣ ከሰባት ዓመት በላይ ያለን ሰው ይገድላችኋል፣ ከሞት ላትተርፉ ነገር ዝም ብላችሁ ወደ ውጊያ ብትገቡ ይሻላችኋል” ይሉናልም ብሏል።

ለግዳጅ እምቢ ያለ ልጅ እናት አባቱ ይታሠራሉ፣ እናት አባት ሲታሠሩ የግድ ወደ ውጊያ እንገባለን ነው ያሉት። የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጥተው በታላቋ ኢትዮጵያ በሰላም እንዲኖሩም ጥሪ አቅርቧል።

በትግራይ ለእርዳታ የሚገባው እህል ለባለሀብቶች እና ለባለስልጣናቱ እንደሚከፋፈል የተናገረው አብርሃም የማመላለሻ ነዳጅ የለም በሚል ሰበብ ደሃው ማኅበረሰብ እርዳታ እንደማይደርሰውም ተናግሯል። የተራቡ ድሃዎች እያሉ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች የእርዳታ ምግብ እየተመገቡ እንደሚዋጉም አረጋግጧል። “ስንቅ ከሕዝባችን፣ ትጥቅ ከጠላታችን” እየተባለ አብዛኛው ታጣቂ ማርከን እናስታጥቃችኋለን እየተባለ በባዶ እጁ ነው የሚገባው ነው ያለው።

“ውረሩ፣ ያገኛችሁትን ግደሉ” እየተባልን ነው የምንመጣውም ብሏል።

የ55 ዓመቱ ገብረ ሰንበት ገበረ ኪዳን ደግሞ ነባር ታጋዮች ተብለን አዲስ ክፍለ ጦር ተመስርቶልን ወደ አፋር ተላክን ነው ያሉት። ከአፋር በኋላ ወደ ትግራይ ተመልሰው በወልቃይት በኩል መምጣታቸውንም ገልፀዋል። በተደጋጋሚ እየከዳሁ በተደጋጋሚ በግዴታ ተመልሼያለሁ ነው ያሉት። ለመከላከያ ሠራዊት እጃቸውን ከሰጡ በኋላ በጥሩ እንክብካቤ ላይ እንዳሉም ተናግረዋል።

የአክሱም ተወላጇና የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት ተማሪዋ ሮዛ ሙሉጌታ ከቤቱ እኔ ነኝ ታላቋ፣ ከቤት አንድ ሰው መውጣት ደግሞ ግዴታ ነው፣ ብዙ ጊዜ ተደበቅሁ፣ ነገር ግን ቤተሰብ ይታሠራሉ፣ ቤተሰብ ከሚታሰሩና ከሚንገላቱ እኔ ብሞት ይሻለኛል ብዬ መጣሁ ነው ያለችው። በሽብር ቡድኑ ውስጥ ለሁለት ወራት እንደቆየች የተናገረችው ሮዛ ያለ መሣሪያ ውጊያ እንዳስገቧትና እጇን መስጠቷን ነው የተናገረችው።

ትግራይን ታላቅ ማድረግ አለብን ይሉናልም ብላናለች። የትህነግ የሽብር ቡድን መሪዎች የሚፈልጉት እንዲፈፀምላቸው እንጂ ሕዝቡ የሚፈልገውን አንዳችም ነገር እንደማያዳምጡና እንደማይቀበሉም ገልፃለች። የትግራይ ሕዝብ የሕወሃት ጠብ አጫሪነት እና እንግልት እንደሰለቸውም ሮዛ ተናግራለች። የሕወሃት መሪዎች ለስልጣናቸው ሲሉ የማያደርጉት ነገር እንደሌለም አስታውቃለች።

እርዳታ ስጡን ስንል፣ የእርዳታ እህል አይገባም፣ እህል የለም ይሉናል፣ ነገር ግን ስልጠና ከገባሁ ጀምሮ የምመገበው የእርዳታውን ስንዴ ነው፣ የገባኝ አሁን ነው እርዳታውን ታጣቂው እንደሚበላው ነው ያለችው።

“የትግራይ ልጆች ለማይሆን ነገር ዋጋ አትክፈሉ፣ እጃችሁን ስጡ፤ እኔ እጅ የሰጠኹባቸው ሰብዓዊነት የሚሰማቸው እና እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ናቸው፣ እናንተም እጃችሁን ስጡ፣ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ እጃችሁን በመስጠት ተባበሩ” ነው ያለችው ሮዛ።

ውረሩ የሚባሉት ሕዝብ በሚናገራቸው ልክ ሳይሆን ደግና ከትግራይ ሕዝብ ጋር መቼም ቢሆን እንደማይለያይም ገልጸዋል ታጣቂዎቹ። (ታርቆ ክንዴ፤ አሚኮ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: eprdf, Ethiopia, ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfai Habte says

    September 9, 2022 03:12 am at 3:12 am

    የኢትዮጵያን መሪዎች ዛሬ ነቅተዋል እንጂ የ ወያኔ ልብ እንደፈለጉት ነው የሚዘውረው የነበረው። ሰላም እያለ፡ ስንቅና መድሃኒት መግብ ዚያገባ ጦርነት ይጀምራል። የኣብይን ርህራሄ እንደ ጅልነት ቆጥሮ ለሰወስተኛ ግዜ ጦርነት መክፈቱ ለጥፋቱ መሆኑ ወያነ ረስቶትስል።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule