“እኛ ትግሬ አንጠላም፣ እነሱ ግን አሁም ያሳድዱናል። ለምን ያሳድዱናል?” የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ በመቀሌ ንግግር ከፍተኛ አቧራ ያስነሳውን የወልቃይትን ጉዳይ ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ከኮሚቴው አባላት ጋር በመነጋገር መቁዋጫ አድርጎለታል። በቅድሚያ ጎንደር ላይ ባደረገው ንግር ይህንን ብሎ ነበር፤ "የወልቃይትን ጉዳይ በተመለከተ በህግ አግባብ ሊፈታ እንደሚችል ህዝቡ ማመን አለበት። ህገ መንግስቱ ይህን ጉዳይ ሊፈታ ይችላል። በቀጣይም ከወልቃይት ኮሚቴዎች ጋር ውይይት አደርጋለሁ ብለዋል፤ጠቅላይ ሚኒስትሩ። በመወያየት ያሉ ጥያቄዎች መመለስ እንችላለን። ዋናው ነገር በዚህ ሂደት ውስጥ ሀይል የተቀላቀለበት እና ወደ ቁርሾ በሚያስገባ መንገድ መሆን እንደሌለበት ህዝቡ ሊያውቅ ይገባል”። ከማህበራዊ ድረገጽ በተገኘ መረጃ ደገሞ ከወልቃይት ኮሚቴ አባላት ጋር … [Read more...] about ጠ/ሚ/ር አብይ “የወልቃይት ኮሚቴ አባላቱን ከወንበር ተነስቶ ይቅርታ ጠይቋል”
Archives for April 2018
የዶ/ር አብይ አህመድ አዋላጅነት ጉዳይ
ቃሉ የሕዝብ ነው። ቃሉንም በተግባር የሚተረጉመው ሕዝብ ነው። የወንዝ ውሃ ሽቅብ እንደማይፈስ ሁሉ፥ ይህም ቃል ወደ ተግባር ሳይቀየር ይቀለበሳል ብሎ መጠበቅ ተገቢ አይደለም። ይልቁንስ ይህን ቃል ለመተግበር የዶ/ር አብይ ድርሻ ምንድነው ብሎ አውቆ በዚያው ሚዛን ብቻ እርሳቸውን መመዘን ያስፈልገናል። ለሕዝብ ታማኝ ባይሆኑ፥ እሳቸው ከታሪካዊነት ይጎድላሉ እንጂ የሕዝብ ቃል ዕውን መሆኑ አይቀሬ ነው። ዶ/ር አብይ አህመድ የሚናገሩት ቃል እርሳቸው የፈለሰፉት ስለሆነ አይደለም የተወደደው። ቃሉ የሕዝብ ቃል ስለሆነ ነው እንጂ። ይህ ሰሚ ያጣ ሕዝብ በትግሉ የራሱን ቃል የሚያስተጋባ ጠ/ሚ ሊያመጣ ቻለ። ታዲያ ይህን ቃል የዶ/ር አብይ የግል ንብረት ተደርጎ፥ ቃል ዋጋ የለውም ብሎ ቃሉን ማጣጣል ለኢትዮጵያ አይጠቅምም። የውልጃ አብሳሪ የሆነ ቃል በውልደት ቀን ዋዜማ ሲሰማ፥ በተስፋና በትጋት ይህን … [Read more...] about የዶ/ር አብይ አህመድ አዋላጅነት ጉዳይ
አብይ አህመድ፤ ለክፉ ቀን የታሰበ የኦሮሞ ወጣቶች ብሶት ማስታገሻ?
የዶ/ር አብይ መሾም “ይህንን ክፉ ቀን የኦሮሞ ወጣቶችን አስታግሶ ለማለፍ” ይሆን? የዶ/ር መረራ ጥያቄ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ቃለምልልስ የሰጡት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በአዲሱ ጠ/ሚ/ር ሹመትና የወደፊት የኢትዮጵያ ፖለቲካ አካሄድ ከኢህአዴግ ድርጅታዊ አሠራር አንጻር ትንታኔ ሰጥተዋል። “ኢህአዴግ ለምን ተዘጋጅቷል?” የሚሉት መረራ ቀለል ያሉ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ያስከትላሉ፤ “ለነጻና ፍትሃዊ ምርጫ፤ ለሃቀኛ የፖለቲካ ውድድር (ኢህአዴግ) ተዘጋጅቷል ወይ?” በማለት ይጠይቃሉ። ራሳቸው ሲመልሱትም “ይህንን ካሁኑ ለመገመት ያስቸግራል” ይላሉ። የጠ/ሚ/ሩ ተስፋ የተሞላበትን ንግግሮች ሁሉ መልካም መሆናቸውን ቢገልጹም እርሳቸው እንደ ዜጋ እና ድርጅታቸውም እንደ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ የአብይ አህመድን ንግግሮችና የወደፊቱን ሁኔታ “ጥንቃቄ የተሞላበት … [Read more...] about አብይ አህመድ፤ ለክፉ ቀን የታሰበ የኦሮሞ ወጣቶች ብሶት ማስታገሻ?
ህወሓት እስክንድርን ከአገር እንዳይወጣ በመከልከል ባላሰበው ማነቆ ውስጥ ገባ
በኔዘርላንድ በሚደረግ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል 50ኛ ዓመት ክብረበዓል ላይ ለመገኘት ተጋብዞ የነበረው እስክንድር ነጋ ሐሙስ ሌሊት ለአርብ ጠዋት ቦሌ ላይ ከአገር እንዳወጣ ታግቷል። ጎልጉል ባገኘው መረጃ መሠረት ጉዳዩ ህወሓትን ትልቅ ቅርቃር ውስጥ ከቶታል። ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩት የመብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት ይህ ፈጽሞ መከሰት ያልነበረበት ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስ ጠ/ሚ/ር አብይ በጉዳዩ ላይ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡበት ጠይቀዋል። ሌላው ለጉዳዩ ቅርበት ያለውና ክስተቱ እንደተፈጸመ አጭር ዘገባ ያሰራጨው ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ “ከሌሊቱ 8 ሰዓት ቦሌ ያሉ የደህንነት አካላት ፓስፖርቱን ቀምተው አትሄድም ብለውታል። የከለከሉበትን ምክንያቱን ግን አልገለጹም” ብሏል። ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ከቦሌ አካባቢ ባገኘው መረጃ መሠረት እስክንድርን … [Read more...] about ህወሓት እስክንድርን ከአገር እንዳይወጣ በመከልከል ባላሰበው ማነቆ ውስጥ ገባ
PM Abiy and a call to build the capacity of stakeholders
In my latest commentary, I shared the second leadership attribute of Dr. Abiy, one of the New Breed Leaders of Africa. I pointed out that since he had done his homework and developed his personal growth very well that he outgrew his past leadership positions and outlived the challenges he had been facing. This is my hope that this same quality is one of the virtues that could empower him to lead the country’s transformation successfully. However, before I cover his third leadership attribute on … [Read more...] about PM Abiy and a call to build the capacity of stakeholders
የጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ራእይ
እንደ መግቢያ ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ስለዶ/ር አብይ ያለኝ የጠለቀ እውቀት ወይም ከነበሩበትና ከተነሱበት ፓርቲና ፓርቲው ከሚያራምደው የፖለቲካ አመለካከት ጋር ያለኝ ጠብ ወይም ዝምድና አይደለም። ይልቁንም እንደ አንድሀገር-ወዳድ ኢትዮጵያዊ ባለው የህወሃት የበላይነትን የተከተለ ፍጹም ዘረኛ ጉዞ ሄደን ሄደን የደረስንበት ደረጃ በጣም አሳሳቢ መሆኑን በመመልከት ነው። በዘረኛው የወያኔ ከሩብ ምእተ አመት የዘለለ የጥፋት ጉዞ ውስጥ ከተጓዙና ከጉያቸው የበቀሉ ዘረኛው ስርአት ከሚያራምደው የተለየና የተሻለ ራእይ ያለው ጉዞን የመረጠ የኦሮሞ፣ የአማራ እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ ወጣቶች በደምና በህይወት ጭምር ዋጋ የከፈሉበትን ትግል ባዳመጠ መልኩ የተቃኘ ‘ቲም ለማ’ ከተባለ የለውጥ አራማጆች ውስጥ የበቀሉት የዶ/ር አብይ ራእይ ምን ቢሆን ለሐገር የሚበጅ መድህን ይሆናል የሚለውን … [Read more...] about የጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ራእይ
እኛም እንዳንሰቅለው!
እንደምን? ይመጣል! ከናዝሬት ላይ ነብይ፣ ልክ እንደተባለው ከወያኔም ዓብይ፣ ተገኝቶ ከመጣ - ጌታ ከመረጠው፣ ፈራሁኝ እንደሱ እኛም እንዳንሰቅለው! (ወለላዬ ከስዊድን) … [Read more...] about እኛም እንዳንሰቅለው!
HR 128 መጽደቅ ለመሰረታዊ የመብት ትግላችን ታላቅ ድጋፍ ነው
ሸንጎ ህጉን ይደግፋል፤ ለተፈጻሚነቱም ተግቶ ይፋለማል HR 128 ተብሎ የሚታወቀው ባሜሪካ ኮንግረስ (ፓርላማ) ውስጥ ለውሳኔ ቀርቦ የነበረው በኢትዮጵያ መንግስት የመብት አያያዝ ላይ ያተኮረ የህግረቂቅ እነሆ ትናንት መጽደቁ ተነገረ። በውጭ አገር ያሉ የሰብዓዊ መበት ተከራካሪዎችና የተደራጁ ኢትዮጵያውያን ይህ የህግ ረቂቅ እንዲጸድቅና በስራ ላይ እንዲውል ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ ተጋድሎ ሲያድርጉ ቆይተዋል። ሸንጎ ለዚህ ስኬት ታጥቀው ለታገሉ ሃይሎች በሙሉ ያለውን አድናቆትና ክብር እያስታወቀ፤ የረቂቁ ህግ ሆኖ መጽደቅ ለኢትዮጵያ ህዝበና ለመላው የዴሞክራሲ ሃይሎች ታላቅ ድል መሆኑን ይገልጻል። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ … [Read more...] about HR 128 መጽደቅ ለመሰረታዊ የመብት ትግላችን ታላቅ ድጋፍ ነው
አምቦ ትናንትና ዛሬ!
አምቦ ስሟ ሲጠራ የብዙዎቻችን ልብ በሃሴት እንደሚሞላ ሁሉ ወያኔዎችና አሽቃባጮቻቸው አጥንታቸው ድረስ የሚዘልቅ ብርድ እንደሚሰማቸው ግልፅ ነው። ያች ምድር የብዙ ጀግኖች መፈጠርያ ናት። ጣልያንን ብርክ ያስያዙ ጀግኖቿን ታሪክ ሲያስታውሳቸው ቢኖርም ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው የአባቶቻቸውን ጋሻ አንስተው የሃገር ጠላት የሆነን ስርዓት በመፋለም ለሌላውም አንቂና አበረታች ሆነው እነሆ እነሱም ታሪክ ሠሩ። አምቦዎች ወያኔን መፋለም የጀመሩት ገና ከመጀመርያው ነው። ከሁሉም በላይ ባለፈው ሶስት ዓመት የአምቦና የአካባቢ ጀግኖች፣ ቄሮዎች የለኮሱት አመፅ መላ አገሪቷን ከዳር ዳር አዳርሶ እነሆ ዲያስፖራንም አነቃንቆ HR 128 በማስወሰን በወያኔ አንገት ገመድ አጥልቆለታል። አምቦና ወያኔ ዐይንና ናጫ ናቸው። ወያኔ በጎንደር፣ በጎጃምና በወለጋ አቆራርጦ ሲገሰግስ ሊሞት አንድ ሃሙስ የቀረው ደርግ … [Read more...] about አምቦ ትናንትና ዛሬ!
ያልታሰበው H. Res. 128 ውሳኔ እና የህወሃት መብረክረክ
ያልታሰበ ነው። ፈጽሞ ያልተገመተ። አገዛዙን እንደ ቀትር መብረቅ ያስደነገጠ ውሳኔ። በጸረ-ሽብር ስም በሚተውኑት የፖለቲካ ድራማ ሳብያ አሜሪካ ይህን አይነት ውሳኔ አጋር በሆነ አካል ላይ ትፈጽማለች ብለው ለአፍታ እንኳን አስበውት አያውቁም። በዚያ ላይ ደግሞ በሚሊዮን ዶላር የሚከፈላቸው ሎቢስቶች ጉዳዩን ይዘውልናል ብለው ተዘናግተዋል። “ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አሕመድ ዕድል እንስጥ” የሚለው የኦክሎሃማው ሴናተር ጄምስ ኢንሆፍ ሃሳብ ያሸንፋል የሚል ግምትም ነበራቸው። ንቀታቸው እና ትዕቢታቸው የት እንደደረሰ የተመለከትነው፤ ሰነዱ ምክር ቤት ሊቀርብ ቀናት ሲቀረው እንኳ ዜጎችን ከእኩይ ተግባራቸው ያልመቆጠባቸው ነው። በሽብር የወነጀሏቸውን የዋልድባ መነኮሳት አሁንም እያሰቃዩዋቸው ይገኛሉ። ሰነዱ ሊጸድቅ አንዲት ቀን ሲቀረው በምስራቅ ሀረርጌ፤ ቆቦ ከተማ ነፍሰጡርዋን በጥይት … [Read more...] about ያልታሰበው H. Res. 128 ውሳኔ እና የህወሃት መብረክረክ