- “እኛ ትግሬ አንጠላም፣ እነሱ ግን አሁም ያሳድዱናል። ለምን ያሳድዱናል?” የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ
በመቀሌ ንግግር ከፍተኛ አቧራ ያስነሳውን የወልቃይትን ጉዳይ ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ከኮሚቴው አባላት ጋር በመነጋገር መቁዋጫ አድርጎለታል።
በቅድሚያ ጎንደር ላይ ባደረገው ንግር ይህንን ብሎ ነበር፤
“የወልቃይትን ጉዳይ በተመለከተ በህግ አግባብ ሊፈታ እንደሚችል ህዝቡ ማመን አለበት። ህገ መንግስቱ ይህን ጉዳይ ሊፈታ ይችላል። በቀጣይም ከወልቃይት ኮሚቴዎች ጋር ውይይት አደርጋለሁ ብለዋል፤ጠቅላይ ሚኒስትሩ። በመወያየት ያሉ ጥያቄዎች መመለስ እንችላለን። ዋናው ነገር በዚህ ሂደት ውስጥ ሀይል የተቀላቀለበት እና ወደ ቁርሾ በሚያስገባ መንገድ መሆን እንደሌለበት ህዝቡ ሊያውቅ ይገባል”።
ከማህበራዊ ድረገጽ በተገኘ መረጃ ደገሞ ከወልቃይት ኮሚቴ አባላት ጋር ሲነጋገር ይህንን ማለቱ ተዘግቧል፤ “የጎንደር ሕዝብ አኩርፎብሃል አትሂድ ተብዬ ነበር። ቢበዛ ቆንጥጦ ቢያስተምረኝ ነው ብየ መጥቻለሁ”።
ጌታችው ሽፈራው ደግሞ ከተሰብሳቢዎቹ የተገኘ መረጃ ያለውን በዚህ መልኩ አቀናብሮታል፤
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኮሚቴ አባላቱን ከወንበር ተነስቶ ይቅርታ ጠይቋል
ዶ/ር አብይ አቶ አታላይ ዛፌን፣ጌታቸው አደመን፣ ተሻገር ወ/ሚካኤልና ወረታው አዛናውን ጠርቶ አናግሯል። የኮሚቴ አባላቱን ከወንበር ተነስቶ ይቅርታ ጠይቋል።
በውይይቱ ወቅት አቶ አታላይ ዛፌ “ወንድ ልጅ ራሱን ይዞ ያለቀሰበት ጊዜ ቢኖር እርስዎ መቀሌ ላይ በወልቃይት ጉዳይ ከተናገሩ በኋላ ነው። ወልቃይት ብዙ ስቃይ ይፈፀማል። በአማርኛችን እንኳ መዝፈን አንችልም። አስከሬን በወጉ መቅበር አንችልም። አሁንም በወልቃይት ጉዳይ እስር ቤት የሚገኙ አሉ። በወልቃይት ጉዳይ 9 ወጣቶች በቅርቡ ተከሰዋል። እኛ ትግሬ አንጠላም፣ እነሱ ግን አሁም ያሳድዱናል። ለምን ያሳድዱናል? የወልቃይትን ጥያቄ ያነሳው ዲያስፖራ አይደለም። ዳያስፖራም ቢሆን ከባህር አሳ፣ ከኮንቴነር ሞት ተርፎ የተሰደደ ወገናችን ነው፣ ሲሞት አስከሬኑ ታሽጎ የሚላክልን ወገናችን ነው። ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱልም እንፈልጋለን። ነገር ግን እኛ በዳያስፖራ አንመራም” ሲል ለዶ/ር አብይ ቅሬታውን አቅርቧል።
ዶ/ር አብይም ወደፊት ከኮሚቴዎቹ ጋር እንደሚወያይ፣ መቀሌ የመለሰው ጥያቄ ከማንነት ጋር በቀጥታ የተገናኘ ሳይሆን አንድ ሰው “ዳያስፖራ እያፋጀን ነው” ብሎ ለጠየቀው ጥያቄ እንደሆነ ገልፆላቸዋል። “የወልቃይት ጉዳይ በእኔ በአንድ ሰው፣ በስብብሰባ አዳራሽ የሚፈታ አይደለም” እንዳለም ታውቋል።
(መረጃዎቹ ከተስሳቢዎቹ የተገኙ ናቸው)
ህወሓት/ኢህአዴግ “ፓርላማ” ባለው ስብስብ በሶማሊያ የሞቱት ወገኖቻችን ስንት እንደሆኑ እንዲነገር ለሞተው መለስ ዜናዊ ጥያቄ ሲቀርብለት ፓርላማው የመጠየቅ መብት እንደሌለውና ማንም እንደማያገባው በእብሪት መናገሩ የሚረሳ አይደለም። ከዚህም ሌላ በምርጫ 1997 ለሞቱት ሰዎች ይቅርታ ትጠይቃለህ ወይ በማለት የቢቢሲ ሃርድ ቶክ ጋዜጠኛ ስቲፈን ሳኩር ሲጠይቀው እብሪተኛው መለስ ሰው ስለሞተ አዝናለሁ፤ ተጣርቶ እስኪታወቅ ግን ይቅርታ አልጠይቅም ማለቱ የሚዘነጋ አይደለም።
ጎልጉል፥ የድረገጽ ጋዜጣ
(መግቢያ ፎቶ፤ ሪፖርተር)
Mulugeta Andargie says
ወልቃይት ምን ጊዜም ቢሆን የትግራይ ክልል ህዝብ ነው!! ብዙ ማስረጃ ኣለኝ!!
aradaw says
Let us hear and see.
Joe Mama says
Dr. Abeye You got the power with the help of the Ethiopian people take charge!!!!
Joe Mama says
Dr abeye You are between a rock and a hard place. We understand your position try to do your best
or explain to the Ethiopian people if mafia hooligans in your way and resign with honor
don’t be like you know who
Ezira says
ጎበዝ!አንርሳ
ጉጭማው የትግሬ ወያኔ አለቃ መለስ ዜናዊ እኮ ስልጣኑን ከጨበጠ ጀምሮ እስኪደፋ ድረስ አንድም ጊዜ ፊቱ ተፈትቶ አይታችሁት ታውቃላችሁ ? በጭራሽ። ምክኒያቱም የትግሬው ወያኔ ነፃ አውጭ ግንባር እንደ ግንባር ፡ ጉጭማው ለገሰ ዜናዊ ደግሞ እንደ ግል የነጮቹ ባሪያ ሆኖ ሊያገለግል የተሸጠ መሸጦ ስለነበር ነርቭስ ነበር – አግሬሲብም ነበር። ምክንያቱም ሲጀመር የተገዛ ባሪያ ስለነበር ለገዙት አለቆቹ ግሩም ባሪያ መሆኑን ለማሳየት ሲተጋ ……የኢትዮፕያ ህዝብ ደግሞ የቆመበትን ምንጣፍ ከታች እየሳበ ይገዘግዘው ነበር። በዚህ ምክንያት የበታችነቱን ለመደበቅ ዳቦ በቀደደው አፉ “ወራዳ እደገመዋለሁ ወራዳ”፡ እያለ ውስጣዊ ጭንቀቱን በስድብ ያንፀባርቅ ነበር። የሚሳደብበት አፉም ስለሚደረቅ በየደቂቃው ዉሃ ይጠጣ ነበር። በመጨረሻም ተቀጣሪ ባሪያ ማንነቱና የተቀመጠበት የምንሊክ ወንበር ተቃርኖ ነቀርሳ ሆኖ ወደ መቃብር ከተተው። Thanks God