• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ራእይ

April 18, 2018 05:48 am by Editor Leave a Comment

እንደ መግቢያ

ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ስለዶ/ር አብይ ያለኝ የጠለቀ እውቀት ወይም ከነበሩበትና ከተነሱበት ፓርቲና ፓርቲው ከሚያራምደው የፖለቲካ አመለካከት ጋር ያለኝ ጠብ ወይም ዝምድና አይደለም። ይልቁንም እንደ አንድሀገር-ወዳድ ኢትዮጵያዊ ባለው የህወሃት የበላይነትን የተከተለ ፍጹም ዘረኛ ጉዞ ሄደን ሄደን የደረስንበት ደረጃ በጣም አሳሳቢ መሆኑን በመመልከት ነው።

በዘረኛው የወያኔ ከሩብ ምእተ አመት የዘለለ የጥፋት ጉዞ ውስጥ ከተጓዙና ከጉያቸው የበቀሉ ዘረኛው ስርአት ከሚያራምደው የተለየና የተሻለ ራእይ ያለው ጉዞን የመረጠ የኦሮሞ፣ የአማራ እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ ወጣቶች በደምና በህይወት ጭምር ዋጋ የከፈሉበትን ትግል ባዳመጠ መልኩ የተቃኘ ‘ቲም ለማ’ ከተባለ የለውጥ አራማጆች ውስጥ የበቀሉት የዶ/ር አብይ ራእይ ምን ቢሆን ለሐገር የሚበጅ መድህን ይሆናል የሚለውን ለማየት የአዲሱን ጠቅላይ ሚስተር ራእይ ከተጨባጭና ከሐሳብ ወለድ መንደርደሪያ በመነሳት ጠቃሚ ያልኩዋቸውን ምልከታዎች በማጣመር ለመመልከት እሞክራለሁ።

የዶ/ር አብይ አህመድ ራእይ እንደማእከላዊ ነጥብ የዶ/ር አብይ ራእይ በማለት መጪውን የሀገሪቱን እጣ ፈንታ ለመመልከት በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ውስጥ ቲም ለማን አካቶ ማየትንና የኒሁ ወጣት የለውጥ አራማጅ መሪን ጉዞ እሳቸውና ቡድናቸው ለወጣት ኢትዮጵያውያን በፈነጠቁት ተስፋና ባሳዩት የኢትዮጵያዊነት ስሜት ላይ በተመሰረተ አላማ ዙሪያ መመልከቱ አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስቴር በወያኔ ዘመን ከተለመደውና በአንድ ጎሳ ጥቅም ዙሪያ ላይ አነጣጥሮ ከተመሰረተው ፓርቲያቸው (ኦሕዲድ) አላማ በሰፋ መልኩ የኦሮሞና የሌላው ኢትዮጵያዊ አንድነት በማይናወጥ መሰረት ባለው አመላካከታቸው በኢትዮጵያ መፈራረስ የሚምለው ህወሃት የጥፋት ጉዞን በፍርሐት ቆፈን ሳይሆን በተረጋጋ አስትዋይ ኢትዮጵያዊ አእምሮ መመልከታችውን በግልጽ በማሳየታችው ይህንን ራእይ ዘመኑ በፈጠረብን መጠራጥር ውስጥም እንኩዋን ተስፋን ልንቸረው ይገባል ባይ ነኝ።

የአብይን ራእይ በሐይለማሪያም ራእይ (እሱም ከነበረ) ለማወዳደር ባልዳዳም ጠቅላይ ሚኒስትርነት በኢትዮጵያ ምን ያህል የተዋረደና ተራ የአዛውንት ወያኔዎች ተላላኪ ከመሆን የዘለለ ወሳኝ ከፍተኛ የስልጣን ደረጃ መሆኑን ለመመልከት ያለንን ጉጉትና ፍላጎት ከፍ ማድረጉን ግን በንጽጽር መግለጹ ጥሩ ማሳያ ነው የሚል ስሜት አለኝ።

እነዶ/ር አብይ በብዙ ኢትዮጵያን ያተረፉት ቅቡልነት ‘ከሀምሳ ዘመን በላይ ዘርና ዘርን ብቻ ያቀነቀኑ የብሔር ፖለቲከኞት ለምን አላገኙትም?’ ብለን ብንል መልሱ ለኢትዮጵያዊነት የሰጡት ክብርና ስለሓገር አንድነት የተናገሩት መሳጭ ንግግሮቻቸው ለመሆኑ ብዙ አስረጂ የሚጠይቅ ጉዳይ አይመስለኝም።

ስርነቀል ወይስ የጥገና ለውጥ?

በኢትዮጵያ ለውጥ መደረግ የነበረበት የህወሀት የጥፋት መርዝ ስር ሳይሰድ በመጀመሪያወቹ ሁለትና ሶስት አመት የወያኔ የስልጣን ዘመን መሆን እንደነበረበት ቢሰማኝም አሁንም የቆሰለው አውሬ ሳያገግም በተጋጋለው የወጣቶች ትግል ታጅቦ መቀጠሉ የዚህን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ራእይ የሁላችን የጋራ ራእይ የማድረግ አቅም በመስጠት ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር በብዙ ምክኛቶች ወደሑዋላ ልመልከት ቢሉ እንኳን እንደሎጥ ሚስት እንደጨው አድርቆ የሚያስቀራቸው ይሆናል።

እነዶ/ር አብይ ሚና በለውጥ ሚዛን ሲታይ የጥገና ለውጥ አራማጅ (reformist) ሚናው ጎላ ይላል። ይህ የለውጥ አይነት ብዙዎቻችን ከወያኔ እኩይ ተልእኮ ልምድ በመነሳት የማንቀበለው ቢሆንም በአንጻሩ ከወያኔ ሀገሪቱ የተሰራችበትን ድርና ማግ የመበታተን የሩብ ምእተ አመት እኩይ ስራ በኋላ የሐገሪቱን የፓለቲካ አቅጣጫ በቀላሉ ወደ አዲስ ስርነቀል የለውጥ መንገድ መዘወር የራሱ የሆኑ ተፈጥሮአዊ አደጋውም የከፋ ውጤት ሊያመጣ መቻሉን ማሰተዋል የግድ ይላል። ይህንንም ሂደት የወጣቱ የትግሉ ወላፈን ለኣፍታም እንኳን ሳይቋረጥ ይህንን መሰረታዊ ሊባል የሚችል ግን የጥገና ለውጥ በጥሩ ተስፋና ቅቡልነት መመልክቱ ተገቢ መስሎ ይሰማኛል።

በመጨረሻም ለስር ነቀል ለውጥ ብንጓጓም እንኳን በምድር ላይ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ የስርነቀል ለውጥ አራማጅ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አደረጃጀት የደረሰበት የእድገት ደረጃ እምብዛም የበሰለ ተስፋ ፈንጣቂ አለመሆኑን መመልከታችን ወደቲም ለማ ለማሸብረክና ሐገርን ከጥፋት ለመታደግ የመጣ ቅርብ እድል መሆኑን በማሰብ በተስፋ እንድንመለከተው ያደርገናል።

እንደማጠቃለያ

ይህንን አጭር ጽሁፍ ስሞነጫጭር ዶ/ር አብይ ቃለመሐላ አድርገው የተናገሩትን የመጀመሪያ ጠቅላይ ሚኒስትራዊ ንግግራቸውን ደጋግሜ አዳመጥኩ። ፓርቲያቸውን ኢህአዴግን ሲያመሰግኑ ለወያኔ ባለሐብቶችም በህዝብ አመጽ እንዳይዘረፉ ዋስትና ሲሰጡ ባዳምጥም ከለውጣቸው እስትራተጂነት ወይንም ከመሳሰሉ ቀጣይ ቅን መሰል ጉዞዎች በዘለለ መሰሪ ወይንም ግልብጥብጥ ያለ ሐይለማርያማዊ ስነምግባር የጎደለው ተላላኪነት አይመስልም። ከግል የቤተሰባቸው ትርክት፣ ከቀደም የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከዘረኝነት ጥላቻም ሆነ ለወደቁ ወጣት የለውጥ ተፋላሚዎች ይቅርታ አጠያየቅ ስመለከት በጣም ተመሰጥክ አትበሉኝና ይህ ነው የምለው እንከን አላገኝሁባቸውም።

ይልቁንም በቃላቶቻቸው ለቤተመንግስቱ ርቆ የነበረውን የከበረ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ በድፍረት በመናገራቸው ቤተመንግስቱን የተጥናወተው ተጻራሪ ኢትዮጵያዊ መንፈስ እንዳይተናኮላቸው ሰጋሁ፥፥

እግዚአብሔር አኢትዮጵያን ይጠብቅ አሜን!

ከበቀለ ደገፋ (t.mesafint@gmail.com)
ሚያዝያ 2010 ዓ.ም.


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule