• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የዶ/ር አብይ አህመድ አዋላጅነት ጉዳይ

April 20, 2018 05:38 am by Editor 1 Comment

ቃሉ የሕዝብ ነው። ቃሉንም በተግባር የሚተረጉመው ሕዝብ ነው። የወንዝ ውሃ ሽቅብ እንደማይፈስ ሁሉ፥ ይህም ቃል ወደ ተግባር ሳይቀየር ይቀለበሳል ብሎ መጠበቅ ተገቢ አይደለም። ይልቁንስ ይህን ቃል ለመተግበር የዶ/ር አብይ ድርሻ ምንድነው ብሎ አውቆ በዚያው ሚዛን ብቻ እርሳቸውን መመዘን ያስፈልገናል። ለሕዝብ ታማኝ ባይሆኑ፥ እሳቸው ከታሪካዊነት ይጎድላሉ እንጂ የሕዝብ ቃል ዕውን መሆኑ አይቀሬ ነው። ዶ/ር አብይ አህመድ የሚናገሩት ቃል እርሳቸው የፈለሰፉት ስለሆነ አይደለም የተወደደው። ቃሉ የሕዝብ ቃል ስለሆነ ነው እንጂ። ይህ ሰሚ ያጣ ሕዝብ በትግሉ የራሱን ቃል የሚያስተጋባ ጠ/ሚ ሊያመጣ ቻለ። ታዲያ ይህን ቃል የዶ/ር አብይ የግል ንብረት ተደርጎ፥ ቃል ዋጋ የለውም ብሎ ቃሉን ማጣጣል ለኢትዮጵያ አይጠቅምም። የውልጃ አብሳሪ የሆነ ቃል በውልደት ቀን ዋዜማ ሲሰማ፥ በተስፋና በትጋት ይህን የሕዝብ ቃል በክብር መያዝ ይገባል። ይህ ታላቅና አስገራሚ ሕዝብ ቃሉን በአደባባይ ካሳወጀ በሁዋላ፥ ይህ ቃል አይተገበርም ማለት የቃልን ምንነትና የቃሉ ነፀብራቅ የሆነውን ሕዝብ ማንነት ያለማወቅ ነው።

ከአሁን በሁዋላ በምድራችን የሚሆነውን ነገር ለማወቅ ከተፈለገ ወደ ፊት በማየት ማገናዘብ እንጂ ወዳለፈው ታሪካችን እየተመለከትን ሽንፈትን ማስተናገድ አይበጅም። በመጀመሪያ ቃል ተወለደ። ይህ ቃል ቀጥሎ ዲሞክራሲን ይወልዳል። ዲሞክራሲ ሁሉን የኢትዮጵያ ልጆችን አሳትፎ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ያስወልዳል። ስለዚህ ይህ የታወጀው ቃል የምጥ መጀመሪያ ነው። ያለፈውን የእርግዝና ወቅት ሳይሆን አሁን ያለውን አዲስ የምጥ ሂደት ማስተናገድ ይገባናል። መወለድን ማስተጓጎል ቀርቶ ማዘግየት የሚቻልበት ወቅት ላይ አይደለንም።

እናስተውል። አሁን ቸኩለን ስለ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ማውራትና መጠየቅ አንችልም። አሁን ዶ/ር አብይን በቅድሚያ የዲሞክራሲ አዋላጅነታቸውን ግዴታ እንዲወጡ ብቻ በተጠያቂነት መያዝ ይኖርብናል። ከዚያ ዲሞክራሲ ተቃዋሚ የሆኑትን ሃይላት ወደ አማራጭ ሃይልነት ቀይሮ ተባባሪ አዋላጅ ያደርጋቸዋል። ያኔ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብን ያሳተፈ ሂደት አዲሲቷን ኢትዮጵያ እንድትወለድ መቻልን ያመጣል። ሁሉንም የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚዳኝ ሕዝብ ነው። ለዚያ ዲሞክራሲ የመጀመሪያው መሰረት ነው። ስለዚህ ይህን የሕዝብ ቃል ይዘን ዲሞክራሲ በቅድሚያ ይወለድ ዘንድ ግድ እንበል።

ኢትዮጵያን በጎሰኝነት ከፋፍሎ ሊበትን ጠላት ያቀደው በቃል ነበር። ፈጣሪ ኢትዮጵያን ወደሚጠብቃት ታላቅ ክብርና ሞዴልነት የሚወስዳትን ጉዞ የሚያስጀምረውም በቃል ነው። የአዋላጅነት ተልዕኳቸውን እንዲወጡ ዘብ መቆም እኛም ከአዋላጆቹ ጎራ እንድንመደብ ያደርገናል። ዶ/ር አብይን በብዙ ጉዳይ እያዋከብናቸው እና አፍራሽ ቃል በመጠቀም ጥሪያቸውን እንዳይወጡ ለጠላት መጠቀሚያ እንዳንሆን እንወቅበት። በዶ/ር አብይ አዋላጅነት ሊሆን ያለውን ድል እንቅፋት እንዳንሆን መጠንቀቅ እጅግ ያስፈልገናል። ይህን የኢትዮጵያ ልጅ ለመውቀስም ሆነ ለማሞገስ አንዱንና ብቸኛውን ዲሞክራሲ ላይ ትኩረት በማድረግ መሞገትና ተጠያቂ ማድረግ መልካም ነው።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!

ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

ኢሜል: ethioStudy@gmail.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Lemma says

    April 25, 2018 07:50 pm at 7:50 pm

    This doctor uses his brain to think positive, and objectively. Endih yemitasibu berket belu, bizu.
    It is clear that reform does not bring us to our goal, but it is, if we take part in utilizing, a step toward our final show-down.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule